>
4:53 pm - Wednesday May 25, 1881

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለምንድን ነው የእራሱን ጥላ አይቶ የሚደነብረው?[ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም - ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ ]

 እ.ኤ.አ በ2015 ለምንድን ነው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የፍርኃት፣ የአጠቃላይ በፍርሀት የመርበድበድ እና እጅግ በጣም በጭንቀት ውስጥ የመግባት አምላኮች የእራሳቸውን ጥላ የሚፈሩት?

እ.ኤ.አ ግንቦት 24/2015 በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች የቅርጫ ምርጫ ለማካሄድ በዕቅድ ተይዟል፡፡ የቅርጫ ምርጫው ምንም እንኳ በሸፍጥ የታጀበ እና የተጀቦነ ቢሆንም፡፡

ከአምስት ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ ግንቦት 23/2010 እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው ወሮበላ አገዛዝ የፓርላሜንታዊ መቀመጫውን በ99.6 በሆነ ውጤት አሸነፈ፡፡ ይኸ የምርጫ ውጤት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን እ.ኤ.አ በ2002 ሳዳም ሁሴን ካስመዘገበው 100 በመቶ በትንሽ በማነስ የሁለተኛነት ደረጃን እንዲጎናጸፍ አድርጎታል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እ.ኤ.አ ግንቦት 24/2015 በሚካሄደው የይስሙላ ምርጫ ቢያንስ በ99.6 በመቶ ድል ይቀዳጅ ይሆን? ጠቃጠቆ ያለባቸው ጅቦች በእርግጠኝነት ጠቃጠቆው አለባቸውን?

ሆኖም ግን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በፍርሀት ተውጦ በላብ ተዘፍቆ እንደሚገኝ  የውስጥ ምንጮች ነግረውኛል፡፡ እስከ ቅርጫ ምርጫው ድረስ በፍርሀት ርዷልን?

ምርጫ! የምን ምርጫ? የዘረፋ ወሮበላ ምርጫ!?

ሽንፈትን መፍራት ምክንያታዊ ነው፣ ሆኖም ግን በ99.6 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ በሆነ ውጤት ማሸነፍን መፍራት ፍጹም የሆነ እብደት ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በእርግጠኝነት በፍርሀት ቆፈን ውስጥ የተወሸቀ መሆኑን የውስጥ ምንጮች ነግረውኛል፡፡

በሚያስገርም ሁኔታ እነዚህ ሰዎች የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አባላት እና ጽኑ ደጋፊዎች እና ተከታዮች ናቸው፡፡ ስለዚህም እውነት ነው ብለው ያምናሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች በእርግጠኝነት አባላት ለመሆን እና አለመሆናቸው የማረጋግጥበት ምንም ዓይነት ማስረጃ የለኝም፡፡ አንዳንዶቹ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ታዛዥ ሎሌዎች እና የቡድን አባላት ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ነጻ በሆነ መልኩ ለንግድ ስራ ሲባል ከአዲስ አበባ በመሄድ እና እንደገና በመመለስ በፍርሀት ተይዘው ይገኛሉ፡፡ በእርግጠኝነት በአሁኑ ጊዜ በፍርሀት ወጥመመድ ተሸብበው እንደሚገኙ አረጋግጠውልኛል፡፡

እነዚህ ሰዎች ለእኔ መጥፎ ምክር ለመስጠት በማሰብ ከመስመራቸው ውጭ ለመንቀሳቀስ ይችላሉን?

ለምንድን ነው እነዚህ ሰዎች በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጎራ ውስጥ ስላለው ፍርሀት እና ጥላቻ ሚስጥራዊነት ዝርዝር እና ጥልቅ በሆነ መልኩ የሚነግሩኝ? ምናልባትም የተሳሳተ መረጃ እየሰጡኝ ይሆናል በማለት ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ሆኖም ግን የእነርሱን የቅጥፈት መረጃ ለመጠቀም የተሰላቸሁ መሆኔን ያውቃሉ ብዬ እገምታለሁ፡፡ ታዲያ ይህ ከሆነ ለምንድን ነው ሚስጥራቸውን እያመጡ ለእኔ የሚዘከዝኩት? እውነት ለመናገር እኔ ስለዚህ ጉዳይ የማውቀው ነገር የለኝም፣ እንዲሁም ለማወቅ ደንታ የለኝም፡፡

ሆኖም ግን አንድን ነገር ለማወቅ ከፍተኛ የሆነ ጉጉት ያለኝ ሰው ነኝ፡፡ በሕጉ ዓለም ሁልጊዜ እንደምንለው ሁሉ በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት መረጃ ለመስጠት ምቾት ሊሰማቸው ይገባል፡፡ ሁሉንም ነገር ይፋ እንደማወጣው ያውቃሉ፡፡ በስልጣን እርካብ ላይ ተፈናጥጠው ለሚገኙት ጉልበተኞች ሁሉ እውነትን እናገራለሁ የሚል ሰው እውነትን በመደበቅ ሌላ ነገር የሚናገርበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ እነርሱ ደንታ ያላቸው አይመስለኝም፡፡ ምንም ዓይነት ስም መስጠት አያስፈልግም፣ እባካችሁ እውነታውን ብቻ መናገር ነው፡፡

የሚመላለሰው ሀሳብ ጭንቅላቴን በጠበጠው፡፡ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት የተጠናወታቸው ሊመስል ይችላልን? አንዳንድ ጊዜ በከፍተኛ የስልጣን ቦታ ላይ ያሉት እና ኃይለኛ ጉልበታሞች ፍጹም የሆነ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውሰጥ ጸጥ ብለው ከሚኖሩት እና አሰልቺ በሆነ መልኩ እያቃሰቱ እንዲሁም እየተወራጩ በችግር ከሚኖሩት ኃይል እና ተስፋ የለሽ ሰዎች የበለጠ መብረቃዊ ነው፡፡

ማቋረጫ የሌለው የተስፋ መቁረጥ ስሜት እንዳለ እየነገሩኝ ነው – ማለትም የደስታ ስሜት መራቅ፣ አሳሳቢ ጭንቀት፣ የሰላም ማጣት እና ትርምስ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራር ብቻ ሳይሆን በተራው አባላት ላይም ተንሰራፍቶ ይገኛል፡፡

እኔ ይህ ሁኔታ ለምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ ኃይለኛው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በማጎሪያው እስር ቤት እና በህሊና አስሮ እንደፈለገው እየፈነጨ ባለበት ሁኔታ በእራሱ ላይ እንደዚህ ያለ የተስፋ መቁረጥ ስሜት የሚታይበት ለምንድን ነው?

በእንደዚህ ያለ ሁኔታ ያሉት እነርሱ ብቻ አይደሉም፡፡ ሌሎችም አሉ፣ ማለትም ጽንፈኞቹ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አባላት፣ ተቃሚዎች እና ትችት አቅራቢዎች ጭምር ይካተታሉ፡፡ እንዲህ የሚል አንድ ዓይነት ነገር ነው የነገሩኝ፡፡ “በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በፍርሀት ማዕበል ውስጥ ተውጦ ይገኛል፡፡ በዓለም ላይ እየተካሄደ ያለው ምንድን ነው ?

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በአሁኑ ጊዜ የሀሰት መረጃ የማሰራጨት ዘመቻ እና መጠነ ሰፊ የሆነ የማታለል ስራ እየሰራ ነው ያለን? እኔ ይኸ ነገር የሚገርመኝ ጉዳይ ነው፡፡ ምናልባትም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እንዲህ የሚለውን የሰን ትዙን ስልታዊ ጨዋታ እየተጫወተ ሊሆን ይችላል፣ “ጠንካራ በሆንክበት ጊዜ ደካማ መስለህ ለመታዬት ሞክር፣ ሆኖም ግን ደካማ በሆንክ ጊዜ ግን ጠንካራ መስለህ ለመታዬት ሞክር፡፡“ ከፍተኛ የሆነ ኃይል ባለህ ጊዜ ለጠላቶችህ የፈራህ በመምሰል ለማሳየት ሞክር፡፡

በአጠቃላይ ሁሉም ነገር ሲታይ ሁከት የመፍጠር ነገር ይመስላል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን ደጋፊዎች እና ጠላቶች በተደጋጋሚ የሚናገሩትን አንድ ዓይነት ነገር ማዳመጥ የወያኔ አመራሮች እና ተራው አባላት በእራሳቸው ላይ ያላቸው እምነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሸረሸረ የመጣ ለመሆኑ የጸሐይ ግርዶሽን የመመልከት ያህል ነው፡፡ሁልጊዜ ሊፈጸም የማይችል ጉዳይ ነው፡፡

ይኸ ጉዳይ አልፎ አልፎ ሊሆን የሚችል ነገር ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች የፈሩ መሆናቸውን ነግረውኛል፡፡ እኔ የማቀርበው ጥያቄ እንዲህ የሚል ነው፣ “እነዚህ ፍጡሮች ምንድን ነው የሚፈሩት?“ ለዚህ ጥያቄ ቀጥተኛ እና ቀላል የሆነ መልስ የለውም፡፡

