በአህያ ቆዳ የተሰራ ቤት ጅብ ሲጮህ ይፈራርሳል!
ከሞገድ እጅጉ
‹‹የአማራ ሕዝብ ጠላት ሆዳም አማራ ነው›› የሚለው የፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ንግግር በብዙዎች ዘንድ ይታወቃል፡፡ ምን ዋጋ አለው! ተግባራዊ የሚያደርገው ግን የለም፡፡ ይሄ ሁሉ የአማራና ምሁር እና ፖለቲከኛ ሀቁን ቢያውቀውም ተግባራዊ ማድረግ ግን አልቻለም፡፡
ሀቁን እንቀበል ከተባለ፤ በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ይሄ ሁሉ ስቃይና መከራ በአብይ አህመድ ጥንካሬ አይደለም፤ ይልቁንም በአማራ ምሁራን እና ፖለቲከኞች ደካማነት ነው፡፡ የአብይ አህመድ ጭካኔ፣ ኢሰብዓዊነትና አረመኔነት ተፈጻሚ የሆነው በብአዴን አስፈፃሚነት እና ተቃዋሚ ነን በሚሉ የአማራ ኃይሎች በፍጥነት አለመደራጀት ነው፡፡
ከዚህ በኋላ ብአዴንንም ሆነ ኦህዴድን መውቀስ ጅልነት ነው፡፡ ኦህዴድ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ የዘለቀውን ዕቅዱን እያሳካ ነው፡፡ ብአዴንም ተላላኪነትና ሆዳምነት ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ የኖረበት መሰረታዊ ባህሪው ሆኗል፡፡ አሁን ችግሩ ያለው በተቃዋሚ የአማራ ፖለቲከኞች ዘንድ ነው፡፡
እየሆነ ያለው ነገር ፋታ የሚሰጥ አይደለም፡፡ አብይ የአማራ ሕዝብ ችግርንና ስቃይን እንድላመድ ተደርጓል፡፡ የአማራ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የአዲስ አበባም ሆነ ሌላው ለጊዜው ጦርነት የሌለበት አካባቢ ያለው ሕዝብ ችግርን እንድላመድ ተደርጓል፡፡ ለምን የሚለውን ልብ ብለን እንመልከት፡፡ ይህን ሀቅ አለመቀበል ደግሞ ዋጋ ያስከፍላል፡፡
በአማራ ሕዝብ ላይ የተቃጣውን የኦህዴድ ወረራ ለመመከት የፋኖ እንቅስቃሴ ሲጀመር በአዲስ አበባ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ነበር፡፡ እንደ ታላቁ ሩጫ ባሉ ሕዝባዊ ትዕይንቶች ላይ ‹‹እየመጡ ነው…›› በሚል ለፋኖ ድጋፍ ይደረግ ነበር፡፡ አማራ ክልል ውስጥ የሚፈፀም ጥቃት በማህበራዊ ገጾች መነጋገሪያ ይሆን ነበር፡፡
አሁንስ?
አሁን ተለምዷል፡፡ ሁሉም እየኖረ ያለው የዕለት የዕለቱን ነው፡፡ ሁሉም እየኖረ ያልው የፊት የፍቱን ነው። በድሮን ብዙ ሕዝብ ተጨፍጭፎ ምንም ስሜት የማይሰጥበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በአማራ ክልል ውስጥ ካህን ቀደም በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተጨፍጭፈው አድረው፤ብዙዎች ግን ኢኳቶሪያል ጊኒ ውስጥ ከትዳሩ ውጭ የወሰለተ ሰው ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ነበር፡፡
በዚህ ሳምንት በወለጋ ሆሮ ጉድሩ ንጹሀን አማሮች ሲጨፈጨፉ አደሩ ማንም ቦታ የሰጠው የለም።አብይ አህመድ እና ዳንኤል ክብረት በ7አመት 30% ብቻ የሰሩትን ለግብጽ የተሽጥ ግድብ ይዘው ብቅ አሉ።አብዛኛው የአማራ ማህበራዊ ሚዲያ አክቲቪት ነን ባይ “”የሚወሩት ስንፈተ ወሲብን እንዲት መከለከል ይቻለል የሚል ሆነ”
ሰዎች ትልልቅ ነገሮችን ትተው ትንንሽ ነገሮች ላይ ብቻ እያተኮሩ የዕለት የዕለቱን ብቻ እንዲኖሩ አድርጓል፡፡
ይህ አጋጣሚ የተፈጠረበት ምክንያት በተቃዋሚ ፖለቲከኞች ላይ ያለው ተስፋ ስለተቀዛቀዘ ነው፡፡ ከአገዛዙ የተሻለ አርቆ አስተዋይነት የሌላቸው ሆነዋል ብሎ ተስፋ ከመቁረጥ ነው፡፡
