አፋሕድ – አፋብኃ እና የፋኖ አንድነት
አፋሕድ እና አፋብኃ ምን እና ምን ናቸው?
አፋብኃ ከሁለት ወር በኃላ ከ10ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ እሰበስባለሁ እያለ ሲያስተዋውቅ – አፋሕድ ደግሞ አመራሮችን ወደ ሚዲያ እየላከ ስለ አማራ ፋኖ አንድነት ሲወተውት ይደመጣል?!! የአንድነት መንገድ ይህ ነውን!?
What’s the building blocks of Unity ?
ጋዜጠኛ ወንድወሰን ተክሉ
የአፋሕድ አመራሮች አርበኛ ጌታ አስራደ እና አርበኛ ምንተስኖት በትናንትናው እለት ከ360 ሚዲያው ጋዜጠኛ ብሩክ ይባስ ጋር ያደረጉትን አጭር ቃለ ምልልስ ላደመጠ አፋሕድ ምን ያህል ስለ አማራ ፋኖ አንድነት Committed እንደሆነ ብቻ ሳይሆን Disparate እንደሆነም ጭምር ይገነዘባል።
ሁለቱ አመራሮች ሕዝባዊ ድርጅቱ ( ድርጅቱን ደጋፊ አልባ አድርገው እርቃኑን ባስቀሩት በእነ ግዛቸው ጠሪነት) ለነገ መስከረም 20 እና 21 ቀን 2025 ስላዘጋጀው የ “አማራ ፋኖ አንድነት ጉባኤ” ጉዳይ ሲያብራሩ በጉባኤው ላይ የአፋብኃ አመራሮች እነ አርበኛ ዘመነ ካሴ፣አርበኛ ሀብቴ ወልዴ፣ አርበኛ ምሬ ወዳጆና አርበኛ ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ ተገኝተው ስለእማራ ፋኖ አንድነት መልእክት እንዲያስተላልፉ በክብር እንግድነት ተጋብዘዋል- ግብዣውንም በደብዳቤ ልከንላቸዋል፣ በተጨማሪም እነሆ በድምጽም በድጋሚ ጥሪውን አስተላልፈናል ሲሉ ተደምጠዋል።
አፋሕድ ስለ አማራ ፋኖ አንድነት በአመራሮች እንዲህ በአደባባይ ወጥቶ ሲናገር ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ከሳምንት በፊት አራት የአፋሕድ አመራሮች አርበኛ ደረጀ በላይ ፣ አርበኛ መከታው ማሞ፣ አርበኛ ኮ/ል ፋንታሁን ሙሀባ እና እርበኛ ምንተስኖት ስለ አማራ ፋኖ አንድነት መልእክት እንዲያስተላልፉ አድርጋል።
አፋሕድ ደጋግሞ በአደባባይ ከሚገልጸው የአንድነት ጥሪ ባሻጋር በተጨባጭ – ስል አንድነቱ. ብሎ ብዙ እጅግ ብዙ እያደረገ ያለ ድርጅት ነው። እየተተኮሰበትና አመራሮችና አባላቱም እየተገደሉበትም የአጻፍ ምላሽ ባለ መስጠት የህይወት ዋጋ እየከፈለ የአማራን ፋኖ ከእርሰበርስ ጦርነት ታድጋል። አፋሕድ – ባዘጋጀው የ “አንድነት ጉባኤ ” ላይ የአፋብኃን ስም ጠርቶ በይፋ ጠርቶ በእንግድነት ጋብዛል፣ በድምጽና በደብዳቤም ይፋ አድርጋል። አፋሕድ ከሁለት ሳምንት በፊት ያዘጋጀውን የውይይት ፕሮግራም ለአፋብኃ ሲምፖዚየም ብሎ ፕሮግራሙን በይፋ ሰርዛል። ባለፈው ግንቦት ወር ቋራ ላይ አፋብኃ ሲመሰረት አፋሕድ የእንኳን ደስ ያላችሁን መግለጫ በይፋ በአደባባይ አውጥታል። የአብረን እንሰራን ጥያቄንም በወቅቱ በይፋ ጥሪ አቅርባል።