ሰውን ምቾት እንዳይሰማው ማድረግ፣

ኃይለኛው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በእብሪት በመወጠር በባለእንጨቱ ዙፋን (ባለወርቁን ዙፋን ቀደም ሲል ሸጠውታል) ላይ ተቀምጦ ይገኛል፡፡ ኃይለኛው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከ5 ሚሊዮን በላይ አባላት አሉት፡፡ አሁን በህይወት የሌለው እና የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ትንሹ አምላክ የነበረው መለስ ዜናዊ ከአምስት ዓመታት በፊት ነበር ይህንን የተናገረው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይህንን ቁጥር እጥፍ ወይም ደግሞ ሶስት ጊዜ እንዲያድግ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ገንዘብ ፍቅርን አይገዛም ሆኖም ግን ያለምንም ጥርጥር ድምጽ ሰጭን እና የፓርቲ አባላትን ሊገዛ ይችላል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የምጣኔ ሀብቱን የደም ስር አንቆ ይዟል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቢሮክራሲውን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የፖሊስ፣ የደህንነት እና ወታደራዊ ኃይሉን በበላይነት ተቆጣጥሯል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በቆሸሸው እጁ የሚበላባት ሜሪካ አለችው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ በማደግ ላያ ያለ የዴሞክራሲ ባለቤት ናት በማለት የሚያውጅላት የዩኤስ አሜሪካ 4ኛ ከፍተኛ የውጭ ጉዳይ ባለስልጣን አግኝቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ምንም ዓይነት ክብር የለም!  እነዚህን በጣም የተማሩ እና ሰፊ ልምድ ያካበቱትን ታላላቅ የዲፕሎማሲ ሰዎች ድድብናን በተላበሰ መልኩ በአደባባይ በህዝብ ፊት እንዲናገሩ በማድረግ እንዴት አድርገው እንደ ዕቃ እንደሚጫወቱባቸው አውቃለሁ፡፡ በዩኤስ መንግስት አራተኛ የውጭ ጉዳይ ዲፕሎማት ባለስልጣን የሆኑት ኢቨሊን ሸርማን ኢትዮጵያ ምርጫ ለማካሄድ እየጎለበተ ያለ ዴሞክራሲ አላት በማለት ተናግረው ነበር፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ተቃዋሚዎቻቸውን እና ተራውን ዜጋ ለማስፈራራት፣ በቁጥጥር ስር ለማዋል፣ በእስር ቤት ለማጎር እና ለመግደል የወታደር እና የፖሊስ ጡንቻውን ይጠቀማል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለሩብ ምዕተ ዓመታት በዘረፈው አንጡራ የህዝብ ሀብት ሌሎችን ለመሳብ ይጠቀምበታል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በአሁኑ ጊዜ ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ ነው፡፡

ሆኖም ግን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በእርግጠኝነት በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ነውን የሚለው አልገባኝም፡፡

በፍርሀት ላይ ናቸው ሲባል ምን ማለት ነው? የአዕምሮ ሰላም የላቸውም ማለት ነውን? የፍጻሜው ቀን ደርሷል በማለት ሌሊት እንቅልፋቸውን አጥተው ያድራሉ ለማለት ነውን? በጠራራው ጸሐይ በእንቅልፍ ውስጥ ሆነው በቅዠት የእንቅልፍ ላይ የእግር ጉዞ እያደረጉ ነው ለማለት ታሰቦ ነውን?

ሁሉንም የሚያንጸባርቁትን ህንጻዎቻቸውን እንደሚያጡ እያቃዣቸው ያለውን ቅዠት ለእኔ ነግረውኛል፡፡ ጊዜው ሲደርስ እና ጽዋው ሲሞላ ወዴት እንደሚገቡ እና የት ሄደው እንደሚያመልጡ በቀን ቅዠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ህዝባዊ ማዕበል ሊነሳብን ነው በማለት በቀን ቅዠት ውስጥ ሆነው በመዋለል ላይ ይገኛሉ፡፡ የመንገድ ላይ ነውጦች ወደ ህዝባዊ አመጽ፣ አብዮት፣ ጸረ መንግስት አልገዛም ባይነት እና ወደ ሁለገብ አመጽ ይሸጋገራል በማለት የቀን ላይ ቅዥትን በማራመድ ላይ ናቸው፡፡

ወታደሩ ትዕዛዝ ለመቀበል ፈቃደኛ ላይሆን ይችላል በማለት የመጨረሻውን የትዕዛዝ እርምጃ ላይወስድ ይችላል በማለት በቅዠት ዓለም ውስጥ ናቸው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከቡርኪና ፋሶ ከናይጀር እና ከቡሩንዲ ተግባራዊ ትምህርት ቀስመዋል የሚል ጥርጣሬ አለኝ፡፡ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት እንዲደረግ ብልሆች ናቸው፡፡

ለበርካታ ዓመታት ያህል በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎችን በማጎሪያ እስር ቤቶቻቸው አስረው ለበርካታ ጊዜ ለመቆየት በማሰብ በቅዠት ላብ ተጠምቀው ባነው ይነሳሉ፡፡

እኔ ይህንን ነገር አላምንም፡፡ ሆኖም ግን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ተዘፍቆ ይገኛል ማለት ማጋነን አይደለም፡፡ ከሁሉም በላይ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኢትዮጵያ ውስጥ የፍርሀት ግዛት መስርቶ ይገኛል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ትንሹ አምላክ እና አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ተወሽቆ ይኖር ነበር፡፡ የእርሱ የቅንጦት መኪና በከተማ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ እርሱ የሚሄድባቸው መንገዶች ለበርካታ ጊዚያት ዝግ ይደረጉ ነበር፡፡ የእርሱ ደቀመዝሙሮች በነጻ በህዝብ ፊት በአደባባይ መውጣት እና ፊታቸውን ማሳየት ፍርሀታቸው ይገድባቸዋል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ መፈራትን ይወዳሉ፡፡ ፍርሀትን መንዛት እና ፕሮፓጋንዳ ማሰራጨትን ስራዬ ብለው ተያይዘውታል፡፡ በፍርሀት የተቀነበበች ሀገርን ፈጥረዋል፡፡ በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ተወሽቆ የሚኖር አገዛዝን መስርተዋል፡፡ በፍርሀት ባህል ውስጥ በመኖር ላይ ናቸው፡፡ ፍርሀትን ያስባሉ፣ ፍርሀትን ይተነፍሳሉ፣ ፍርሀትን ያልማሉ፣ ፍርሀትን ያራምዳሉ፣ በፍርሀት ይኖራሉ፡፡ የፍርሀት ጌቶች እንዴት ነው ፍርሀትን የሚፈሩት? ሆኖም ግን ወያኔዎቹ በአሁኑ ጊዜ እራሳቸውን በፍርሀት ታስረው አገኙት፡፡

የፍርሀት አራማጆች በአሁኑ ጊዜ እራሳቸው ቦቅቧቃ ፈሪዎች ሆነው ተገኙ፡፡ እኔ የምፈራው ፍርሀትን እራሱን ነው የሚለውን አባባል አልተገነዘቡትምን? ስለሆነም ይፈራሉ፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የፍርሀት አፈታሪክ እኔን በጣም ይገርመኛል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ፎቦስ እና ዲሞስ የተባሉት የግሪክ የፍርሀት የሰቆቃ፣ የሽብር እና ሁሉም የሰይጣናዊ ድርጊት ተምሳሌቶች እራሳቸው በፍርሀት፣በሽብር፣ በስቃይ እና በግፍ ተጠርንፈው ይገኛሉ፡፡ የፍርሀት ጌታ በዲሞን ፍርሀት እንዴት ተግባራዊ ሊሆን ይችላል?

ታላቅ ክብር ያላቸው እና የተቀደሱ ሰው በአንድ ወቅት እንዲህ በማለት ጽፈው ነበር፣ “መፈራትን የሚወዱ ሰዎች መወደድን ይፈራሉ፣ እናም ከማንም በላይ እራሳቸው የበለጠ ይፈራሉ፣ ሌሎች ሰዎች እነርሱን ብቻ የሚፈሯቸው ቢሆንም እነርሱ ግን እያንዳንዱን ሰው ይፈራሉ፡፡“

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በእነርሱ ላይ እያንዣበበ ያለውን የኢትዮጵያን ህዝብ ቁጣ በመፍራታቸው ምክንያት ይፈራሉን?

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን የመፍራት ትረካ ሰምቻለሁ፡፡ ከተለመደው ውጭ ትኩረት በመስጠት ለማዳመጥ ሞክሪያለሁ፡፡ ይኸ ሁኔታ እንዲህ የሚለውን የቆዬ አባባል አስታወሰኝ፣ “የሚያውቁ ሰዎች አይናገሩም፣ የሚናገሩ ሰዎች ግን አያውቁም፡፡“

ስለሆነም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን የፍርሀት ታሪክ የሚታወቅ ቀላል ጥያቄ እና የሚታወቅ እና የማይታወቅ መሆኑን ለእራሴ ግልጽ አደረግሁ፡፡ ይህም ማለት የሚታወቅ እና የማይታወቅ ፍርሀት ነው፡፡ በእርግጥም ይህ ጉዳይ ከዚያም የበለጠ ውስብስብ ነገር ነው፡፡

የዶናልድ ሩምስፌልድስ (የቀድሞው የዩኤስ መከላከያ ጸሀፊ ከነበሩት) እንቆቅሎሾች መካከል በመዋስ እስከ አሁን ድረስ እየተነገሩኝ ያሉት ነገሮች ሁሉ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን ፍርሀት በሚመለከት ቀጣይነት ያለው፣ ቀስ በቀስ እያለ የአውዳሚነት ባህሪን የተላበሰ፣ እና የወያኔውን የፖለቲካ ሰውነት እንክት አድርጎ የሚበላ መርዛማ ካንሰር መሆኑን ግንዛቤ ወስጃለሁ፡፡

ሩምስ ፌልድ እንዲህ የሚል ጥቆማ ሰጥተው ነበር፣ “የምናውቃቸው ነገሮች አሉ (የምናውቃቸው የማይታወቁ ነገሮች)፡፡ እንደዚሁም ሁሉገ ነገሮች አሉ የምናውቃቸው የማይታወቁ ነገሮች አሉ፡፡ ይህም ማለት የምናውቃቸው የማይታወቁ ነገሮች አሉ፡፡ ሆኖም ግን የማናውቃቸው የማይታወቁ ነገሮች አሉ፡፡ የማናውቃቸው ነገሮች ልናውቃቸው አንችልም፡፡“ ሩምስ ፌልድ የረሱት እና የተውት እንዲህ የሚል ሌላም ነገር አለ፣ “የሚታወቁ የማይታወቁዎች (የሚታወቁትን ታዋቂ ነገሮች እንደማይታወቁ አድርጎ የመካድ ሁኔታ)፡፡“

ስለሆነም ከዚህ አንጻር እንዲህ ማለት ይቻላል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የፍርሀት ምክንያት፡ የሚታወቅ ታዋቂ ነገር፣

