>

“በአሽባሪነት ተጠርጥሮ “የታሰረው ታዳጊ የፕ/ት ኦባማ ልዩ እንግዳ ሆኖ ተጋበዘ [ታምሩ ገዳ]

“ልጄ በት/ቤት ጓደኞቹ ፊት በካቴና በመታስሩ በጣም አዝኛለሁ” ወላጅ አባት

የ 14 አመቱ አህመድ መሃመድ ገና ታዳጊ፣ የሙስሊም እምነት ተከታይ እና የ9ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን በእርሱ እድሜ ሊሰሩ አይደለም ሊታሰቡ የማይሞከሩትን የኢሌክትሮኒክስ ቁሶችን መገጣጠም የእለት ተገባራቱ ናቸው ። ታዲያ ይህ በአሜሪካው የቴክሳሱ ግዛት በኢቪርንግ ከተማ የ ማክአርቱር ከፍተኛ ደረጃ የመጀመሪያ አመት ትምህርቱን ሰሞኑን የጀመረው ታዳጊው አህመድ ባለፈው ሰኞ ወደ ት/ቤቱ አንድ እንግዳ ነገር ይዞ ጎራ ሲል ያለጠበቀው እና ያልገመተው ችግር ይገጥመዋል።አህመድ ከፈጠራ ሰራዎቹ መካከል አንዱ የሆነው የማንቂያ ሰአት ለመምህሩ ለማሳየት እና ችሎታውን ለማሰመረቅ ቢሞክርም መምህርቱ የአህመድ እቃ ሰአት ሳይሆን “ቦምብ ይመሰላል” ከሚል ጥርጣሪ ላይ በመወደቃቸው ፖሊስ ተጠርቶ አህመድም አጁ በካቲና ታስሮ በቁጥጥር ሰር ይውላል።  Ahmed Mohamed by Tamru Geda

ከ ሱዳን ተሰደው በ አሜሪካ ከ 30 አመት በላይ የኖሩት ወላጅ አባቱ መሃመድ ኢል ሁሰን መሃመድ በልጃቸው ላይ የደርሰው የሰበኣዊ መብት ረገጣን በማሰመልከት ሲናገሩ “ ልጄ ያለበቂ ምክንያት በተማሪዎች ፊት እጁ በካቴና የፊጥኝ በመታሰሩ በጣሙን አዝኛለሁ። ይህ አይነቱ ድርጊት እኔ በማወቀው አሜሪካ መሬት ላይ ይካሄዳል ብዩ በፍጹም አልጠብቅም። ይሁን እንጂ ህዝቡ ከጎናችን በመቆሙ በጣሙን ተደሰተናል።ለጄ ጉብዘናውን ለ አለም ለማሳየት የሚጥር በሩህ አይምሮ ያለው ነው።” ብለዋል ። የወላጅ አባቱን ሞባይል ስልክ ፣መኪና ፣ ኮምፒውተር እና የመሳሰሉትን እንደነበሩ አደርጎ የሚጠግነው አህመድም “በራሴ ጥረት የሰራሁትን ሰአቴን ለአስተማሪዩ በማሳየት ላስገርማት ብሞክር በአስተማሬ ተጠርጣሪነት(የውሸት ቦምብ ነው ብላ በመሰጋቷ ) የተነሳ ለእስራት በመዳረጊ እጅጉን አዝኛለሁ።ከዚህ በሁዋላ በዚህ ትምህርት ቤ/ት መማር በጭራሽ አልፈልግም ት/ቤቱን ለቅቄ መሄድ እሻለሁ።” ብሏል። አህመድ በ አሁኑ ወቅት ከት/ቤቱ መታገዱም ታውቋል።

የአህመድ በ አራት ፖሊሶች በጥር ጣሪ ታስሮ ወደ ወጣቶች ጽባይ ማረሚያ/ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ የጣት አሻራ ሰጥቶ መለቀቅ በሺዎች የሚቆጠሩ የማህበራዊ ድህረ ገጾችን ያጨናነቀ እና ተከታዮችን ያስቆጣ ሲሆን ለአብነት ያህል ፕ/ት ባራክ ኦባማ በቲዊተር አካውንታቸው “ አህመድ ድንቅ ሰራ ነው የሰራሀው ። ይህን የለፋት ወጤትህን ወደ ዋይት ሃወስ(ቤተ መንግስታቸው ) ይዘሀው እንደትመጣ ትፈልጋለህ? ።በአንተ ትጋት ብዙ ታዳጊዎች በሳይንስ ትምህርት እንዲማረኩ ታደርጋለህ ። አሜሪካ ማለት የታላቅ ጥረት ውጤት አገር መሆኑን አስመሰክረሃል ።”በማለት ጥረቱን አወድሰውታል።የፕ/ት ኦባማ ቢሮም በበኩሉ እሮብ እለት ባወጣው መግለጫው በመጪው ጥቅምት 19 2015 እኤአ በቤተመንግስታቸው/ዋይት ሃውስ ውስጥ በሚደረገው የ ሰነ ኮዋክበት ባለሙያዋች ምሽት ላይ ታዳጊው አህመድ አዳሩን በክበር እንግድነት ከሳይነቲስቶች፣ ከኮዋክብት አጥኝዎች፣ ከኢንጅነሮች ከአስተማሪዎች እና ከተማሪዎች ጋር ኣንዲያሳልፍ ጋብዞታል ። የፊስ ቡክ መሰራቹ ወጣቱ ማርክ ዙኩር በርግ እንዲሁ በሰጠው አስተያየት “አህመድ ለሰራው ፈጠራ እስራት ሳይሆን ሽልማት ነበር የሚገባው ።ለማንኛውም የሚቸግርህ ነገር ካለ ወደ ፊስ ቡክ ጎራ በል፣ ላገኝህ እወዳለሁ ” ብሎታል ። ታዋቂዎቹ እነ ጉግል እና ቲዊተርም አህመድን “በርታ ከእኛ ጋር መሰራት ከፈለግህ በሩ ሁሌም ለአንተ ክፍት ነው”ሲሉ ጋብዘውታል ። አንዱ በር ሲዘጋ ሌላኛው ወለል በሎ ይከፈታል ነው ነገሩ።

Ahmed Mohamed by Tamru Geda 3አንዳንድ ወገኖች አህመድን ሰሙ እና ሃይማኖቱ ለጭፍን ተጠርጣሪነት እና ለእሰራት ሳይዳርገው እንዳልቀረ ይገምታሉ። ይሁን እንጂ ፖሊስ ግን ወቀስውን አሰተባብሏል ። “ከክስተቱ ብዙ ተምረናል ፣ክሱንም ወድቅ አድርገነዋል “ብሏል። አሜሪካዊው አህመድን ሰናሰብ በእኛም አገር ቢሆን ያለበቂ ማሰረጃ ለእሰራት እና ለመንጓጠጥ የሚዳረጉ ከታሰሩ በሁዋላለምን እና እንዲት እንደተፈቱ እንኳን የማያውቁ አያሌ ወገኖች መኖራቸውን አንዘንጋ። ቢያንስ ለእርምጃ አንቸኩል ፣ከሆነም ይቅርታ ለመጠየቅ አንዘግይ።

Filed in: Amharic