>

‘’ጓደኛህን ንገረኝ ማንነትህን እነግርሃለሁ"

‘’ጓደኛህን ንገረኝ ማንነትህን እነግርሃለሁ”


“Don’t expect a pigeon from the eggs of a snake”

ሰሞኑን ዘመነ ካሴ “እንደፋኖ እንምከር ” አለ የምትል አጀንዳ ማህበራዊ ሚዲያውን አጨናንቃ ባይ እንደተለመደው ትዝብቴን ለማጋራት ተገደድኩ። 

“ወደው አይስቁ” አሉ አበው።  ነገርየዋ እኔንም ሳልወድ ፈገግ አሰኝታኝ ነበር። 

የብአዴን ካድሬዎች ከአባታቸው ወያኔ የወረሷት አንድ የተለመደች የማጭበርበሪያ ስልት አለቻቸው። ሰላም አደፍርሰው ሰላም ፈላጊ፣ የጦርነት ጠማቂ እነሱ ሆነው ሳሉ የሰላም አምባሳደር፣ በክፋት የተሞሉ እባቦች ሳሉ ፡ የዋህ ነጫጭ እርግብ መስለው ይታያሉ። ገድለው ጥቁር ለብሰው እያነቡ ገዳዩን ያፋልጋሉ፣ ከተጎጂው ቤተሰቦች ጋር አብረው ለቅሶም ይቀመጣሉ። 

ዘመነ ካሴም ከብአዴን በተማራት በዚህች ጥበብ በተደጋጋሚ ተከታዮቹን ለማደናገር ሲደክም ይታያል። ሰሞኑን ባቀረባት ዲስኩር አንዳንድ የዋሃን ከመቀመጫቸው ተነስተው ሲያጨበጭቡ አይቸ አዘንኩላቸው። 

ዋናው የዐማራ አንድነት ጠንቅ እሱ ዘመነ ሆኖ ሳለ ለሌሎች የአንድነት ጥሪ ያቀርባል። ዋናው የስልጣን ጥመኛ እና ወንበር ናፋቂ እርሱ ሆኖ ሳለ ሌሎችን በስልጣን ጥመኝነት፣ በእንቅፋትነት ይከሳል። እርሱ ከህወሃት ጋር በአደባባይ አንሶላ እየተጋፈፈ ሌሎችን የዐማራ ትግል ሻጭ ፣ ከሃዲዎች ፣ ባንዳዎች አድርጎ ይከሳል። ግሪሳ አሰማርቶ ይወነጅላል። እርሱ ራሱ የሃሳብ የበላይነት እና የዲሞክረሲ ፀር ሆኖ ሳለ ሌሎችን በአምባገነንነት ይከሳል። 

አብይ አህመድን እና ዘመነ ካሴን ከሚያመሳስላቸው በርካታ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ግሪሳውን በማደናገር ለመግዛት የሚያደርጉት ጥረት ነው።  ግሪሳው Short memory ስላለው የዛሬውን እንጂ የትናንቱን አያስታውስም። 

ዋናው ጥያቄ በዚህ ውስጥ ዘመነ ማስተላለፍ የፈለገው ቁልፍ የፕሮፓጋንዳ ጭብጥ ምንድነው ? የሚለው ነው። በጣም ግልፅ ነው። እርሱ ሁልጊዜም ቢሆን አንድነት ፈላጊ መሆኑን፣ ሌሎች ደግሞ ከአንድነት በተፃራሪ መቆማቸውንና ትግሉን ማዘግየታቸውን፣ እንቅፋት መሆናቸውን ለነ Short memory ማስታወስ ፣ እጃቸው እስኪግል ማስጨብጨብ ፣ የዐማራ አንድነት ጠበቃ መስሎ መቅረብ፣ ሌሎችን በማሳጣት የፕሮፓጋንዳ ነጥብ ማስቆጠር! 