ይህ እንግዲህ የአፋሕድ – ስለ አማራ ፋኖ አንድነት ብሎ በተጨባጭ ሁኔታ በግልጽና በአደባባይ እየፈጸመ ያለው ገሀዳዊ ተግባር የድርጅቱን ለአንድነት ያለውን ጥማት፣ ቁርጠኝነት እና Committee የሆነ Commitment ያሳያል።
እናም ሁለቱ ድርጅቶች የጋራ ኮሚቴ አዋቅረው ንግግር ጀምረዋል። የሁለቱ ድርጅቶች ተወካይ ኮሚቴ አባላትም
፩ኛ- ከአፋሕድ በኩል
– አርበኛ ጌታ አስራደ – (ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ)
– አርበኛ ማስረሻ ሰጤ
– አርበኛ ኢያሱ ይመር- (ወሎ ጠቅላይ ግዛት እዝ)
-አርበኛ ምንተስኖት- – ( ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ )
፪ኛ- በአፋብኃ በኩል
– አርበኛ አስረስ አማረ
– አርበኛ አስቻለው -( ጎንደር )
– አርበኛ ብርክ – ( ሸዋ እዝ )
– አርበኛ – ሔኖክ ኪዳኔ ( ወሎ እዝ ) ናቸው።
እነዚህ የኮሚቴ አባላት Already ንግግር መጀመራቸው ብቻ ሳይሆን የማስማሚያ ስነድ እያዘጋጁ ስለመሆናቸው ከትናንትናው የጌታ አስራደ ቃለ መጠይቅ መረዳት ተችላል።
እንደ ጌታ አስራደ አገላለጽ –
ኮሚቴው –
– አዲስ የመግባቢያ ሰነድ
– አዲስ ቤት ( አዲስ ድርጅት)
– የአመራር ሽግሽግ. – ጉዳይ ላይ እየሰራንበት ነው በማለት ገልጻል። አብሮት የቀረበው ምንተስኖትም ይህን ሀሳብ የሚጋራ ተመጋጋቢ ሀሳብ አቅርባል።
ይህ እንግዲህ በአፋሕድ በኩል ያለውን ሁኔታ የሚያሳየን ነው።
እንደ ጌታ አስራደና ምንተስኖት አገላለጽ አፋሕድ ስለአማራ ፋኖ አንድነት ብሎ እራሱን – ማለትም ድርጅታዊ ህልውናውን አክስሞ፣ የድርጅቱንም አመራሮች አሸጋሽጎና ቀይ ሮም ቢሆን ከአፋብኃ ጋር እራሱን አቅልጦ በመዋሃድ አዲስ ድርጅት ለመፍጠር ዝግጁ መሆኑን ነው መርዳት የተቻለው። ይህንን የትናንቱን የጌታ አስራደንና የምንተስኖትን አጭር ቃለ ምልልስ የሰሙ አማራዊያን – በተለይም የአፋሕድ ጠንካራ፣ ቋሚ ደጋፊ አባላት አፋሕድ እንደ ቅቤ ቀልጦ እራሱን ሊያከስም ያሰበ ይመስላል እያሉ ስጋታቸውን ሲገልጹ ተሰምተዋል።
π የአፋሕድ እና የአፋብኃ ወደ አንድነት ጉዞ ያላቻ ጋብቻ አይነት አንድነት ነው ወይንስ አንዲት ሴት ልጅ በግድ ማግባት የፈለገቺውን ወንድ ልጅ በጠለፋ አፍና ትዳር ለመመስራት የመጣር ያህል ነው?
