>

ኢትዮጵያ የተሻሉ አማራጮችን አጥታ ነውን ? [ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም]

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

Ethiopia 40እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 “ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የእራሱን ጥላ የሚፈራው ለምንድን ነው?“ በሚል ርዕስ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡

በዚያ ትችት ላይ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ደጋፊዎች የወያኔው አመራሮች በግንቦት ስለሚካሄደው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ተሸብበው የመገኘታውን እውነታ ሲነግሩኝ ለእኔ ይህ ሁኔታ በጣም እንቆቅልሽ እንደሆነብኝ ግልጽ አድርጌ ነበር፡፡ የተሰማኝን አግራሞት እንዲህ በማለት አቅርቤ ነበር፡

በወያኔው ጎራ ያሉ ደጋፊዎቻቸው ሚስጥር የሆነውን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን በፍርሀት ቆፈን ውስጥ መዘፈቅ ዝርዝር ጉዳይ ለእኔ የሚነግሩኝ ለምንድን ነው የሚል ጥያቄ አቅርቤ ነበር፡፡ ምናልባትም ለእኔ የተሳሳተ መረጃ ለመስጠት አስበው ሊሆን ይችላል በማለት ጠረጠርኩ፡፡ ሆኖም ግን እኔ የተሳሳተ መረጃ እንደማልወስድ እና እንደተሰላቸሁ አሳምረው ያውቃሉ፡፡ ታዲያ ነገሩ እንዲህ ከሆነ ለምንድን ነው እነዚህ የወያኔው ደጋፊዎች የድርጅታቸውን ፍርሀት ለእኔ በመንገሩ ጉዳይ ላይ ትኩረት በመስጠት ጥረት በማድረግ ላይ  የሚገኙት? እውነት ለመናገር ስለዚያ ጉዳይ የማውቀው ነገር የለም፣ ለማወቅም አልፈልግም፡፡

በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጎራ ውስጥ የመተረማመስ እና በጭንቀት አዘቅት ውስጥ የመዋለል ምልክት የሚስተዋል ይመስላል፡፡

አዲስ ፎርቹን/Addis Fortune የተባለው እና በኢትዮጵያ በሳምንት አንድ ጊዜ በርካታ ገጾችን በማካተት በእንግሊዝኛ ቋንቋ እየታተመ የሚወጣው ጋዜጣ እ.ኤ.አ መስከረም 7/2015 ባወጣው የህትመት አምዱ ላይ አንድ ስሜትን የሚስብ ጽሑፍ አስነብቧል፡፡

አዲስ ፎርቹን ጋዜጣን በየጊዜው በድረ ገጽ የግንኙነት መስመር ላይ እየተከታተልኩ አነባለሁ፡፡ በቀላሉ ለመገንዘብ በጣም አስቸጋሪ ከሆነው እና ከድብቁ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ልብ ውስጥ የሚገኝ መረጃን መሰረት በማድረግ የሚዘጋጅ መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም እንኳ አስተያየቶችን በማቅረብ ሌሎች ሰዎች ሀሳባቸውን እንዲገልጹ በሚያቀርባቸው ጽሁፎች እና ትንታኔዎች ላይ ማታለልን ባስወገደ መልኩ ጥሩ መረጃዎችን የሚሰጥ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ የአዲስ ፎርቹን ትንታኔዎች አብዛኛውን ጊዜ በአመክንዮ ላይ የተመሰረቱ እና አሳማኝ ትንታኔዎች የሚቀርቡበት ሲሆን አጠቃላይ የጋዜጣው ውስጣዊ ይዘት ሲገመገም ደግሞ በጋዜጣው ህትመት ላይ ግልጽ ምርመራን ከማድረግ ጀምሮ ምክንያታዊ ያልሆነ ተቃውሞን እስከማራመድ ይደርሳል፡፡ ስለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሸፍጥ፣ ህገወጥነት እና እምነተቢስነት ጉዳይ ሲነሳ ግን አዲስ ፎርቹን አብዛኛውን ጊዜ ከገንዘብ ጉዳይ ጋር ብቻ የሚቆራኝ ይመስላል፡፡

ይህንን ትችት ለመጻፍ እ.ኤ.አ መስከረም 7/2015 በወጣው የአዲስ ፎርቹን ጋዜጣ የመጨረሻው ዓምድ እንዲህ በሚለው ዓረፍተ ነገር ላይ እወሰናለሁ (የበለጠ ግልጽ ለማድረግ እታቀባለሁ)፡