 የዘመነ ካሴ ፓለቲካ በአጭር አገላለፅ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ፓለቲካ ነው።” ዘመነ ካሴ እንደ አብይ አህመድ እናቱ ባይነግሩትም ራሱን በምናብ በዐማራ ህዝብ ላይ ያነገሰ አሳዛኝ ሰው ነው። ለዚህ ማሳያ እሩቅ ሳንሄድ በሁለቱ ድርጅቶች (ዐፋህድ እና ዐፋብኃ) ምስረታ ወቅት እኔ ካልመራሁት የዐማራ ህዝብ ትግል በአፍጢሙ ይደፋ ብሎ ከአንዴም ሁለት ጊዜ የዐማራ ህዝብ አንድ አታጋይ ድርጅት እንዳይኖረው የተጫወተው ግልፅ አፍራሽ ሚና መጥቀስ ይቻላል። 

ለዘመነ ካሴ አንድነት ማለት በዐማራ ስም መሰባሰብ እና እርሱን የዐማራ ህዝብ ንጉስ አድረጎ ማንገስ ነው። ከዚህ በመለስ ያለ ማንኛውም የአንድነት ጥሪ በዘመነ ካሴ መዝገበ ቃላት ተቀባይነት የለውም። ይህ ደግሞ ከአብይ አህመድ መዝገበ ቃላት የሚለየው በአማርኛ በመፃፉ ብቻ ነው። 

ዘመነ ካሴ ልዩነቶችን የመቀበል፣ የሃሳብ የበላይነትን የማስተናገድ፣ ዴሞክራሲያዊ አሰራሮችን ለመቀበል አቅሙም ብቃቱም የለውም። በተደጋጋሚ በተግባር ተፈትኖ ወድቋል። የልዩነት ሃሳብ የነበራቸውን በሙሉ አሳዷል፣ አስ ሯል ፣ አስድዷል፣ ገድሏል። 

እንደማሳያ ኮሎኔል ጌትነትን፣ ካፕቴን ማስረሻ ሰጤን፣ ዶ/ር እንዳላማው፣ ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው እና ሌሎች የደረሰባቸውን ማንሳት ይቻላል።  አሁን ደግሞ ወሎ ተሻግሮ ከብአዴን ፋኖ ጋር በመናበብ ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሃቤን ለማስገደል እንቅልፍ አጥቶ በመስራት ለይ ይገኛል።

ብአዴን የሃሳብ ልዩነቶችን የሚያስተናግደው በማሰር፣ በማሳደድ፣ በመግደል እና ደብዛውን በማጥፋት ነው። የብአዴን ደቀመዝሙር ዘመነ ካሴ ጥርሱን የነቀለው ብአዴን ቤት ይህን እያየ ነው። በዘመነ ካሴ መዝገበ ቃላት ስልጣን የሚገኘው የምርጫ ኮሮጆ በመገልበጥ፣ በማጭበርበር እና በማጨናበር ብቻ ነው። ስለሆነም ከዘመነ ካሴ እና እሱ ከሚመራው ድርጅት /ዐፋጎ የዐማራ አንድነት ብስራት ከመስማት ከእባብ እንቁላል እርግብ መጠበቅ ይቀላል! 

እስቲ አንድ ቁልፍ ጥያቄዎች እናንሳ። ለመሆኑ ዘመነ ካሴ ማነው? ይህ ጥያቄ ብዙዎቻችሁን እንደሚያስገርማችሁ ግልፅ ነው? Truly speaking who is Zemene Kassie? Do you really know him? እኔም በአካል አላውቀውም! ታዲያ ማንነቱ እንዴት ታወቀ አትሉኝም? መልሱ በጣም ቀላል ነው። በስራዎቹ!!!

የሚያስብ፣ የሚያገናዝብ፣ የሚሰራ አእምሮ ካለህ እነዚህን ጥያቄዎች ጠይቅ ወይም መልስ! 

ለመሆኑ

1ኛ. “ዐማራን እና የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን አከረካሪ ሰብረናል” ካለው ስብሃት ነጋ ጋር “የዐማራ ታጋይ” ዘመነ ካሴ ምን አገናኘው? 