ከአሰር ቀን በፊት አራቱ የአፋሕድ አመራሮች ማለትም አርበኛ ደረጀ በላይ፣ አርበኛ ኮ/ል ፋንታሁን ሙሀባ፣ አርበኛ መከታው ማሞ እና አርበኛ ምንተስኖት ቀርበው ስለአንድነቱ ሲናገሩ – ከአርበኛ ምንተስኖት በስተቀር ሶስቱ ተመሳሳይ የሆነ አንድ ወሳኝ መልእክት አስተላልፈው ነበረ። ያም መልእክት አንድነት የሚገነባው በአንድ ወገን በኩል ብቻ በሚደረግ ጥረት ሳይሆን በሁለቱም ወገን እኩል አቻ ድርሻቸውን መወጣት የሚፈጠር ነው አንድነት በማለት ገልጸዋል። የትናንትናው የጌታ አስራደና የምንተስኖት አነጋገር ግን ይህንን የአንድነት መገንቢያ የሆነውን መሰረታዊ ንጥረ ነገር ወደ ጎን ያደረገና አፋሕድ ብቻ እራሱን አቅልጦ ስለአንድነት ለመፍረስ የወሰነ ያስመሰል አነጋገር በመሆኑ ብዙዎችን ግራ አጋብታል፣ ብዙዎችንም አስቆጥታል።
ወደ አፋብኃ ጉዳይ እንመለስ-
አፋብኃ ከዚህ በተቃራኒ እየተጋዘ ያለ ድርጅት ሆኖ ነው እያየን ያለነው።
በማስረጃ ለማሳየት ያህልም
– አፋብኃ የአፋሕድን ስም እየጠራ መግለጫ ሲያወጣም ሆነ ለአፋሕድ ይፋዊ መግለጫ ይፋዊ መልስ ሲሰጥ አልተሰማም
– አፋብኃ ላዘጋጀው ሲምፖዚያም ስኬት አፋሕድ ፕሮግራሙን መሰረዝ ገልጾ ምስጋና ሲገልጽ አልተሰማም
– በአፋብኃ ሲምፖዚየም ላይ አፋሕድ የሚባል ስም ፈጽሞ አልተጠቀሰም
-አፋብኃ – ከአፋሕድ ጋር ኮሚቴ ተዋቅሮ ስለ አንድነት እየተነጋገረ ከሁለት ወር በሃላ የአስር ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ ማሰባሰብን ሰራ ለብቻው ይፋ አድርጋል።
– አፋብኃ የአማራን ህዝብ የህልውናን ትግል ክዶ እጁን ለጠላት የሰጠውን አሰግድ መኮንንን ያየ የሚል ዘመቻ ከፍታል – ( በእርግጥ አፋሕድ ውስጥም ለከሀዲ ባንዳው ጸዳሉ ደሴ ጥብቅና የቆሙ አመራሮችን ማየታችን ይታወቃል)
– አፋሕድ – አመራሮቹን ወደ ሚዲያ እየላከ በአንድነት ዙሪያ Promising የሆነ መልእክት ሲያስተላልፍ አፋብኃ ግን አንድም ግዜ አመራሩን በአፋሕድ እና በአፋብኃ መካከል ስለሚፈጠረው አንድነት እንዲያብራሩ ሲያደርግ ፈጽሞ አልተሰማም።
ከአርበኛ ዘመነ ካሴ የአንድ ገጽ ጥሪ በስተቀር አፋብኃ ልክ እንደ አቻው አፋሕድ ስለ አማራ ፋኖ አንድነት የአፋሕድን ስም እየጠቀሰ ማብራሪያ ሲሰጥ አልታየም።
ይህንን የሁለቱን ድርጅቶች የአንድነት ጥሪንና ፍላጎትን የተመለከተ የአፋሕድ አባል ደጋፊ – የሚደግፈውን ድርጅት በሴት ጾታ በመምሰል – በሀገራችን ያላቻ ጋብቻ አለ፣ ያለ ፍላጎት የአስግድዶ ጠለፋ አለ፣ ዛሬ ግን በአፋሕድ በኩል እየሰማን ያለነው አንዲት ሴት አንድን ወንድ አስገድዳ ጠልፋ በግድ ባል ለማድረግ ስትጥር የማየት ያህል ነው በማለት ሲናገሩ ተሰምታል።
The building blocks of Unity is -Equilty & Equal Contribution
የእውነተኛ አንድነት መሰረት መገንቢያ ጡቦች – አቻነት፣ እኩልነት እና አቻ እኩል አስተዋጾ አድራጊነት ነው እውነተኛውን አንድነት የሚፈጥረው። ያላቻ ጋብቻ ትዳር ሳይሆን ደባልነት ነው፣ አስገድዶ መጥለፍም ትዳር ሳይሆን አስገድዶ መድፈር ነው። የአንድ ወገን የአንድነት ጥማት በራሱ አንድነትን አይፈጥርም። ገዢና ተገዢን ፣ ጌታና ሎሌን ካልፈጠረ በስተቀር የአንድ ወገን ለአንድነት መቃተት ፈጽሞ አንድነትን እውን አያደርግም።