በኃይለማርያም ደሳለኝ አመራር ሰጭነት ኢህአዴጎች ከአብዮታዊ ዴሞክራትነት እራሳቸውን ባገለሉ ቁልፍ ደጋፊዎች ዓይን እንደገና ተቀባይነትን ለማግኘት እና ሀሜትን በማራገብ የተሻሉ አማራጭ ዕድሎችን ካመከኑት አባላት ጋር ተቀራርቦ በመስራት የፓርቲውን የቀድሞውን ዝና ለመመለስ በተግባር ከመስራት ሌላ አማራጭ የለም፡፡ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

የአዲስ ፎርቹን ጋዜጣ አምድ ግልጽ ባልሆነ መረጃ ሰጭነት “ሀሜት” (አቶ/ወይዘሪት ሀሜት የሚለው ምን ለማለት እንደተፈለገ ግልጽ ባይሆንም) የሚለውን በመጠቀም አሁንም ቢሆን ኢህአዴግ ምንም ዓይነት ብልህነት የተላበሰ ነገርን መሰረት አድርጎ እንደማይሰራ እና በጭፍን ጥላቻ ላይ ተንጠልጥሎ የሚገኝ ድርጅት መሆኑን የሚያመላክት ነገር ነው፡፡

(ኢህአዴግ የሚለው ቃል እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ እያለ የሚጠራው ወሮበላ የዘራፊ እና የማፊያ ቡድን ስብስብ በዚህ የይስሙላ ስብስብ ውስጥ አድራጊ ፈጣሪ መሆኑን በአደባባይ ከኢትዮጵያ እና ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለመደበቅ እና እውነተኛ የብዙ ብሄረሰቦችን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ፍላጎቶችን እና ጥቅሞችን ለማስጠበቅ የተቋቋመ ጥምረት በማስመሰል ለማታለያነት የሰጠው የሸፍጥ የፖለቲካ የታዕይታ መድረከ ስያሜ ነው፡፡ እስቲ የጅቦችን ጥምረት ከበግ ጠቦቶች ጋር አስቡ፡፡

እንደ አቶ/ወይዘሪት ሀሜት፡

በቅርቡ በኢህአዴጎች በመቀሌ ከተማ በተካሄደው ጉባኤ ላይ በጥምረቱ ከተራ የገበሬ ካድሬ እስከ ከፍተኛ ልምድ እስካለው ነባር አመራር፣ ከወጣትነት ደረጃ ካሉት እስከ አረጋዊ ነባር የፓርቲው አባላት ድረስ በአንድነት በመሆን ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ አደጋ ውስጥ እንደሚገኝ እና ለህልውናው አስጊ ደረጃ ላይ እንደደረሰ በዓለም አብዮታዊ ዴሞክራቶች አንድ ነገር መወሰን እንዳለበት ስምምነት አድርገው ነበር፡፡

አብዛኞቹ አባላቱ በአሁኑ ጊዜ ፓርቲው ከፍተኛ የሆነ አደጋ ተደቅኖበት በሞት አፋፍ ላይ ቆሞ እንደሚገኝ በግልጽ የተናገሩ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ግልጽ በሆነ መልኩ የትኛውም መስዋዕትነት ተከፍሎም ቢሆን ስልጣንን ጨምድዶ መያዝ እንዳለበት በይፋ ተናግረዋል፡፡ እንደዚሁም ሌሎቹ ደግሞ ፓርቲው እንደገና እንዲያገግም ለማድረግ መከተል ስላለበት መንገድ ተናግረዋል፡፡ በአመራሩ ጸድቆ ለጉባኤው በቀረበው የአፈጻጸም ዘገባ ባልተለመደ ሁኔታ ስለሚመጣው የማገገም ሁኔታ ፍርሀት እና ስጋቶች የተንጸባረቁ መሆናቸው ተስተውሏል፡፡ አንጋፋዎቹ እና ለበርካታ ዓመታት አገልግሎት የሰጡት አመራሮች ከዓባይ ጸሐየ እስከ አዲሱ ለገሰ ድረስ ያሉት እራሳቸውን አግልለው ከምንም ነገር ተሳትፎ ታቅበው ታይተዋል…