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሚያውቃቸው እና የሚፈራቸው ነገሮች አሉ፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለሩብ ምዕተ ዓመታት ያህል በሌላ በምንም ነገር ሳይሆን በኃይል እና በጡንቻው ብቻ በመተማመን ከህዝብ ፍላጎት ውጭ በህገወጥ መንገድ እየገዛ እንዳለ የሚታወቅ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜም እንደዚሁ የተለመደውን ጡንቻውን በመጠቀም የህዝብን ድምጽ በጠራራ ጸሐይ ዘርፎ እና ነጥቆ በመግዛት ላይ እንደሚገኝ ከምንም በላይ አሳምሮ የሚያውቀው የሚታወቅ ጉዳይ ነው፡፡ ሆኖም ግን በማንኛውም ጊዜ በህዝብ ቁጣ ከተቆናጠጠበት የስልጣን ወንበር ላይ በኃይል እንደሚወገድ ይገነዘባል፡፡ ይህ ፍርሀት ነባራዊ እውነታነት አለው፡፡የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከስልጣን ወንበሩ ላይ የማይወገድ ቢሆን ነበር የሚያስገርመው ነገር፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኢትዮጵያ ህዝብ ዓይን፣ ልብ እና አዕምሮ ውስጥ ምንም ዓይነት ህጋዊ ዕውቅና እንደሌለው የሚያውቀው የሚታወቅ ጉዳይ ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ መንበረ ስልጣኑን የተቆናጠጠው በኢትዮጵያ ህዝብ ይሁንታ እና ሙሉ ፈቃድ ሳይሆን በጠብመንጃ እጃ በጡንቻ ኃይል እንደሆነ አሳምሮ ያውቃል፡፡ እስከ አሁን ድረስ  የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ምን ያህል የተጭበረበሩ እና ዝርፊያ የተካሄደባቸው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫዎች እንዳካሄደ የሚታወቅ ቢሆንም ማንም በሰከነ አዕምሮ ለሚያስብ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የተካሄዱት የቅርጫ ምርጫዎች ሁሉ ነጻ፣ ፍትሀዊ እና በህዝብ ዘንድ ታማዕኒነት ያላቸው እንዳልነበሩ የሚታወቅ ጉዳይ ነው፡፡ ህጋዊ ዕውቅና ያለው መንግስት የህዝቡን ፍላጎት ይወክላል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ግን የሚወክለው የወያኔውን እና የእርሱን ተላላኪዎች እና ጋሻጃግሪዎች ፍላጎት እና ጥቅም ማስጠበቅ ብቻ ነው፡፡

እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 ለሚካሄደው የቅርጫ ምርጫ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዋናው ዓላማው ነጻ፣ ፍትሀዊ እና በህዝብ ዘንድ ታማዕኒነት ያለው ምርጫ በማካሄድ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ ሳይሆን በገንዘብ እየደገፉ እና እየረዱ የኢትዮጵያን ህዝብ መከራ እና ስቃይ በሚያራዝሙት አበዳሪ እና ለጋሽ ድርጅቶች ዘንድ ህጋዊ መስሎ ለመቅረብ ነው፡፡ ገንዘብ በእራሱ ይናገራል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ዴሞክራሲ በመጎልበት ላይ ያለ ነው ካለች ማነው አይደለም ኢትዮጵያ ጭካኔነት በተንሰራፋበት አምባገነናዊ ስርዓት ውስጥ በመዳከር ላይ የምትገኝ ሀገር ናት ሊል የሚችለው? እኮ ንገሩኛ! በእርግጥ ሄለን ኤፕስተን እንዲህ ብለው ነበር፣ “የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ህጋዊነት ዩኤስ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የዓለም ባንክ፣ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ዩኤስ ኤይድ እውቅና የሚሰጡ ቢሆንም ምንም ነገር ማለት አይደለም…“

የቅርጫ ምርጫው እንዲካሄድ የሚፈለገው ዩኤስ አሜሪካ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየፈጸመችው ላለው ዕኩይ ድርጊት የሞራል ኪሳራን ለማካካስ በሚል አጉል ፈሊጥ ልዕልናን ለመቀዳጀት የምታደርገው አሳፋሪ ሁኔታ ነው፡፡ የቅርጫ ምርጫው በየጊዜው መቶ በመቶ እየተዘረፈ እና እየተሰረቀ በሚገባ እየተገነዘበች ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቷ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ምን ያህል ንቀት እና ትዕቢት እንዳላቸው በግልጽ የሚያመላክት ጉዳይ ነው፡፡ እንዲህ በማለት ይሳለቃሉ፣ “ኢትዮጵያ በመጎልበት ላይ ያለ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እያራመደች በመሆኑ በቀጣይነት የሚደረገው ምርጫ ነጻ፣ ፍተሀዊ፣ በህዝብ ዘንድ ታማዕኒነት ያለው፣ በህዝብ ዘንድ ግልጽ እና ሁሉን አቀፋ አሳታፊ እንደሚሆን እንጠብቃለን፡፡ ምርጫ በየጊዜው እንዲደረግም የምንጠብቀው ጉዳይ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ የሀገሪቱ ዴሞክራሲ ከምንጊዜውም በላይ እየተሻሻለ የመጣበት ሁኔታ ነው የሚስተዋለው፡፡“ በማለት ነበር የዩኤስ አሜሪካ ረዳት ጸሐፊ የሆኑት ኢቨንሊ ሸርማን በህዝብ ፊት በአደባባይ የተናገሩት፡፡ ምን ያህል ሸፍጠኝነትን የተላበሰ አባባል ነው!

ደህና፣ እንግዲህ በግንቦት ይካሄዳል እየተባለ ስለሚደሰኮርለት ይቅርጫ ምርጫ ወደፊት የምናየው ስለሆነ የሚያስቸኩል ነገር የለም፡፡

ከህዝብ ይሁንታ ውጭ በኃይል በስልጣን ማማ ላይ ተንጠልጥሎ ለሚገኘው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባህሎች ባይተዋር መሆኑ የሚታወቅ ታዋቂ ነገር ነው፡፡ የኢትዮጵያን ህዝብ ውስብስብ ታሪክ ማህበረሰብ እና ባህል እንደማያወቁት ያውቃሉ፡፡ ይህ ካልሆነማ ታዲያ ለምንድን ነው ኢትዮጵያ የ100 ዓመታት ብቻ ታሪክ ያላት ሀገር ናት እያሉ ህዝብን ሲያደናግሩ የከረሙት? ታዲያ ይህ ባይሆን ኖሮማ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የተቀባው መሪ የነበረው እና በአሁኑ ጊዜ በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ በአያት ቅድመ አያቶቻችን የደም መስዋዕትነት ተከብራ የኖረችውን የነጻነት ቀንዲል አርማ የሆነችውን ባንዲራችንን በአደባባይ ጨርቅ ናት ለማለት ደፈረ?

ምናልባትም ይህ እኩይ አባባሉ ከጨካኙ እና ከአምባገነኑ የቤኒቶ ሙሶሎኒ አስተሳሰብ ጋር ቤተሰብነትን በመመስረት እንዲህ ከሚለው አባባል ጋር መሳ ለመሳ ሊሆን ይችላል፣ ”ለእኛ ብሄራዊ ባንዲራ ማለት በከብቶች የእበት ቁልል ላይ የተተከለ ቡትቶ ነው፡“

በአጠቃላይ በህዝቡ ዘንድ በጣም እንደተጠሉ እና ተቀባይነት እንደሌላቸው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሚያውቁት የሚታወቅ ጉዳይ ነው፡፡ እያንዳንዱን ሰው በመከፋፈል እና በመለያየት እንዲሁም አንድ ለአምስት በሚለው ጥርነፋቸው አማካይነት እያንዳንዷን ነገር የተቆጣጠሩ ይመስላቸዋል፡፡ ጎሰኝነትን የፖለቲካ መሳሪያ አድርገው የመጠቀም ስልትን ነድፈው ላለፉት 24 ዓመታት ህዝቡን በማናቆርና እና በማጫረስ ስኬታማ ሆነዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ዓለም አቀፍ ጥላቻን እና በእነርሱ ላይ መጥፎ አመለካከትን በማጨድ ላይ ይገኛሉ፡፡

ባለፉት 24 ዓመታት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኢትዮጵያ ውስጥ የአሸዋ ቤተመንግስት በመገንባት ላይ እንደሚገኙ የሚታወቅ ታዋቂ ነገር ነው፡፡ አንድ ትንሽ መነሻ ነገር ቢኖር እና የህዝብ የተቃውሞ ማዕበል ቢነሳ በአጭር ጊዜ ወስጥ ተጠራርገው ወደ ታሪክ ቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ እንደሚጣሉ ያውቃሉ፡፡ እነዚህ ዓይን አውጣ ፈጣጣዎች ህዝቡ በቀን አንደ ጊዜ እንኳ ለመብላት ተስኖት በስቃይ ላይ እያለ መሆኑን እየተገነዘቡ ለማደናገር ባለሁለት አሀዝ የምጣኔ ሀብት ዕድገት አስመዝግበናል ይላሉ፡፡ እንደዚሁም ደግሞ በአሁኑ ወቅት እየጎለበተ ያለ ዴሞክራሲ እየገነቡ እንዳሉ በመጮህ እና በመስበክ ሌሎችንም ቆሻሻ የሆኑ ነገሮችን በመፈጸም እነርሱ ምንም የማይነቀነቁ ኃይሎች እና ስርዓታቸውም እንደማዕበል እየተናጠ ባለበት ሁኔታ የተረጋጋ አስመስሎ ለማቅረብ ግብር በሚከፈልበት የህዝብ መገናኛ ብዙሀን ሌት ቀን እንደበቀቀን ሲደግሙት እና ሲደጋግሙት ይደመጣሉ፡፡ እራሳቸውን በባህር ዳርቻ ላይ እንዳለ እና ሊፈርስ እንደማይችል የአሸዋ ግንብ አድርገው ይቆጥራሉ፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዳሉት የታወቁ የወንጀለኛ ድርጅቶች ሳይሆን ከዚያም በበለጠ እና በባሰ መልኩ በከፍተኛ ደረጃ የተዳራጀ ወንጀለኛ የማፊያ ድርጅት መሆኑን የሚያውቁት ታዋቂ ጉዳይ ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ድርጅት መሰረቱን የጣለው በሙስና ቢዝነስ ላይ ነው፡፡ ወያኔው የሌብነት እና የማጭበርበር ባህልን በማዳበር፣ ማታለልን፣ ሸፍጥ መስራትን በጉቦ ቅሌት ውስጥ ተዘፍቆ መገኘትን   እና ህገወጥ በሆነ መልክ  ገንዘብ ማግበስበስን እንደዋና ስልት አድርገው በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡

ማህበረ ረድኤት ትግራይ (ማረት)/Endowment Fund for the Rehabilitation of Tigray (EFFORT) እያለ እራሱን ከሚጠራው የግል የማፊያ ቡድን ስብስብ የግል ንብረት ውጭ አይደለም በአፍሪካ በዓለም ላይም ቢሆን የእራሱ የንግድ ግንኙነት፣ ካፒታል፣ መንግስታዊ ጥበቃ የሚደረግለት፣ ከግብር ነጻ የሆነ፣ ገንዘብን ከህግ አግባብ ውጭ ወደ ውጭ ማስወጣት የሚችል እና በህግ ተጠያቂ ከመሆን ነጻ የሆነ የግል ድርጅት ከማረት በስተቀር ሌላ ሊኖር ይችላልን? እንደዚህ ያለ የበከተ ድርጅት አይደለም መኖር ሊታሰብ የሚችል አይመስለኝም፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እንደ ወንጀለኛ ድርጅት ከማጭበርበር፣ ከመዝረፍ እና ሌሎቸችንም ህገወጥ የሆኑ ነገሮችን ከመስራቱም በተጨማሪ የሰብአዊ መብቶችን በመርገጥ፣ የገንዘብ ማጭበርበር፣ የፖለቲካ እና የጦር እንዲሁም መንግስታዊ ወንጀሎችን በመፈጸም ስራ ላይ ተጠምዶ በመዳከር ላይ ይገኛል፡፡ የዚህ ማፊያ ድርጅታዊ አወቃቀር እና የግንኙነት ሰንሰለቱ በዓለም ላይ እጅግ በጣም በመጥፎነታቸው ከሚታወቁት ወንጀለኛ ድርጅቶች ጋር ጎን ለጎን የሚሄድ ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በሙስና የበከተ፣ በመንደርተኝነት የተሰባሰቡ ጅቦች ከርስ ማጋባሻ የተቋቋመ ወንጀለኛ ድርጅት ነው፡፡ ይህ ወንጀለኛ ድርጅት በርካታ በሆኑ ግላዊ እና የጎሳ እንቅስቃሴ ተግባራት ውስጥ ተዘፍቆ ይገኛል፡፡ እንደዚሁም ይህ ድርጅት ውስጣዊ የቤተሰባዊ ውድድር እና ሊሻሻል እና ሊለወጥ በማይችል ግትር የአስተሳሰብ ማዕቀፍ ውስጥ ተቀፍድዶ ይገኛል፡፡ የማፊያ ጌቶች ለስልጣን፣ ለተጽዕኖ ፈጣሪነት እና የበላይነትን በመቀዳጀት አንዱ ሌላውን ለማጥፋት እንደሚያደርገው ጥረት ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብም ይህንኑ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ስንቶቹ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቁንጮ የአመራር አባላት ናቸው ሻርክ እንደሚባለው ዓሳ እርስ በእርስ በመበላላት ላይ ያሉት?

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሚመራበት ምንም ዓይነት ርዕዮት ዓለም ወይም ደግሞ መሰረታዊ የሆነ የፖለትካ እምነት እንደሌለው የሚታወቅ ታዋቂ ነገር ነው፡፡ እንደ ማፊያ ሁሉ በሙስና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ማግኘት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን እየዘረፈ እንዲኖር እና ኢኮኖሚያዊ የበላይነቱን እንደያዝኩ እንድኖር ያስችለኛል ብሎ ያስባል፡፡ ሁሉም ነገር ዝቅተኛውን የጨረታ ዋጋ ላቀረበ የወያኔ አባል ይሸጣል፣ ወይም ደግሞ በነጻ ይሰጣል (ምንም ዓይነት የልውውጥ ግብይት ይደረጋል የሚል ሀሳብ አልሰነዘርኩም)፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ካራቱሪ ግሎባል ለተባለው ዓለም አቀፍ ኩባንያ በዓመት እጅግ በጣም ጥቂት በሆነ የገንዘብ ኪራይ ብቻ ለም የሆነውን በሚሊዮኖች የሚቆጠር የሀገሪቱን መሬት አስረክቦ ነበር፡፡ ካራቱሪ በአሁኑ ጊዜ ባዶ ሆዱን ሀገር ጥሎ ወጥቷል፡፡ በኢትዮጵያ በጋምቤላ የሚኖሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በአሁኑ ጊዜ የካራቱሪን ባዶ ኮረጆ ተሸክመው ይገኛሉ፡፡ ሌሎች መንታፊ ሌቦች ግን ከካራቱሪ ጋር በተደረገው ስምምነት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ባለቤት ሆነዋል!

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ብቸኛው በስልጣን ላይ የመቆያ ዘዴ አንዱን ጎሳ በሌላው ላይ ማነሳሳት፣ የኃይማኖት ጽንፈኝነት እንዲፈጠር እና በኃይማኖቶች መካከል መተማመን እንዳይኖር አበርትቶ ማስራት እና የጥላቻ እና የበቀል መንፈስ ስር እንዲሰድ ሽንጡን ገትሮ በመስራት ላይ እንደሚገኝ የሚታወቅ ታዋቂ ጉዳይ ነው፡፡ ዘለቄታዊነት ባለው ሁኔታ በስልጣን ላይ ለመኖር እንዲችል የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እኔ ከሌለሁ ሀገሪቱ ትበታተናለች እናም ከፍተኛ የሆነ ብጥብጥ እና ትርምስ ይፈጠራል በማለት ያስፈራራሉ፡፡ እነርሱ ባመጡት የጎሳ የመበላላት ፖለቲካ ምክንያት የኢትዮጵያ ህዝብ እነርሱ እንደሚሉት ወደ ጦርነት ሊገባ እንደማይችል ወያኔዎቹ እራሳቸው ያውቁታል፡፡

እንደ ፍራንከንስተይን ልቦለዳዊ ታሪክ እብዱ ሳይንቲስት በሰው ልጆች ላይ ያደረገው ምርምር መጨረሻው እጅግ በጣም ግዙፍ እና አስቀያሚ የሆነ ፍጡርን ማግኘት ነበር፡፡ በአዲስ መልክ ወደዚች ዓለም በምርምር እንዲመጣ ያደረገውን ሰይጣናዊ ሰው ምንንነት ሳይገነዘብ የእርሱን ፍጡር በማጥፋት ረገድ ሙሉ እድሜውን ጨርሶ ቀርቷል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የእራሳቸው የግል የሆነች ኢትዮጵያን የጎሳ ፌዴራሊዝም እየተባለ በሚጠራ መርዛማ በሆነ የጎሳ ፖለቲካ ቤተሙከራ ውስጥ በእራሳቸው ምዕናብ ለመፍጠር ጥረት ያደርጋሉ፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ክልሎችን (መንቀሳቀስ የሚከለክሉ በረቶችን) ወይም ደግሞ ታዋቂ የሆነውን የአፓርታይድን አይነት ባንቱስታንስ ወይም የጎሳ መንደሮች ለመፍጠር ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ከ25 ዓመታት በኋላ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የእራሱን ፍርንከንሰትይንን አግኝቷል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የጎሳ ፌዴራሊዝምን ያጠፋዋል ወይም ደግሞ እራሱ የጎሳ ፌዴራሊዝሙ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን እንደሚያጠፋ የሚታወቅ ታዋቂ ነገር ነው፡፡ ከወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ውጭ የጎሳ ፌዴራሊዝም እንደማይኖር እና ከጎሳ ፌዴራሊዝም ውጭም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊኖር እንደማይችል የሚታወቅ ታዋቂ ጉዳይ ነው፡፡

አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ እንደ ዶ/ር ቪክተር ፍራንከንስተይን ሁሉ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጭንቅላት እና ልብ የነበረ መሆኑ የሚታወቅ ታዋቂ ነገር ነው፡፡ የመለስ ሁሉም ታዛዥ ሎሌዎች እና ታዛዦች ምሁራዊ ክህሎት በአንድ ላይ ተጨምቆ የመለስን አራት አስረኛ እንኳ እንደማይሆን እንዲሁም የእነርሱ ዶ/ር ፍራንከንሰተይን ቢሞትም እርሱ የፈጠራቸው አጭበርባሪዎቹ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ደቀመዝሙሮች በአሁኑ ወቀት በፍርኃት፣ በሰቀቀን፣ በጭንቀት እና በሽብር የቅዠት ዓለም ውስጥ በመኖር ላይ እንደሆኑ የሚታወቅ ታዋቂ ነገር ነው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሚፈጥረው የጎሳ ፌዴራሊዝም እየተባለ የሚጠራው የፍራንከንሰተይን ስርዓት እራሱ አኝኮ እንደሚተፋው የታወቀ ታዋቂ ነገር ነው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አባላት ሀገር ለመምራት የሚያስችል አቅም እና ችሎታ  እንደሌላቸው የሚታወቅ ታዋቂ ጉዳይ ነው፡፡ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ተቃውሞ አቀጣጥለዋል በሚል ጅል አስተሳሰብ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያላቸውን በርካታ ኢትዮጵያውያን ምሁራንን ከዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ አባረዋል፡፡ ምንም የማያውቁ ደናቁርት ካድሬዎችን፣ የፓርቲ ተማኝ ሎሌዎችን እና ጋሻጃግሬዎቻቸውን በመተካት ልምድ ያላቸውን የሀገር ባለውለታ የሆኑትን ምርጥ የኢትዮጵያ የቢሮክራሲ አራማጆችን እና ወታደራዊ ኃይሉን በማስወገድ እንዲጸዳ አድርገዋል፡፡ ሰፊ ልምድ ያካበቱ እና ችሎታ ያላቸው አስተዳዳሪዎች እንዲወገዱ ተደረጓል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቁንጮ አመራሮች በቅርቡ ለህዝብ ይፋ እንደሆነው በድረ ገጽ በመጠቀም ዲፕሎማዎችን እና ዲግሪዎችን ከሚቀፈቅፈው ወፍጮ በገንዘብ እየገዙ እራሳቸውን ምሁር በማስመሰል ደንቆሮነታቸውን በሀሰት የወረቀት ምስክር ወረቀት ጭንብል ለመደበቅ ሞክረዋል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች እና ተራ አባላት በትምህርት እና በሙያ ክህልት ድርቀት እየተሰቃዩ መሆናቸው የሚታወቅ ታዋቂ ነገር ነው፡፡ ምንም ማድረግ አይችሉም፡፡ አብዛኛውን ጊዚያቸውን በጫካ ውስጥ ያሳለፉ ናቸው፡፡ የተመረቁትም የጭካኔ፣ የማሰቃየት፣ የግድያ እና በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን መፈጸም የሚባሉ ዋና ዋና የትምህርት ኮርሶችን አጠናቅቀው ነው ከጫካ ዩኒቨርስቲ የተመረቁት፡፡ ሆኖም ግን የህግ የበላይነት፣ መልካም አስተዳደር፣ ተጠያቂነት፣ ግልጽነት፣ ወዘተ የተባሉ የትምህርት ኮርሶች በጫካው ዩኒቨርስቲ በፍጹም አይታወቁም ነበር፡፡