በአፋብኃ በኩል እስካሁን ለአፋሕድ ይፋዊ ጥሪና ይፋዊ የአንድነት ስራ የሚመጥን አቻ አጸፌታ ሲሰጥ ፈጽሞ አላየንም። የነገውን ዛሬ ላይ ሆነን መግለጽ ባይቻለንም ዛሬ ላይ ሆነን ትናንት እና ዛሬ እየሆነ ያለውን ስንመለከት በሁለቱ መካከል ያለው ወደ አንድነት ጉዞ ፈጽሞ አቻና ተመጣጣኝ አይደለም።
π የአፋሕድ የአንድነት መሻት እና የአፋብኃ የ 10,000,000 $ ( አስር ሚሊዮን ዶላር)ፕሮጄክት
አፋሕድ እዚህጋ ስለአንድነት ይጮሀል፣ አፋብኃ ደግሞ ስለተናጥላዊ ሚሊየነርነት በእነ ኤልያስ ክፍሌ፣ ግርማ ካሳና መሰል ሼር ሆልደሮች በኩል የአስር ሚሊዮን ዶላር ፕሮጄክት ነድፎ ሲንቀሳቀስ ይሰማል።
የ 10 ሚሊዮን ዶላሮች ፕሮጄክት ሀሳብ ባለቤት የመረጃው ቲቪ ኤሊያስ ክፍሌ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ግለሰቡ በየስቴቱ ላሉት የአማራ ማህበራት እና አመራሮች እየደወለ ስለ አስር ሚሊዮን ዶላር ቴሌቶን ዝግጅት የመመልመል ስራን እየሰራ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ በገፍ ደርሶኛል። ግለሰቡ ግን – ማለቴ ኤሊያስ ክፍሌ ጠይቄው ( በአሜሪካን ፍርድ ቤት የከሰሰኝን ባላንጣዬን ማለቴ ነው) የሰጠኝ መልስ ውሸት ነው የለሁበትም የሚል ነው። ሆኖም እራሱ ኤሊያስ ክፍሌ እየደወለላቸው በዚህ ቴሌቶን ላይ እንዲሳተፉ የጠየቃቸው ሰዎች መረጃ የኤሊያስ ክፍሌን ክህደት ሀሰተ መሆኑ የሚያረጋግጡ በመሆናቸው የአስር ሚሊዮኑ ዶላር ፕሮጄክት ሀሳብ የኤሊያስ ክፍሌ መሆኑን መረዳት ችያለሁ። በሰሩ እነ ግርማ ካሳን ጨምሮ አፋጎ ወደ አፋብኃ ከመቀላቀሉ በፊት የነበሩትን የአፋብኃ አክትቪስቶችን ያቀፈ ኮሚቴን አካታል። ምንም እንካን የአፋጎ ጠንካራ ደጋፊዎች ፕሮጄክቱን ያልታቀፍንበት ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ ሊካሄድ አይገባም እያሉ ቢቃወሙም – የአፋጎ ከፍተኛ አመራሮች ይሁንታ እና እውቅና በኤሊያስ ክፍሌ ሀሳብ አመንጪነት አፋብኃ ብቻውን በተናጥል ከሁለት ወር በሃላ አስር ሚሊዮን ዶላር እቅድና ፕሮጄክት ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ነው።
ለዚህ ጸሀፊ የአስር ሚሊዮን ዶላር Fundraising Project ለአማራ ፋኖ አንድነት ታላቅ ተግዳሮት እና መረገምት ሆኖ ቁልጭ ብሎ የሚታየው።
ምክንያቱም
፩ኛ- አስሩ ሚሊዮን ዶላር የሚሰበሰበው ከሁለት ወር በሃላ ነው ( ቢሳካም ባይሳካም)
፪ኛ- የገንዘቡ አሰባሳቢ አፋብኃ ብቻ እና ብቻ ነው
፫ኛ- የገንዘቡ አሰባሳቢ እነ ኤልያስ ክፍሌ፣ግርማ ካሳ – በተለይ በተለይ ግርማ ካሳ ፈጽሞ የአማራን ፋኖ አንድነት የማይሹ – በግድም ይሁን በውድ የአማራ ፋኖ አንድነት መፈጠር ካለበት እንደፈለጉ ሊሾፍሩት የሚችሉትን ደካማ አመራር ያለውና በእነርሱ Term & Conditions የሚፈጠር አንድነትን ለመፍጠር የሚጥሩ ግለሰቦች የመሆናቸው ጉዳይ ይህ የአስር ሚሊዮን ዶላር ፕሮጄክት የአማራን ፋኖ አንድነት ለመፍጠር ከማገልገል ይልቅ የልዩነት እና የማራራቂያ ግብአት ሆኖ የሚያገለግልበት ሁኔታ በእጅጉ የጎላ ሆኖ ነው እያየን ያለነው።
ታዲያ የአማራ ፋኖ አንድነት በዚህ አይነት አካሄድ እውን የሚሆን ነውን?.., የሚለውን ጥያቄ ምላሽ በቀጣይ የምመለስበት ወሳኝ ጥያቄ ይሆናል።
አበቃሁ።