>

ህያዋንን ለማየት ህያው መሆን ይጠይቃል!

ህያዋንን ለማየት ህያው መሆን ይጠይቃል!

ሙታኖችን ህያውያኖች ያያቸዋል እንጂ ሙታኖች ህያዋንን ፈጽሞ ማየትም ሆነ ማወቅ አይችሉም!!!

ይድረስ ጭንቅላትህ ሞቶ ህያውን የግእዝ ቋንቋን ሞ

ሙቷል ብለህ በድፍረት ለተናገርከው የዋቅጅራ ልጅ በድሉ ዋቅጅራ!!!

ህያውን ከሙታን መለየት አልቻልክም!!!

ለመሆኑ የሞቱ ቋንቋዎች (Dead Languages) ተብለው በተለየ ሁኔታ ተለይተው የሚጠቀሱት ቋንቋዎች ምን አይነቶቹ ናቸው?!??

እንደ የዋቅጅራ ልጅ በድሉ አገላለጽ አንድ ቋንቋ የአፍ መፍቻነት ካላገለገለ የሞተ ቋንቋ ነው ባይ ነው።
የአፍ መፍቻ ቋንቋ ማለት አንድ ህዝብ አፉን የሚፈታበት ቋንቋ ምለት ነው። ነገር የቋንቋ ጠበብቶች አንድን ቋንቋ ሙታል ብለው ለመደምደም ከሚያስቀምጡት መስፈርቶች ውስጥ ቋንቋው የአፍ መፍቻ መሆን ካልቻለ ብለው ያስቀመጡት – ከመስፈርቶቹ ውስጡ እንደ አንዱ አድርገው ነው እንጂ የአፍ መፍቻ ያልሆነ ቋንቋ በሙሉ የሞተ ነው የሚል መደምደሚያ ላይ አላስቀመጡም።

አንድ ቋንቋ ሞተ  የሚባለው

– ለአፍ መፍቻነት የሚጠቀመው ሲያጣ
– ለሥነ ጽሁፍነት የሚጠቀመው ሲያጣ
-በፊደል እና በድምጽ ምንም አይነት አገልግሎት መስጠት ሲያበቃ
-በቤተ እምነት፣በታሪክ ተቋማት አገልግሎት መስጠት ሲያበቃ
ቋንቋው ሙታል ተብሎ ይደመደምና በታሪክ መዛግብት ውስጥ እንዲቀመጥ ይደረጋል።

ለአብነትም ያህል

ሱሜሪያን- (Sumerian )
አርኬዲያን -( Akkadian) አይነት ቋንቋዎች Literally የሞቱ ቋንቋዎች (Dead Languages) ተብለው ይገለጻሉ።

እነዚህ የሞቱ ቋንቋዎች ተብለው. የሚገለጹት – የአፍ መፍቻ ቋንቋ መሆን ስላልቻሉ ብቻ ሳይሆን በእምነት ተቋማት፣ በስነ ታሪክ ዘርፍ ዛሬ ላይ ጥቅም ላይ ያልዋሉ በመሆናቸው የሞቱ ቋንቋዎች ይባላሉ።

የግእዝን ቋንቋ ከእነዚህ ቋንቋዎች ጋር እያነጻጸርን ብንመለከተው ቋንቋውን እንደ ህዝብ አፍ መፍቻው አድርጎ የሚጠቀመው የህብረተሰብ ክፍል የለም ብለን እናስቀምጥና – ሆኖም ግን ቋንቋው በእምነት ተቋማት ውስጥ የአንድ ሀይማኖት (ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን) ስርአተ መንፈሳዊ ትምህርት መማሪያና ስርአተ አምልኮ ማገልገያ ቋንቋ ሆኖ ስንመለከት – ግእዝን እንደ ቋንቋ አፍ መፍቻው ያደረገ ብሄር/ ማህበረሰብ የለም እንልና የግእዝን ቋንቋ ለስርአተ አምልኮ አስተምህሮት አፍ መፍቻው ቋንቋ ይደረግ የእምነት ማህበረሰብ እንዳለ እንመለከታለን ማለት ነው።