ማንም የሚያስብ እና ጭንቅላት ያለው ሰው ምንም ዓይነት የዲፕሎማሲ ስልጠና እና ትምህርት የሌለውን ወይም ደግሞ በሙያው ዘርፍ ምንም ዓይነት ልምድ እና ተሞክሮ የሌለውን የወባ ትንኝ ተመራማሪ የሆነን ግለሰብ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የሀገሪቱ ዋና የዲፕሎማት ሰው አድርጎ የሚሾም ማን ነው? ሌላ ምንም ሳይሆን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ነው፡፡

የአካባቢ ንጽህና መሀንዲስ የሆነን ግለሰብ የአንድ ታላቅ ሀገር ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ የሚሾም ማን ነው (ሹመቱ ለስም ብቻ ለይስሙላ መሆኑ እንዳለ ሆኖ)

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እጅግ በጣም ደካማ የሆነ ስብዕና ያለው ድርጅት ነው!

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የወሮበላ ስብስብ የዘራፊ ጥርቅም መሆኑ የሚታወቅ ታዋቂ ነገር ነው፡፡ (“አምባገነናዊ ዘራፊነት፡ የአፍሪካ ከፍተኛው የአምባገነንነት ደረጃ” በሚል ርዕስ ያዘጋጀሁትን ትችት ልብ ይሏል፡፡) እነዚህ አምባገነኖች በእራሳቸው ልክ የተሰፋ ልብስ ለብሰው ምንም ዓይነት ዝርፊያ እና ሙስና የማያካሂዱ ለመምሰል ይሞክራሉ፡፡ እውነታው ፍርጥርጥ ብሎ ሲታይ ግን ዘራፊ ሌቦችን ከጫካው ማውጣት ይቻላል፣ ሆኖም ግን ጫካውን ከዘራፊዎች ማውጣት አይቻልም፡፡ ስለሆነም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዘራፊ ጌቶች ያለምንም ተጠያቂነት የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ፡፡

ከግንቦቱ የሸፍጥ የቅርጫ ምርጫ በኋላ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እንደተለመደው ሲሰራው የነበረውን የቢዝነስ ስራ እንደዚያው ሊቀጥልበት እንደሚችል የታወቀ ታዋቂ ነገር ነው፡፡ የአሜሪካ ግብር ከፋይ ህዝብ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር በእርዳታ መልክ እንዲፈስ ያደርጋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ዩኤስ ኤይድ የተባለውን ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት እንዲመሩት በኦባማ የተጠቆሙት እና እ.ኤ.አ ከ1980ዎቹ ጀምሮ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዋና ደጋፊ የሆኑት ጋይሌ ስሚዝ ጸድቆላቸው ድርጅቱን የሚመሩት ከሆነ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በዶላር ባህር ውስጥ የሚዋኝ ይሆናል፡፡ ስለመልካም ዕድል ሰበር ዜና! ከይስሙላው የቅርጫ ምርጫው በኋላ የገንዘብ ዕርዳታዎች ከዓለም ባንክ፣ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት፣ ከቻይና፣ ከአውሮፓ ህብረት እና ከሌሎችም እንደ ወንዝ ውኃ ይፈስሳል፡፡ በእርግጥ ህይወት ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጥሩ ይሆናል፡፡

ይኸ ነገር በእርግጥ በእውን የሚሆን ነውን? 

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የፍርሀት መንስኤዎች፡ የሚታወቁ የማይታወቁዎች፣

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሚያውቃቸው ጥቂት የማይታወቁ ነገሮች አሉ፡፡ ስለሆነም በፍርሀት ይርበደበዳል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ጓደኞች እንዳሏቸው ያውቃሉ፡፡ ሆኖም ግን የቁርጥ ቀን ሲመጣ ከእነዚህ ጓደኞች መካከል ስንቶቹ በጽናት ሊቆሙ እንደሚችሉ የሚያውቁት ነገር የላቸውም፡፡

የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረው አዲሱ ለገሰ ባለፈው ዓመት ስለመልካም ጓደኞች 1፡09 የፈጀ ጊዜ ለቡድኑ እንዲህ የሚል ንግግር አድርጎ ነበር፡

ከእራሳችን ሁኔታ ጋር አዛምደን ስንመለከተው ነገሮች ሁሉ ከእጃችን የወጡ ይመስላሉ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ምንም ጥያቄ የሚያስነሳ ነገር አይደለም፡፡ ይህንን ጉዳይ የመምሀራን ማህበር ምን ሲያደርግ እንደነበር በማስረጃነት መመልከት ይቻላል፡፡ 2/3ኛ የሚሆነው የመምህራን ብዛት የእኛ ፓርቲ አባላት ሲሆኑ ከመስመር በመውጣት እኛን እየተቃወሙ ናቸው፣ እንግዲህ ይኸ ነው የታሪኩ መጨረሻ፡፡

በሁለተኛ ደረጃ ችግር እየፈጠረ ያለው አረና ትግራይ ብቻ ነው ብየ አላስብም፡፡ ግንቦት 7ትም እንደዚሁ አለ፡፡ የባህርዳር ሁኔታም አለ ብየ አስባለሁ፡፡ በራሪ ወረቀቶች በመበተን ላይ ነው ያሉት፡፡ ይህ ነገር እውነት አይደለምን? ይህንን አልተቀበላችሁምን? ባህርዳር ላይ ተደርጓል፡፡ ምንጩ ከየት እንደሆነ የምናውቀው ነገር የለም፡፡ ሆኖም ግን በራሪ ወረቀቶችን ሲያሰራጩ ነበር እናም በህዝቡ ሲታዩ ነበር፡፡ በእያንዳንዱ ሁኔታ ሲታይ እስከ ህዋስ ደረጃ ድረስ የወረዳ አካሄድ ድረስ እንደሄዱ አስባለሁ፡፡ እራሱን ያደራጀ ኃይል ያለ ይመስላል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወዳጆች እንዳሉት ያውቃል ሆኖም ግን ከወዳጆቹ መካከል የትኞቹ እውነተኛ ወዳጆች እንደሆኑ የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ወሳኙ ቀን ሲመጣ አባላቱ/ወዳጆቹ መካከል የትኞቹ ዋና ጠላቶች እንደሆኑ የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ ስለሆነም በፍርሀት ቆፈን ውስጥ እንደተወሸቀ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የኢሳት ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ስርጭቶች የአየር ሞገዱን እንደተቆጣጠሩት እና በከፍተኛ ደረጃ ተመራጭ የመረጃ ምንጭ እየሆኑ እንደመጡ ያውቃል፡፡ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ስሌት እና ግምት መሰረት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች በእርግጠኝነት የኢሳትን ፕሮግራሞች የሚመለከቱ እና የሚያዳምጡ መሆናቸውን ያውቃሉ፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የኢሳት ፕሮግራሞች በህዝቡ ልብ እና አዕምሮ ውስጥ ምን ዓይነት ሽግግራዊ እና መዋቅራዊ እንደምታ ሊያስከትሉ እንደሚችሉ የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ ስለሆነም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የኢሳትን ስርጭት ለማፈን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዶላሮችን ወጭ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ በበርካታ አጋጣሚዎች የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች የተቆጣጠሯቸው የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን መገናኛ ዘዴዎች በአብዛኛው ህዝብ እንደማይታዩ እና እንደማይደመጡ ለህዝብ አምነዋል፡፡ 

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የፍርሀት ምክንያት፡ የማይታወቀው የማይታወቅ ነገር፣