ደፈር ብለን እውነቱን እንናገር ከተባለ፤ የፋኖ ትግል በፍጥነት ወደ ውጤት እንዳይመጣ ያደረገው ፖለቲከኛውና የአማራ ምሁር የሚባለው ነው፡፡
ልብ መባል ያለበት ነገር በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ጥይት በመተኮስ ብቻ መንበረ መንግሥትን መቆጣጠር አይቻልም፡፡ የኮምኒኬሽን ትግል ያስፈልጋል፡፡ የአማራ ምሁራን እና ፖለቲከኞች የኮምኒኬሽን ትግል ደግሞ ደካማ ነው ብቻ ሳይሆን የሞተ ነው ማለት ይቻላል፡፡ አርቆ አስተዋይነትና ብልህነት የለውም፡፡ ዕለታዊ ስሜት የተጫነው ነው፡፡
ወዲህ ደግሞ እጅግ አደገኛ የሆነ ጎጠኝነት አለበት፡፡ አገዛዙን ከመታገል በላይ እርስ በእርሳቸው የሚታገሉት ይበልጣል፡፡ ይህ ደግሞ የሚጠቅመው አገዛዙን ነው፡፡ ይህን እንኳን አርቆ አለማስተዋል የአማራ ሕዝብ ጠላትነት ነው፡፡
ወቅታዊ ብሽሽቅ እና እልህ ከጀግና አይጠበቅም፡፡ ጀግና ማለት የራሱን የግል ክብር ሳይሆን የሕዝቡን ክብር የሚያስቀድም ሲሆን ነው፡፡ አንድ ሰው ጀግና ነኝ ካለ፤ ራሱ ተዋርዶም ቢሆን የሕዝቡን ዘላቂ ክብር ያስጠብቃል፡፡
መሬት ላይ የሚታየው ነገር ግን ‹‹እኔ ተናግሬ ነበር›› ለማለት እንዲያመቻቸው እነርሱ ያሉት እንዲሆን የትኛውንም ነገር የሚያደርጉ ናቸው፡፡ የእነርሱ ትንቢት ይሰምር ዘንድ ሕዝብን አደጋ ላይ የሚጥል ነገር የሚያደርጉ ናቸው፡፡
የአማራ ሕዝብ በየዕለቱ እየተጨፈጨፈ፤ የማይመለከታቸውን የግለሰብ ጉዳይ ያነሳሉ፡፡ የዘር ጭፍጨፋውን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳወቅና ለሚጨፈጨፈው ሕዝብ ድምጽ መሆን ሲገባቸው፤ ከወቅታዊ ጉዳይ ጋር የማይገናኝ ያረጀ ያፈጀ የግለሰብ ጉዳይ አንስተው ይጨቃጨቃሉ፡፡
ታዲያ እነዚህ ምሁራን እና ፖለቲከኞች ከገዳዩ የአብይ አህመድ አገዛዝ በምን ይለያሉ? በአንድ ፊቱኑ የለየለት ጠላት አይሻልም ወይ?
እነዚህ ሆዳም እና አርቆ ማሰብ የተሳናቸው የአማራ ፖለቲከኞችና ምሁራን የአብይ አህመድ አገዛዝ ዕድሜ እንድኖረው አድርገዋል፡፡ እሳት የሚተፋውን የፋኖ ትግል ውሃ ቸልሰውበታል፡፡ በቀን በሺዎች የሚቆጠር ወታደር የሚመረክበትን የአብይ አህመድ አገዛዝ ዕድል ሰጥተውታል፡፡ የአብይ አህመድ አገዛዝ ይህን ያህል የተዳከመው በፋኖ የመሬት ላይ የትጥቅ ውጊያ ብቻ ነው፡፡ በፕሮፖጋንዳ አንዲት ፐርሰንት አልታገዘም ማለት ይችላል፤ እንዲያውም መሰናክል ነው የሆኑበት፤ ቢያንስ ቢያንስ አርፈው ቢቀመጡ ይሻል ነበር፡፡
የአብይ አህመድ አገዛዝ ወታደር አልቆበታል፡፡ የአገሪቱን ድንበር ባዶ አድርጎ ወደ አማራ ክልል ያሰማራው ሠራዊት ሁሉ ተማርኮበት አሁን ከየመስሪያ ቤቱ በግዳጅ መመልመል ጀምሯል፡፡ በቅርቡ በወጣ ዘገባ እንዳየነው፤ ከአዳማና አዲስ አበባ ወጣቶች በብዛት እየታፈሱ ነው፡፡
አብይ አህመድን ለዚህ ሁሉ መዳከም ያበቃው የፋኖ የትጥቅ ትግል ብቻውን ነው፡፡ በሰለጠነ ኮምኒኬሽን እና ፕሮፖጋንዳ ቢታገዝ ኖሮ ይህን ጊዜ የአማራም ሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብይ አህመድን ተገላግሎት ነበር!
አሁን በዚህ ሳምንት እንኳ ሁለት የካቢኔ ሚንስትሮች ከስራ ተብረዋል ለገሰ ቱሉ እና ማሞ ምርቱ ይህ የሚያሳየው የመንግስትን ድክመት እንጂ ጥንካሬ አይደለም።
እናም
መደምደሚያ፦
“ይህ እርስ በእርሱ የሚጠላለፍ የአማራ ምሁርና ፖለቲከኛ ሁሉ የአብይ አህመድ አገዛዝ እንዲቀጥል የሚያደርግ የአማራ ሕዝብ ጠላት ነውና አንድ ሊባል ይገባል!”