ሆኖም ግን በፓርቲው ላይ ስለተደቀነው አደጋ የፓርቲው መስራች እና የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ነባር አመራር እንደ በረከት ስምኦን ደስታ የራቀው እና እውነታውን በግልጽ የተናገረ ማንም ያለ አይመስልም ነበር…ከ30 ዓመታት በላይ የአመራር ሰጭነት በኋላ የሁለቱንም መድረኮች የመሪነት ሚና ያጣው በረከት ስምኦን ብአዴን በቅርቡ በባህርዳር ከተማ አካሂዶት በነበረው ጉባኤ ላይ የተሰማውን ጭንቀት በግልጽ ተናግሮ ነበር፡፡ ፓርቲው እየተጓዘበት ባለው መንገድ ላይ ጠንካራ የሆነ ትችት አቅርቦ ነበር…ድርጅቱ እ.ኤ.አ ከተቋቋመበት ከ1980ዎቹ ሁለተኛ አጋማሽ ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢህአዴግ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ መቀሌ አልሄደም ነበር…ይህ ክስተት በርካታዎቹን የብአዴንን ተራ አባላት ልብ የሰበረ ነበር…

በፖለቲካ ክርክሩ ላይ የነበረው ዋናው የመከራከሪያ ነጥብ ፓርቲው መልካም አስተዳደርን፣ የሕግ የበላይነትን እና የጋራ ብልጽግናን አሰፍናለሁ ብሎ ገብቶበት የነበረውን ቃል ማክበር አለመቻሉ ነበር… በአብዮታዊ ዴሞክራቶች ላይ የህጋዊነት ምንጭ አለ ከተባለ ዋናው ስኬታችን ነው ብለው ሌት ከቀን እንደ በቀቀን የሚለፈልፉት ህዝቡን መግዛታቸው እና በምጣኔ ሀብት ዘርፉ እድገትን በማስመዝገብ ሀገሪቱ የተረጋጋች እና ጸጥታዋ የተረጋጋ ነው በሚለው ላይ ነው…

በሀሜቱ ጎራ ላይ ላሉት ደግሞ በተጻጻራሪው መልኩ አስገራሚ የሆነው ነገር የእራሱን የፖለቲካ ተቀናቃኞች በእግሩ ስር ተንበርክከው ይቅርታ እንዲለምኑት እና ተማኝነታቸውን እንዲገልጹለት የሚፈልገው አምባገነን ድርጅት በኡሁኑ ጊዜ በህዝቡ ላይ ተመሳሳዩን ድርጊት ለመፈጸም ስምምነት አድርጓል፡፡ በቅርብ ጊዜ ውስጥ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ስብሰባ በማድረግ መቀሌ ላይ ተደርጎ በነበረው ጉባኤ ላይ በተራ አባሎቹ ተነግሮ ስለነበረው ሀሜት ውይይት በማድረግ የህዝቡን ቁጣ እና ተስፋ መቁረጥ ዘለቄታዊ ባለው መንገድ ለመፍታት አሳውቋል፡፡

አስገራሚ በሆነ መልኩ ደግሞ የእነርሱ ጠንካራ ደጋፊዎች እንኳ ድርጅቱ በህዝቡ ላይ የሚሰራውን ስህተት በማረም ለመልካም ነገር የገባውን ቃል አጥፏል በማለት ሰጥተውት የነበረውን ዕውቅና በመንሳት በሀሜት ተግባራት ላይ ተጠምደው የመገኘታቸው ጉዳይ ነው፡፡

በኃይለማርያም ደሳለኝ አመራር ሰጭነት ኢህአዴጎች ከአብዮታዊ ዴሞክራትነት እራሳቸውን ባገለሉ ቁልፍ ደጋፊዎች ዓይን እንደገና ተቀባይነትን ለማግኘት እና ሀሜትን በማራገብ የተሻሉ አማራጭ ዕድሎችን ካመከኑት አባላት ጋር ተቀራርቦ በመስራት የፓርቲውን የቀድሞውን ዝና ለመመለስ በተግባር ከመስራት ሌላ አማራጭ የለም፡፡ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

“ለሀሜቱ” አዲስ ፎርቹንን እንኳን ደስ ያለህ ለማለት እፈልጋለሁ፡፡

ጆናታን ስዊፍት (የ”ጉሊቨር ተጓዦች” ደራሲ  ) እንዲህ ብለው ነበር፣ “ትንሿ ወፍ ስትናገር ሰምቻለሁ፡፡“ እንደዚሁም አቶ/ወይዘሪት ሀሜት/ሙስናም ትናገራለች፡፡

ሆኖም ግን አዲስ ፎርቱን ትንንሽ ወፎችን እና ከንግግሮች ምን ያህል ሀሜቶችን ማውጣት እንደሚችሉ አሳምረው የሚገነዘቡ ሀሜተኞችን እንዴት እንደሚጠቀም ያውቃል፡፡