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊያውቃቸው የሚችላቸው የማይታወቁ ነገሮች እንዳሉ ያውቃል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በሁሉም ክልሎች የለኮሱት የጎሳ እሳት በመጨረሻው ምን እንደምታ ሊያስከትል እንደሚችል የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ክልሎች በአመጽ ሊቀጣጠሉ ከሚችሉ የፖለቲካ አመጾች አስቤስቶስ በመሆን ከሚቀጣጠለው እሳት ሊድኑ እና ሊያገለግሉ እንደሚችሉ እና አገዛዙን ለዘላለም ሊያቆዩለት እንደሚችሉ አድርጎ ያስባል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ክልል እየተባለ የሚጠራው የትም ሊያስሄድ እንደማይችል እና ተግባራዊነቱ አጠራጣሪ መሆን በውል ተገንዝቧል፡፡ ሆኖም ግን የክልሎች አስቤስቶሱ የበለጠ እየጋለ ሲሄድ እና ጋሱ ወደፊት እና ወደ ኋላ እያለ ሲቀልጥ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ከፍተኛ ግፊት ይፈጠር እና የህዝቡ ከፍተኛ ቁጣ እና ጥላቻ አውዳሚ የሆነ እሳት በመጫር ሊያስከትል የሚችለውን እንደምታ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊያውቀው ያልቻለው የማይታወቅ ሁኔታ ነው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በቀላሉ ሊፈነዳ በሚችል በሰዓት በተሞላ ቦምብ ላይ የተቀመጠ መሆኑን የሚያውቀው አይመስልም፡፡ የማቀጣጠያው ፊውዝ ከክልሎች ጋር የሚገናኝ መሆኑን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊያውቀው የማይችለው የማይታወቅ ነገር ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ፊውዙን በማቋረጥ እሳቱ ተቀጣጥሎ ፍንዳታ እንደሚያመጣ ብልሀቱን የሚያውቀው አይመስልም ምክንያቱም በእብሪት እና በድንቁርና በመሞላት በጭፍን እየጋለቡ ያሉ ፍጡርች ናቸው፡፡ ተቀጣጣዩ ፊውዝ መቀጣጠሉን ቀስ በቀስ እያያዘ ይገኛል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ክልላዊ ያለመረጋጋት በአገዛዙ ላይ ከፍተኛ የሆነ ውድመትን ሊያስከትልበት እንሚችል ሊያውቀው የማይችለው የማይታወቅ ነገር ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በየመን፣ በሶማሊያ፣ በኤርትራ እና በደቡብ አፍሪካ የተቀሰቀሱት አመጾች ወደ ኢትዮጵያም ሊዛመቱ እንደሚችሉ እና ያልተጠበቀ ቀውስ ሊያስከትሉ እንደሚችሉ የሚያዉቁት ነገር የላቸውም፡፡ ያ አውዳሚ ክስተት መቸ ሊፈጸም እንደሚችል የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊያውቀው የማይችል የማይታወቅ ነገር ነው፡፡ ስለሆነም ወያኔው ጣቶቹን እያወዛወዘ እና እራሱን እያከከ ዝም ብሎ የሚመጣውን ነገር በመመልከት ላይ ይገኛል፡፡

የኃይማኖት ጽንፈኝነት እሳት እያደገ ሄዶ ወደ 7ኛ የብሄራዊ እሳት ሊሸጋገር የሚችል ማስጠንቀቂያ መሆኑን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊያውቀው የማይችል የማይታወቅ ነገር ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዓይኑን በጨው ታጥቦ በኃይማኖት ላይ ያለምንም ይሉኝታ እጁን በማስገባት ለክርስትና እና ለእስልምና ኃይማኖት እምነቶች የኃይማኖት መሪዎችን እራሱ መርጦ በመሾም እንካችሁ ብሏል፡፡ በኃይማኖት ቡድኖች እና በእምነት ተቋሞች መካከል የኃይማኖት ጽንፈኝነት ጦርነትን ለማምጣት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በእምነቶች መካክል ጭረውት የነበረው ግጭት በምን ምክንያት ስኬታማ ሊሆን እንዳልቻለ ሊያውቁት የማይችሉት የማይታወቅ ነገር ነው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኃይማኖት ጽነፈኞች በኩል እየጫሩት ያለው እሳት በመጨረሻ እራሳቸውን ሊያወድም እንደሚችል ሊያውቁት የማይችሉት የማይታወቅ ነገር ነው፡፡ የጫካ እሳት ምንም ዓይነት ልዩነት አያደርግም፣ በመንገዱ ላይ ያገኘውን ማንኛውንም ነገር ሁሉ ይለበልባል፣ ያወድማል፡፡

ወጣቱ ወደፊት ምን ለማድረግ እንደሚችል ምንስ ውጤት ሊያስከትል እንደሚችል የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊያውቀው የማይችለው የማይታወቅ ነገር ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ወጣቱን በጥቅማ ጥቅም እና በሌሎች ዕድሎች በመደለል የወጣቱን ልብ እናአዕምሮ ለመቆጣጠር እንደማይችል የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በጥቅማ ጥቅም በመደለል ወጣቱን ታማኝ እና ለድርጅቱ ምን ያህል ፍቅር እንዳለው በአባልነት የተለያዩ መደለያዎችን በመስጠት ጥቂት የሆኑ ወጣቶችን ሊያገኙ ለመቻላቸው እንኳ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ ገንዘብ ፍቅርን ወይም ደግሞ ታማኝነትን ሊገዛ እንደማይችል የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሚያውቀው ነገር አይደለም፡፡ ወጣቱ ከምንም በላይ ነጻነቱን ይፈልጋል፡፡

አብዛኛውን ሙያዊ ህይወቴን ያሳለፍኩት በዓለም ላይ ከሚገኙ ወጣቶች ጋር ነው፡፡ ከሁሉም ነገሮች በላይ ወጣቶች በሁለት ነገሮች ላይ የበለጠ ፍላጎት ያሳያሉ፡ እነርሱም እኩልነት እና ነጻነት ናቸው፡፡

የእኔ አመለካከት “የዓለም ወጣቶች ድምጽ በድህረ 2015” በሚል ርዕስ በበርካታ ሀገሮች ከተጠናው ጥናት ጋር ተደጋጋፊ ሆኖ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ወጣቶች የዜግነት ደረጃቸው፣ የህይወት ዕድሎቻቸው እና ዕጣፈንታዎቻቸው በአባልነት እና በታማኝነት ላይ በተመሰረተ መብትን፣ እኩልነትን እና ነጻነትን በገፈፈ በአንድ ቡድን ወይም ድርጅት እንዲወሰን በፍጹም አይፈልጉም፡፡ ወጣቶች ግላዊ ነጻነትን መቀዳጀት እና የሀገራቸውን ዕድል መወሰን እንደሚፈልጉ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊያውቀው ያልቻለው የማይታወቅ ነገር ነው፡፡ ወጣቶች የህግ የበላይነት የሰፈነበት እና የግለሰብ መብቶች ሙለ በሙሉ የሚጠበቁበት እኩልነት የሰፈነበት ስርዓት ተመስርቶ ማየት ይፈልጋሉ፡፡

የተቃዋሚ ኃይሎች በአንድነት ህብረት ፈጥረው በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ የሚገኘውን አካል በአንድ ወቅት አስፈንጥረው እንደሚጥሉት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊያውቀው ያልቻለው የማይታወቅ ነገር ነው፡፡ አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ ጋዳፊ እየታደነ እና እንደ አይጥ ከፉካ ውስጥ ተወሽቆ በተቃዋሚዎች ተይዞ በተገደለበት ወቅት  እንዲህ የሚል የመማጸኛ ንግግር ተናግሮ ነበር፣ “ህዝቦች እኔን ይወዱኛል!“ በታሪር አደባባይ ላይ እርሱን ከስልጣን ለማውረድ ህዝባዊ አመጽ እንደ ሰደድ እሳት ተቀጣጥሎ በነበረበት ጊዜ ለሙባረክ ማንም የተጻፈ ማስታዋሻ ወይም ደግሞ የኢሜይል መልዕክት አልላከም ነበር፡፡ ጊዜው በመጣበት ጊዜ መጣ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ላይም ጊዜው ሲመጣ ይመጣበታል፡፡ ሆኖም ግን ጊዜው መች እንደሚመጣ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊያውቀው የማይችለው የማይታወቅ ነገር ነው፡፡ መቸ እንደሚወድቁ እና የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውስ ምን ሊሆን እንደሚችል ቀኑ መቸ እንደሆነ ለመተንበይ በርካታ እንቅልፍ አልባ ሌሊቶችን በማሳለፍ ላይ ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ መች እንደሚመጣ እና እነርሱን ወደ ታሪክ አተላ ሊጥላቸው እንደመሚችል የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊያውቁት የማይችሉት የማይታወቅ ነገር ነው፡፡ ዴሞክራሲ የህግ የበላይነትን ጋሻ እና የተጣያቂነትን ጦር በመያዝ መቸ እንደሚመጣ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊያውቁት የማይችሉት ነገር ነው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የፍርሀት ምክንያት፡ የማይታወቀው የሚታወቅ ነገር (የሚታወቅን ታዋቂ ነገር መካድ)

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እያወቀ ሆን ብሎ ለመቀበል ፈቃደኛ የማይሆንባቸው እና እያወቀ ዕውቅና የማይሰጥባቸው እውነታዎች አሉ፡፡ ስለሆነም ይፈራል!

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች እስከ አሁን ድርስ ለሰሯቸው ወንጀሎች አሁን ወይም ቆይቶ በህግ አደባባይ ቀርበው እንደሚጠየቁ እያወቁ ያላወቁ መስለው ለመቅረብ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ “ፍትህ እንደ ባቡር ነው፣ ሁልጊዜ ይዘገያል” የሚለውን እውነታ የማያውቁት ለማስመሰል ይሞክራሉ፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ይዘገያል የሚለውን ቃል በፍጹም እንደሚል ቃል አድርገው ይገነዘቡታል፡፡ በእነርሱ የድንቁርና እብሪት ተነግሮ ለማያልቀው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለፈጸሟቸው የሰብአዊ መብት ረገጣ ወንጀሎች ተጠያቂ እንደሚሆኑ የማያውቁ መስለው ለመቅረብ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ምንም ዓይነት መሳሪያ ያልታጠቁ 193 ሰላማዊ ዜጎችን በጠራራ ጸሐይ በአደባባይ ገድለው እና ሌሎች 800 የሚሆኑትን ደግሞ የመግደል ሙከራ አድርገው በፈጸሙት ወንጀል ተጠያቂ ሳይሆኑ በእርግጠኝነት አምልጠው የሚሄዱ ይመስላቸዋል፡፡ ጊዜው ሲደርስ ለህግ ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡ ይህ ማለት ጸሐይ በጠዋት ትወጣለች የማለት ያህል እውነታነት ያለው ነገር ነው፣ ምክንያቱም የዩኒቨርስ ግማሽ ጥምዝ ክብነት ረዥም ነው፣ ሆኖም ግን ሁልጊዜ ወደፍትህ ያጋድላል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች ኡሁሩ ኬንያታ በኬንያ ህዝብ ላይ ተካሂዶ ከነበረው እልቂት ጋር በተያያዘ መልኩ ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተመስርቶበት ከነበረው ክስ እንዲለቀቅ ለማድረግ ያለ የሌለ ጥረታቸውን አድርገዋል፡፡ በሰው ልጆች ላይ የሰብአዊ መብት ረገጣ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸሙ አምባገነኖች ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በመቅረብ ጉዳያቸው በፍትህ አደባባይ እንዲመረመር ስልጣን የሚሰጠውን የሮም ስምምነት በመጣስ የአፍሪካ የድርጅቱ አባል ሀገሮች በጅምላ ለቀው እንዲወጡ በማስተባበር ከፍተኛ የሞት ሽረት ትግል እድርገዋል፡፡ ኡሁሩ በሰራው የሰብአዊ መብት ረገጣ ወንጀል ወደ ዘብጥያ ሲወርድ በቀጣይነት ደግሞ እነርሱ እንደሚገቡ ያላወቁት ሆኖም ግን የሚያውቁት ነገር ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፍትህ እንደባቡር ትዘገያለች፡፡ በማረፊያ ጣቢያዋ እስከምትድርስ ድረስ በትዕግስት መጠበቅ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እንደሚባለው በእርግጠኝነት በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ነውን?