የግእዝ ቋንቋ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን

-Liturgical
-Prayers
– Hymns እለት በእለት እያገለገለ ያለ ቋንቋ ከመሆኑም በላይ ለአማርኛ እና ለትግሪኛ ቋንቋዎች Subsidiary ሆኖ እያገለገለ ያለ – የኢትዮጲያም ታሪክ እንደ ክብረ ነገስትን ጨምሮ በርካታ መንግስታዊ ዜና መዋእሎች የተጻፈበት ቋንቋ እንደመሆኑ መጠን እነዚህን የታሪክ መዛግብት የሚያገላብጥ በሙሉ የግእዝን ቋንቋ መናገር ይጠበቅበታል።

የግእዝ ቋንቋ ምንድነው ብለን ጠቅለል አድርገን ብናየው ግእዝ ብደቡባዊ ምስራቅ የሚኖሩ ሴሜቲክ ህዝቦች – በዛሬይቱ ኢትዮጲያና ኤርትራ ያሉ ህዝቦች እስከ 12ኛው ክፍለዘመን ድረስ (አጼ ይኩኑ አምላክ ሀይቅ ላይ ከነገሰበት በ1258 ድረስ ) የኢትዮጲያ ብሄራዊ ቋንቋ ሆኖ ያገለገለ ሲሆን ከአረቢኛ እና ከእብራይስጥ ቋንቋዎች ጋር የሚወራረስ የአንድ ቋንቋ ቤተሰብ አካል ነው።

በዚህም ምክንያት የግእዝ ቋንቋ በዛሬይቱ ኤርትራና ኢትዮጲያ ውስጥ የሚነገሩ የትግሪኛንና የአማርኛን ቋንቋዎችን የወለደ ሲሆን ትግሪኛ ቋንቋ ሙሉ በሙሉ የግእዝ የመጀመሪያ የበኩር ልጅ በመሆን ግእዝን ይጠቀምበታል። ወደ አማርኛ ቋንቋ ብንመጣ አማርኛ በራሱ የበለጸገ ቃላት እጥረት ሲያጋጥመው መለስ ብሎ ቃላትን የሚቀዳው ከእናቱ የግእዝ ቋንቋ ነው።

ለምሳሌ ያህል አዳዲስ የፈጠራ ግኝቶችና የቴክኖሎጂ ውጤቶች ወደ ገበያ ሲቀርቡ ከአማርኛ ቋንቋ ያንን አዲስ ግኝትንና አዲስ ቴክኖሎጂን ምርት ስም ማውጣት ይከብዳል። እናም አማርኛ ወደ እናቱ ግእዝ መለስ እያለ – ተዝቆ ከማያልቀው የግእዝ ቋንቋ ቃላትን እየጨለፈ በመጠቀም አማርኛን ቋንቋ ዘመኑን የዋጀ ቃላት ባለቤት እንዲሆን አድርጎታል።

ለምሳሌ አይሮፕላን – የአማርኛ ቋንቋ አይደለም። እንግሊዘኛ ነው። አይሮፕላንን በአማርኛ የምንጠራው ጢያራ ብለን ነው። መኪና የሚለው ቃል አማርኛ አይደለም። የጣሊያን ቋንቋ ነው። መኪና በአማርኛ ተሽከርካሪ ብለን ነው የምንጠራው። ለመኪና – ተሽከርካሪ- ለአይሮፕላን – ጢያራን ቃላት ያገኘነው ከግእዝ ቋንቋ ነው።

ቋንቋ ህያው ነው። ሙታኖች ህያዋንን አያውቁም!!!

