ወደ ወገን መተኮስ ወደ ነጻነት ሳይሆን ወደ ባርነት፣ ወደ ድል ሳይሆን ወደ ገደል ይመራናል።
ከአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ
ከሁሉ አስቀድመን ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮችና ለሁሉም ኢትዮጵያውያኖች እንኳን ለደመራና ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዓሉ የሰላም የፍቅር የ አንድነት የድል እንዲሆንልን እንመኛለን።
የአማራ ፋኖ ትግል የተጀመረው በ አማራ ህዝብ ላይ የተጋረጠውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ተጽፎ ተግባር ላይ እየዋለ ያለውን ጸረ አማራ ትርክት ለመቀየር ጨፍጫፊና ሃገር አፍራሽ የሆነውን ስርዓት አስወግዶ የ አማራን ነጻነትና የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት አጽንቶ ሕዝባችንን ማህበራዊ እረፍት እንዲያገኝ ለማድረግ መሆኑ ግልጽ ነው።
ነገር ግን እራሱን አፍብኃ ስሜን ቀጠና በላይ ዕዝ እያለ የሚጠራው ቡድን በ አማራ ፋኖ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት በማድረስ በትግሉ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ በመፍጠር ላይ ይገኛል። ትላንት የትግላችን አይተኬ ጀግኖች ያሳጣን ይህ ቡድን ከስ ህተቱ ይማራል፣ የመከራል፣ ይፀፀታል ብለን ብቻ ሳይሆን ለታላቁ ዓላማችን ስንል፣ እነሱ ለጠብ ሲጠሩን እኛ ለፍቅር ስንጠራቸው መቆየታችን ህዝብና ስራዊታችን ህያው ምስክር ነው።
በአሁኑ ወቅት በተለይም
⇒ መላ የ አማራ ፋኖን አንድ ለማድረግ የ አፋሕድና የ አፋብኃ የ አንድነት አመቻች ኮሚቴ አቋቁመን ስራ በጀመርንበት
⇒ በርካታ ሽማግሌዎች ከ የ አቅጣጫው አንድነቱን ለማምጣት ሌት ተቀን በሚደክሙበት
⇒ በምስራቁ በኩል ያሉ ፋኖ ወንድሞቻችን በትብ ብር አስደማሚ ጅብድ እየሰሩ ባሉበት ሰዓት
⇒ ሕዝባችንና ሰራዊታችን የታላቁን የመስቀል በዓል በሚያከብርበት በዚህ ወቅት
ከጀርባ የጠላትን ዓላማ አዝሎ ከፊት ያለ ጠላትን አላማ በሚያሳካ መልኩ ወገንን እርስ በእርስ ለማጫረስ በተለያየ ቦታዎች ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተው የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች ወዳሉበት ቀጠና ሰርጎ በመግባት በ አምስት አቅጣጫ አማራንም ሆነ ጎንደርን አንገት በሚያስደፋና በሚያሳፍር ደረጃ ጦርነት የከፈቱ መሆናቸውን ህዝባችንና ሰራዊታችን እንዲያውቅልን እንፈልጋለን።
ራስ አርበኛ ደረጀ በላይ
የአማራ ፋኖ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ዋና አዛዥ