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በፍርሀት ውስጥ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡ በአጠቃላይ ወታደሩን፣ የምጣኔ ሀብቱን፣ ቢሮክራሲውን በብቸኝነት ጨምድዶ ይዞ እና ከ5 ሚሊዮን በላይ አባላት አለኝ የሚል ኃይል በፍርሀት ውስጥ ነው የሚለው ክርክር አመክንዮ የለውም፡፡

ከዚህ በተጻረረ መልኩ ግን ፍርሀት እራሱ ነው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ወታደራዊ ኃይሉን፣ ቢሮክራሲውን፣ የምጣኔ ሀብቱን፣ ወዘተ በብቸኝነት ጠቅልሎ ይዞት እንዲቀጥል ያደረገው፡፡ ፍርሀታቸውን ለማሸነፍ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ስልጣንን ያዙ፡፡ እናም በአሁኑ ጊዜ ለሩብ ምዕተ ዓመት ያህል በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ይገኛሉ፡፡ ፍርሀት እራሱ እነርሱን ድል አድርጓቸዋል፡፡

ሆኖም ግን ፍርሀት ግላዊ እንጅ ድርጅታዊ አይደለም፡፡ እያንዳንዳቸው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራር እና አባላት በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ናቸው፡፡ ነግር ግን የሁሉም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች በመቀላቀል የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የግል ኃላፊነቱ የተወሰነ የፍርሀት ማህበር ድርጅትን ፈጥረዋል፡፡

ፍርሀት እራስን ለመጠበቅ ከሚደግ ተፈጥሯዊ ክስተት ይመነጫል፡፡

የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪ ከነበርኩበት ጊዜ ጀምሮ በቶማስ ሆብስ ጽሁፎች ላይ በጣም እመሰጥ ነበር፡፡ ይህ ሲባል እነ ሎኬን፣ ማቻቬሊን፣ አኩይናስን፣ ዲስካርተስን፣ ማርክስን፣ ሩሴልን እና ሌሎችን ጥቂቶች ጸሐፊዎችን በማግለል አይደለም፡፡ በእርግጥ ስለአምባገነንነት ጽሁፍ ያበረከተው እና ክብር የማይሰጠው እንዲሁም ሁሉንም ባህል ለማጥፋት ጥረት የሚያደርገው ቶም ባይኔም አለ፡፡

እንደ ሰብአዊ መብት ተሟጋችነቴ በተለይም በሆብስ “የሉዓላዊነት ፍጹምነት” ሀሳቦች ላይ እና ፍርሀት ፍጹምነትን በምን ዓይነት አመክንዮ እንደሚመለከት በሚለው ላይ የተለየ ትኩረት አለኝ፡፡ ሆብስ አምባገነንነት እያልን በምንጠራው ላይ ጠቃሚ የሆኑ እይታዎችን አካትቷል፡፡ ንጉሳዊ አገዛዙ በተገዥዎች ላይ ፍጹም የሆነ ስልጣንን የሚያሳይ የንጉሳዊ መንግስት ቅርጽን በመፍጠር ረገድ በጣም ፍላጎት ነበራቸው፡፡ የሆቤሲያን ፍጹማዊ ንጉሳዊ አገዛዝ በአሁኑ ጊዜ ካለው ዘመናዊ ፍጹማዊ አምባገነንነት ጋር እኩል ይሆናል፡፡

ሆብስ ፍርሀት በተፈጥሯዊ ባህሪ ላይ ይሰራጫል በማለት ሞግተዋል፡፡ (ምዕናብ የሰው ልጆች  የሲቪል ማህበረሰቡን ከመፍጠራቸው በፊት እራሳቸው እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፡፡) በተፈጥሮ ባህሪ የሰው ልጆች ቀጣይነት ባለው ሁኔታ በፍርሀት እና በኃይለኛ የሞት አደጋ ውስጥ ገብተው ይናጣሉ፡፡ እናም የሰው ልጅ ህይወት ብቸኛ፣ ደኃ፣ ደስታ የራቀው፣ ጨካኝ እና ባለጌ ይሆናል፡፡ ሆብስ ሲቪል ማህበረሰቡ በጋራ ፍላጎት ላይ በመመስረት እና ለእያንዳንዱ በመተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን ሁሉም እያንዳንዳቸው ባላቸው ፍርሀት እንደነበር ሞግተዋል፡፡ ፍርሀታቸውን ከማውጣት ከሚጠብቃቸው ውጭ እያንዳንዱ ሰው ከሌላው ሰው ጋር ተጻራሪ በመሆን ጦርነት እየተባለ በሚጠራው መጥፎ ድርጊት ውስጥ እራሳቸውን ያገኙታል፡፡

ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የኢትዮጵያን ሲቨል ማህበረሰብ ወደ ሆቤስቲያን የተፈጥሮ ባህሪ ወስዶታል ፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እ.ኤ.አ በ1991 ስልጣንን ሲቆናጠጥ በጫካ ውስጥ ሲሰሩት የነበረውን ባህል ይዘው በመምጣት በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ላይ መተግበር ጀመሩ፡፡ በጫካ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ በጫካው ህግ ይገዙ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ የጫካውን ህግ በህግ የበላይነት ለመተካት ፈቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡ ስለሆነም አሁንም ቢሆን በጫካ ውስጥ ሲያደርጉት አንደነበረው ሁሉ ሰላማዊውን ህዝብ ያስፈራራሉ፣ ያሸማቅቃሉ፣ ያስራሉ፣ ስቃይ ያደርሳሉ እንዲሁም በተቃዋሚዎቻቸው ላይ ግድያን ይፈጽማሉ፡፡ ከዚህም በላይ በሲቪሎች ላይ የሽብር ድርጊትን ይፈጽማሉ እንዲሁም በሀሰት ተቃዋሚዎቻቸውን ይወነጅላሉ፡፡ በእርግጥ ለእነርሱ በሚስማማ መልኩ ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡

ለሩብ ዓመታት ያህል የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በጣም ውስብስብ የሆነውን የኢትዮጵያን ሲቪል ማህበረሰብ ወደ ሆቤሲያን የተፈጥሮ ባህሪ መልሰውታል፡፡ በሆቤስቲያን የተፈጥሮ ህግ መሰረት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ፍጹማዊ አምባገነኖች ተፈጥረዋል፣ ይከሰታል ብለው በሚፈሩት የህዝብ አመጽ፣ ሽፍትነት፣ ህዝባዊ ነውጥ እና አብየት ምክንያት ቀጣይነት ባለው ሁኔታ በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ተዘፍቀው ይገኛሉ፡፡ አስቀድሞ ሊወሰን በማይችል የሚታወቅ ታዋቂ፣ በሚታወቅ የማይታወቅ እና በማይታወቅ የማይታወቅ የተፈጥሮ ባህሪ ውስጥ እየኖሩ ይገኛሉ፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዋናው ፍርሀቱ ለውጥ ነው፣

ለውጥ መጣ ማለት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ባለፉት 24 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ያከማቸውን ስልጣኑን እና ክብሩን አጣ ማለት ነው፡፡ ለውጥን ይፈራሉ ምክንያቱም ለውጥ ማለት ደህና፣ ማን ያውቃል? ለውጥ የማይቀር ተፈጥሯዊ ህግ ነው፡፡ በዩኒቨርስ ላይ በቋሚነት በሂደት ላይ የሚገኘው ለውጥ እራሱ ነው፡፡ ለውጥ የሚታወቅ ታዋቂ፣ የሚታወቅ የማይታወቅ፣ የማይታወቅ ታዋቂ ወይም ደግሞ የማይታወቅ ታዋቂ ያልሆነ ቢሆንም ባይሆንም መምጣቱ የማይቀር የተፈጥሮ ህግ ነው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች አናሳ የሆነ አመላካከት እና እይታ ያላቸው በመሆናቸው ምክንያት በአሁኑ ጊዜ ያለውን ነገር ብቻ አይደለም የሚፈሩት ሆኖም ግን የወደፊቱን ጭምር ነው፡፡

ድንቁርና ፍርሀትን ይፈለፍላል፡፡ ፍርሀት ማቆሚያ የሌው ደህንነትን ይጠይቃል፡፡ አንድ ዋና የሆነ የሚታወቅ ታዋቂ፣ ታዋቂ የማይታወቅ እና መወሰን ከማይቻለው ፍርሀት ጋር እንዴት ነው ስምምነት ማድረግ የሚቻለው?