መጀመሪያ ቃል ነበረ፣ ቃልም ስጋ ሆነ ይላል የእግዚአብሔር ቃል። በቃል ውስጥ ህይወት ባይኖር ቃል ስጋ አይሆንም ነበር። እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን፣ እን በውስጡ ያሉትን ፍጥረታትን በሙሉ የፈጠረው በቃል ነው። “ብርሃን ሁን አለ፣ ብርሃንም ሆነ ብርሃንም ጥሩ መሆኑን አየ፣ ውሃ ይሁን አለ ውሃ ሆነ-ወዘተ እያለ እግዚአብሔር ፍጥረታቱን የፈጠረው በቃል እንደሆነ መጽሀፍ ቅዱስ ይገልጻል። ይህንን አገላለጽ ሳይንሱ በ Big bang theory አንዲት ቅንጣት አተም ፈንድታ ዩንቨርሱን ፈጠረች ይለናል። የሚታየውን ግዙፉን ዩንቨርስ በማይክሮስኮፕ እንካን የማይታየው Dark Energy ዩንቨርሱን 85% እንደሸፈነው ይገልጻል።

ቃል ይፈጥራል። ቃል ያድናል። ቃል ይገድላል። ቃል አይታይም አይዳሰስም። ቃል የቋንቋ መግለጫ muth piece ነው።
እናም ቃል ደግሞ ህይወት ያለው ህያው ነው። የዋቅጂራ ልጅ በእድሉ ግእዝ ቋንቋ ሙታል ብሎ ሲገልጽ እሱ ያለበትን የህይወትና የአእምሮ Status መግለጽ ነው። ያም ስታተስ የሞተ አእምሮ ስታተስ ነው። የሰውዬው Boddy ( Avatar)ህያው ነኝ ብሎ እየተንቀሳቀሰ ይሆናል። የሰውን ልጅ ክቡር Human Conscious የሚያስበለውን ጠቢቡን የአእምሮውን ክፍል ካጣ አለሁ ቢልም የሌለ ሙታን ነው።

The absence of light (Photons) called Darkness) ጨለማ ማለት የብርሃን አለመኖር/የብርሃን መጥፋት ማለት ነው። ብርሃን ባለበት ጨለማ የለም።
ብርሃን ደግሞ ህይወት ነው። ህያው ነው። ሞት መጨለም ነው። ሞት መጥፋት ነው። ሞት በህይወት ያለመገኘት ነው።እንደ መንግስታዊው ስታትስቲክስ ዳታ ውጤት ከሆነ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከ 50 ሚሊዮን በላይ አባላት አላት። እነዚህን ምእመናኖቻንም የምታስተምረው በግእዝ እና በአማርኛ ነው። ስርአተ ትምህርቱ የተጻፈው በግእዝ ቢሆንም እየተተረጎመ ትምህርቱ የሚሰጠው በአማርኛ ነው። ነገር ግን ስርአተ ቅዳሴው በሙሉ በግእዝ ነው።

ከዲያቆኑ እስከ ጳጳሱ የተማሩት በግእዝ ነው። የሚያስተምሩትም በግእዝ ነው። ይህ ጸሀፊ እንካን በአቅሙ ከውዳሴ ማሪያም በእለተ ሰኑይ ጀምሮ እስከ እለተ ሰንበት አልፎ አንቀጸ ብርሃንና ይወድስዋ መላእክትን እና ሰላም ለኪን የተማረው በግእዝ ነው። ዳዊት ፍካሬ ዘጻድቃን ወዘ አጥን -መዝሙር ዘዳዊት ——- ለምንተ አንገለጉ አህዛብ ወዘተ እያለ ከ150 በላይ ምእራፍ ያለውን ዳዊት የድርገመው በግእዝ ነው። እናም የግእዝ ቋንቋ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አፍ መፍቻ ቋንቋ ተብሎ መገለጽ በሚቻልበት ሁኔታ የዋቅጂራ ልጅ ይህንን ህያው የሆነን ቋንቋ መረዳትና ማወቅ ተስኖት ግእዝ የሞተ ቋንቋ ነው በማለት በድፍረት ለመናገር የቻለው ቋንቋው ሞቶ ሳይሆን የዋቅጂራ ልጅ ጭንቅላት በበታቸኝነት በሽታ የሞተ ስለሆነ ህያው የሆነውን ቋንቋ ማወቅና መረዳት ስላልቻለ ነው።