2ኛ. “ለትግራይ ህዝብ ከዐማራ ይልቅ የሱዳን ህዝብ ይቀርበዋል” ብሎ ከልቡ ከሚያምነው ደ/ጽዮን ገ/ ሚካኤል ጋር “የዐማራ ታጋይ” ዘመነ ካሴ ምን አገናኘው?

3ኛ. የዐማራ ህዝብ አፅመ ርስቶች ወልቃይት፣ ጠጌዴ እና ራያ የትግራይ አካል ናቸው። እነዚህን ሳናስመልስ እንቅልፍ የለንም ከምትል ህወሃት ጋር “የዐማራ ታጋይ” ዘመነ ካሴ ምን አገናኘው ?

4ኛ. ዐማራ ጨቋኝ ገዢ መደብ ነበረ፣ ሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች የዐማራ ባህል፣ቋንቋ፣ ሃይማኖት ለዘመናት ተጭኖባቸው የኖሩ እስረኞች ናቸው። “ኢትዮዽያ የብሔር ብሔረሰቦች እስር ቤት ነበረች” ብላ የሀገሪቱን ህገመንግስት ፅፋ፣ ብሔር ብሔረሰቦችን አስጠንታ፣ ዐማራ በጠላትነት እንዲታይ፣ እንዲፈረጅ፣ እንዲሳደድ፣ ንብረቱ እንዲወድም፣ እንዲገደል፣ በገዛ ሀገሩ ላይ እንደ መጤ፣ ወራሪ እና ሰፋሪ እንዲታይ ፣ ለማኝ እና ስደተኛ እንዲሆን እንቅልፍ አጥታ ከሰራችው አሁንም ከምትሰራው ህወሃት ጋር “የዐማራ ታጋይ” ዘመነ ካሴ ምን አገናኘው? 

5ኛ. ከዐማራ ጋር የምንጋራው ሀገርም፣ ባህልም፣ ሀይማኖትም የለንም፣ ኢትዮዽያ የዐማራ ኢምፓየር ናት ፣ ኦርቶዶክስም የዐማራ ሃይማኖት ነው ። ከዐማራ ጋር የምንጋራው መቅደስም መሰጂድም የለንም። ከምትል ህወሃት ጋር “የዐማራ ታጋይ” ዘመነ ካሴ ምን አገናኘው? 

6ኛ. ዐማራ systematically ከመንግስታዊ ስርዓት እንዲገለል፣ የህዝቡን ቁጥር systematically በመቀነስ የበጀት፣ የፓርላማ ውክልና አሻጥር እንዲስራ ካደረገች፣ ዐማራ እንደህዝብ ጄኖሳይድ እንዲፈፀምበት ካደረገች ህወሃት ጋር ጋር “የዐማራ ታጋይ” ዘመነ ካሴ ምን አገናኘው? 

7ኛ. ከዐማራ ታሪካዊ ጠላት፣ ከዐማራ መከራ ጠንሳሽ/ master mind ከህወሃት መሳሪያ ተቀብሎ ለዐማራ ሊሞቱ በወጡ ፋኖዎች እና የዐማራ ፋኖ አመራር በሆኑት ኮ/ል ፈንታሁን ሙሃቤ ላይ የተኮሰው  “የዐማራ ታጋይ” ዘመነ ካሴ ማነው?

8ኛ. የዐማራ ታጋይ” ዘመነ ካሴ ከደብረፅዮን ይልቅ ለምን እስክንድር ነጋ፣ ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሃቤ፣ አርበኛ ደረጀ በላይ ፣ ሻለቃ መከታው ማሞ ስጋት ሆኑበት?! ከህወሃት ይልቅ የዐማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ላይ ለምንስ ጦርነት ከፈተ? ከዐማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ይልቅ ለምን ከህወሃት ጋር አብሮ ለመስራት፣ ጡት ለመጣባት፣ አንሶላ ለመጋፈፍ መረጠ???

“ጓደኛህን ንገረኝ ማንነትህን እነግርሃለሁ” ይላል አበሻ! 

ፈረንጆቹ ደግሞ

“Birds of the same feather flock together” ይላሉ። 

This is how I came to know him. I hope now you know him too!!!

@Dagmawit Getaneh

Filed in: Amharic