ስለሆነም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ መሰረት የሌለውን ፍርሀት መፍራቱን እንዲያቆም በመወገዝ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ለእዚህ የእራሳቸውን ቅርጽ ለመያዝ ጥረት እያደረጉ ናቸው፡፡ ግንቦት 7፣ አንድነት ፓርቲ፣ ሰማያዊ ፓርቲ እና አረና ፓርቲ…አሸባሪነት ነው፡፡ በእርግጥ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ በተለይም አክራሪው እና ጽንፈኛው ዲያስፖራ ነው በዚህ ዓይነት መልክ እየተፈረጀ ያለው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በስልጣን ላይ እስከሌለ ድረስ በኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት እና ስርዓተ አልበኝነት ሊፈጠር እንደሚችል በተደጋጋሚ ሲለፍፍ ቆይቷል፡፡ እነርሱ በስልጣን ላይ እስካልኖሩ ድረስ የእርስ በእርስ ጦርነት እና እልቂት እንደሚመጣ ህዘቡን በማስፈራራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ይኸ ድድብና የተቀላቀለበት ንግግር ቀበሮ በጎችን እረኛ ሆኖ ከመስክ ሲጠብቃቸው ውሎ ማታ ወደ ጉረኗነቸው በማምጣት እንደሚያስገባቸው ዓይነት የመጠበቅ ሁኔታ ነው፡፡

በአረቦች የጸደይ አብዮት ህዝብ ፍርሀቱን አስወግዷል እናም አምባገነኖችን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ሁኔታ በአንድ ጀንበር ላይ ይፈጸማል ብሎ ማሰብ አይቻልም፡፡ ይህን ሁኔታ በአስርት ዓመታት እና ከዚያ በላይ ጊዜ ሊወስድ ይችላል፡፡ የአረብ አምባገነኖች ለበርካታ አስርት ዓመትት በብረት ጡንቻቸው ቀጥቅጠው ገዝተዋል፡፡ በመጨረሻም የህዝቡ ቁጣ እነዚህን አምባገነኖች እንዳለ በመክበብ ውጧቸዋል፡፡ ዓሊን በቱኒሲያ ለማስወገድ ጥቂት ቀናት ብቻ ናቸው የወሰዱት፡፡ ሙባረክን ከዙፋኑ አውርዶ ለመጣል ጥቂት ሳምንታትን ወስዷል፡፡ ጋዳፊን ለማስወገድ ደግሞ ጥቂት ወራትን ጠይቋል፡፡ በሶሪያ አላሳድን ለማስወገድ 5 ዓመታትን የወሰደ ሲሆን አሁንም ቢሆን ከስልጣኑ አንኮታኩቶ ጥሎ ወደ ታሪክ ቆሻሻነት ለመቀየር ኃይለኛነቱን እንደቀጠለበት ይገኛል፡፡ እነዚህ አምባገነኖች ለበርካታ አስርት ዓመታት ያህል የጭራቃዊነትን ረዥም ጥላቸውን በህዝብ ላይ ጥለው ቆይተዋል፡፡ በመጨረሻም የእራሳቸው ጭራቃዊ ጥላ ከስልጣናቸው ላይ እንዲያጠላባቸው ተደርገዋል፡፡

ታሪክ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን ዋና ፍርሀት ያወግዛል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የገነባው የፍርሀት ግንብ ጡቦች ቀስ በቀስ እያሉ እየፈረሱ ናቸው፡፡ እነዚህ እየፈረሱ የሚወድቁት ጡቦች ወያኔው እራሱን እንዲደብቅበት ከለላ ሆነዋል፡፡ ሆኖም ግን የህዝቡን የቁጣ የሱናሜ ማዕበል ሊያስቀር የሚችል ምንም ዓይነት ግድግዳ የለም፡፡

ፍትህን የደፈጠጠ ማንም ደፋር የሆነ ወንጀለኛ ሰው ቢሆንም እንኳ ዞር በማለት እራሱን ይመረምራል፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ምን እንደሰራ ስለሚያውቅ ነው፡፡ በጭራቃዊው ምዕናብ ላይ የሚታይ ይሆናል፡፡ ፖሊስ ከእርሱ በኋላ ሲመጣ ይታያልን? ሰዎች ሲተነፍሱ የሚመለከት የአዕምሮ በሽተኛ ሆኗል፡፡ ስለእርሱ ጉዳይ ያወራሉን? የፖሊስ መኪና የፎቶግራፍ ካሜራ ይዞ ይመለከታል፡፡ እርሱን ለማግኘት እየመጡ ነውን? የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ወንበዴዎች ሁለጊዜ ትከሻዎቻቸውን ነው የሚመለከቱ፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን በከበበው ፍርሀት ላይ የመጨረሻው ክሴ እንዲህ የሚል ቀላል ነገር ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች መጠጫ ምን ሊሆን እንደሚችል ጥቂቶች ሊተነብዩት የሚችሉት ጉዳይ ነው፡፡ እነርሱ ገንዘብ አይደለም የሚፈልጉት፡፡ ይኸ እጅግ በጣም ብዙ አላቸው፡፡ ሁሉንም ነገር ለማድረግ ሁሉም ስልጣኑ አላቸው፡፡ ሙገሳን አይፈልጉም፡፡ ሆኖም ግን አንድ በጣም የሚፈልጉት ግን የማያገኙት ነገር ቢኖር ከህዝቡ ጋር አብሮ መሄድ እና የህዝቡን ከበሬታ ከማግኘቱ ላይ ነው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች፣ አባላት እና የእነርሱ ታዛዥ ሎሌዎች በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ተወሽቀው እየኖሩ ስለመሆናቸው እውነታውን በእርግጠኝነት አላውቅም፡፡ ነግር ግን በእርግጠኝነት የማውቀው  ጉዳይ ቢኖር ህዝቡ ከቀን ወደ ቀን ድፍረቱን እየጨመረ መጥቷል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እራሱ በፈጠረው ችግር ምክንያት በተስፋ መቁረጥ ፍርሀት ውስጥ እየሰመጠ እንደሚገኝ እውነታውን አውቃለሁ፡፡ ህዝቡ እየተነሳሳ ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ደግሞ ወደ መቀመቅ እየወረደ ነው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሁለት አማራጮች አሉት፡፡ እንዲህ የሚለውን የኔልሰን ማንዴላን መንገድ መከተል ይችላሉ፡፡ “ጀግና ማለት የማይፈራ ማለት አይደለም ሆኖም ግን ጀግና ማለት ፍርሀትን የሚያሸንፍ ነው፡፡“ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ያለበትን ፍርሀት በነባራዊ ካሉት እና ሊመጡ ከሚችሉት ጠላቶች ጋር ሰላም በመፍጠር ድል ማድረግ ይችላል፡፡

ሌላው አማራጭ ደግሞ ፍርሀትን እራሱን በመፍራት ከፍርሀት ግድግዳ ጀርባ በመሆን የአሸዋ ቤተመንግስት መገንባት ነው፡፡ ይህንን ጉዳይ በማስመልከት ፍራንክሊን ሩዝቬልት እንዲህ በማለት ተናግረው ነበር፣ “እኛ መፍራት ያለብን ብቸኛው ነገር ስምየለሹን፣ በአመክንዮ የማያምነውን፣ የሚያስልጉ ጥረቶችን በሽብር የሚያመክነውን ፍርሀትን እራሱን ነው፡፡“

እንግዲህ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ምርጫ ይኸ ነው!

የዘረፋው የግንቦት 24/2015 የቅርጫ ምርጫው እንዴት ነው?

ምርጫን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለአፍሪካ ህዝቦች ሁሉ ያስተምራል የሚል እምነት አለኝ፡፡ መርህ አልባው የሱዳኑ ኦማር አልባሽር ከጥቂት ሳምንታት በፊት አካሂዶት በነበረው ምርጫ 94.04 በመቶ በሆነ የድምጽ ውጤት ያሸነፈ መሆኑን አውጆ ነበር፡፡ ይኸ ምንም ነገር ሳይሆን ባዶ ነገር ነው!

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከአምስት ዓመታት በፊት የቅርጫ ምርጫ በማካሄድ 99.6 በመቶ አሸነፍኩ ብሎ ሲያውጅ አሁን በህይወት የሌለው መለስ እንዲህ የሚል ንግግር ነበር ያሰማው፡

ለእኛ ድምጻቸውን ያልሰጡን ዜጎች እንዳሉ እንገነዘባለን፡፡ ለእኛ ድምጻቸውን ያልሰጡን ዜጎችን ፍላጎት በጽኑ በማክበር የነበሩብንን ደካማ ጎኖች እና ድክመቶች በማስተካከል የእነርሱን ድምጽ በቀጣዩ ምርጫ ለማግኘት ስንል ሌት እና ቀን የምንሰራ መሆናችንን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡

ስለሆነም ትክክለኛው ጉዳይ እና በግንቦት 2015 ስለሚካሄደው የቅርጫ ምርጫ እ.ኤ.አ በ21010 ድምጻቸውን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ያልሰጡትን ሰዎች ልብ ማሸነፍ እና የአንድ ፐርሰንት 4/10ኛ የሆነችዋን ቁርጥራጭ ቁጥር በማሟላት በ2015 መቶ በመቶ ማሸነፍ ነው፡፡ አልባሽር ተበልጠሀል ልብህን ብላ! መቶ በመቶ በማምጣት አስከንድተንሀል!

እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ በማለት እንዲህ የሚል ንግግር ያደርጉልናል፣ “ባለፈው ጊዜ ምርጫውን መቶ በመቶ ባለማሸነፋችን በጣም አዝነናል፡፡ ጭራዎቻችንን በእግሮቻችን መካከል ወትፈናል፡፡ አሁን ግን መቶ በመቶ አሸንፈናል!“

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በሙሉ የቅርጫ ምርጨውን መቶ በመቶ በማሸነፋችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አስደማሚ በሆነ መልኩ በዝረራ  ለሚያሸንፈው የቅርጫ ምርጫ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ለማስተላለፍ የመጀመሪያው እኔ እንደምሆን ለእያንዳንዱ ሰው ግልጽ ለማድረግ እፈልጋለሁ፡፡ 

መንግስት ህዝብን መፍራት ሲጀምር ነጻነት አለ ማለት ነው፡፡ ህዝብ መንግስትን መፍራት ሲጀምር ደግሞ አምባገነንነትተንሰራፍቷል ማለትነው፡፡ “ ቶማስ ጃፈርሰን 

ህዝብን ፍሩ! እውነትን ፍሩ! 

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ሰኔ 7 ቀን 2007 .

 

Filed in: Amharic