መደምደሚያ

የአማራ ክልላዊ መንግስት በ2018 የመማር ማስተማር ፕሮግራም ላይ ከ3ኛ ክፍል ጀምሮ ግእዝን እንደ አንድ Subject ማስተማር እጀምራለሁ ብላል።

አይደለም የግእዝን ቋንቋ ለማስተማር ይቅርና ከ 5,8 ሚሊዮን በላይ አማራዊያን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ሙሉ በሙሉ ታግደው ቤት መዋል ከጀመሩ ድፍን ሁለት አመት አልፎታል። ከስድስት ሺህ በላይ የትምህርት ተቋማት ወድመው የጨፍጫፊው እና የወራሪው የብልጽግና ሰራዊት መከማቻ ካምፕ ሆነዋል።

ጽድቁ ቀርቶ በቅጡ በኮነነኝ እንዳሉ፣ የግእዝን ቋንቋ እናስተምር አታስተምሩም የሚለውን ጉንጭ አልፋ ክርክር መላው አማራ እርግፍ አድርጎ በመተው ህዝባችንን ከተጣበቀበት ጨቋኝ ወራሪ ስርአት ነጻ በማውጣቱ ትግል ላይ ነው ሙሉ ግዜያችንን እና አቅማችንን አውለን መረባረብ የሚገባን።

አማራው ዛሬ አይደለም ቋንቋውን ግእዝ አትማርም መባል ይቅርና በአማራነትህ አትኖርም ተብሎ የተፈረደበት ህዝብ እንደመሆኑ መጠን የግእዝ ቋንቋ ሙታልን ብልጽግናዊን ቃል – አእምሮአቸው በበታቸኝነት ስሜት በሽታ ከሞተባቸው ጸረ አማራ ሀይሎች ጎራ የተወረወረ ቃል መሆኑን ተረድተን አትኩሮቶችንን በሙሉ በስርነቀል ለውጥ ህዝባችንን ነጻ ለማውጣት ትግሉ ላይ ማድረግ ይኖርብናል።

ህዝባችንን ከባርነት ነጻ ስናወጣ አይደለም የግእዝን ቋንቋ በ Subject ደረጃ ማስተማር ይቅርና – ይጠቅመናል ብለን ከፈለግን ግእዝን የአማራ ህዝብ መግባቢያ እና አፍ መፍቻ ቋንቋ ማድረግ እንችላለን። እስከዚያው ግን መላ አትኩሮታችን በሙሉ በህልውና ትግሉ ላይ እናድርግ። ዛሬ ፋሺስቱ ብልጽግና የግእዝን ቋንቋ አይደለም በአማራ ክልል ይቅርና በመላው ኢትዮጲያ እንደ አንድ Subject ትምህርት መሰጠት አለበት ብሎ ቢያውጅ እንካን የነገደ አማራ ህዝብ ሁለንተናዊ መብት ተክብራል፣ የህልውናውም አደጋ ተቀልብሳል ማለት አይደለም። እናም መላው የአማራ ህዝብ ፣ ትንሽ ትልቅ፣ ተማሪ አስተማሪ፣ ምሁር ወዛደር፣ ባለሀብት አርሶ አደር፣ ሴትና ወንድ ሳይል ሁለንተናዊ አትኩሮቱን በህልውና ትግሉ ላይ ያድርግ። ነጻ ስንወጣ እማይገደብ፣ እማይሸራረፍ ተፈጥሮአዊ መብታችንን እናስከብራለን። አበቃሁ።

ወንድወሰን ተክሉ

Filed in: Amharic