ዋናው ነጥብ ከአዲስ ፎርቹን ጋዜጣ አምድ ሊያወያዩ የሚችሉ በርካታ ነገሮች አሉ፡፡

እውነት ለመናገር ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ “የተሻለ አማራጭ” ጥያቄ በቃላት እንጅ በተግባር የማይገለጸው ባዶ ዲስኩር እ.ኤ.አ በ2005 ተካሂዶ የነበረውን የኢትዮጵያ የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ተከትሎ ተፈጥሮ በነበረው ውዝግብ አሁን በህይወት የሌለው መለስ በእራሱ ትዕዛዝ ምርጫው መዘረፉን በማስመልከት ተቃሟቸውን በሰላማዊ መንገድ ወደ አደባባይ በመውጣት ለመግለጽ በተንቀሳቀሱት ወገኖቻችን ላይ እልቂት እንዲፈጸም ካደረገበት እና እኔም በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጥበቃ ትግል ከጀመርኩበት ጊዜ ጀምሮ የምሰማው አደንቋሪ ጩኸት ነው፡፡

አሁን በህይወት በሌለው በመለስ ዜናዊ ልዩ ትዕዛዝ 200 መሳሪያ ያልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች እንዲያልቁ እና ከ800 በላይ የሚሆኑትን ሌሎችን ደግሞ ለመግደል በዕቅድ ተይዞ እንደነበር  በአስተማማኝ መረጃ ላይ በተመሰረተ እና ከምንም ጥርጣሬ በላይ ያረጋገጥኩ በመሆኑ በወገኖቸ ላይ በተፈጸመው ዘግናኝ እና ጭካኔ የተመላበት አረመኒያዊ የግድያ ዕልቂት ምክንያት በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እና በመለስ ላይ ጥብቅና ከፍተኛ  ተቃውሞ እንዳለኝ አንባቢዎቼ በሙሉ ያስታውሱታል የሚል እምነት አለኝ፡፡

በመለስ ትዕዛዝ በወገኖቻችን እልቂት ላይ ሙሉ ተሳትፎ ያደረጉ እና በመረጃ የተረጋገጠ 237 ነፍሰ ገዳይ ወሮበሎች የስም ዝርዝር ተይዞ ይገኛል፡፡ በአንድ ወቅት ምናልባትም በቅርብ ጊዜ ለፍትህ እንደሚቀርቡም የሚያጠያይቅ ጉዳይ አይደለም፡፡

የተሻሉ አማራጮች እጥረት ጥያቄ፣

የተሻሉ አማራጮች ሲባል ምን ማለት ነው?

የአዲስ ፎርቹን ትንሿ ወፍ የኢህአዴግን ዋና ደጋፊዎች መንገዳቸውን በመሳት ወደተሳሳተ አቅጣጫ መጓዛቸውን ትገልጻለች፡፡

የኢህአዴግ ዋና ደጋፊዎች የተሻሉ አማራጮችን እየፈለጉ ቢሆንም ቅሉ እስከ አሁን ድረስ የተሻሉ አማራጮችን አላገኙምን?

ምን ዓይነት ልዩ የሆነ ምልከታ ነው!!

የተሻሉ አማራጮች እጥረት የሚለው የኢህአዴግ ትርጉም “ንጉሱ ልብስ ሳይለብስ ራቁቱን ነው” ከሚለው አባባል ጋር አንድ ነውን?

ልብስ ሳይለብስ መለመላ እራቁቱን የሆነው የኢህአዴግ ዋና ገዥ የሆነው ንጉስ ህወሀት ነውን (ንጉስ አንጋሽ አላልኩም)?

የአዲስ ፎርቹን ትንሿ ወፍ ስለምንድን የተሻሉ አመራጮች እየተናጋረች እንደሆነ በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር የለም፡፡

ሆኖም ግን ስለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የተሻሉ አማራጮች ጉዳይ እንዲህ የሚሉ በርካታ ጥያቄዎች በጭንቅላቴ ውስጥ ይመላለሳሉ፡

የጫካ ወሮበሎች እና ምንም ዓይነት መሳሪያ ያልያዙ ሰላማዊ ሰልፈኞችን በጠራራ ጸሐይ በአደባባይ በመፍጀት ብቻ ሳይሆን ተቀናቃኞቻቸውን ሁሉ ስልታዊ በሆነ መልክ በመግደል ስልጣናቸውን የሙጥኝ ብለው ስለሚገኙበት የተሻለ አማራጭ ነው እየተነጋገርን ያለነው?

የጫካ ወሮበሎች እና ሙጥጥ ጥርግ አድርገው አጥንቷ እኪቀር ስለዘረፉባት ኢትዮጵያ የተሻለ አማራጭ ነው እየተነጋገርን ያለነው? እ.ኤ.አ በ2011 ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ/Global Financial Integrity የተባለው ዓለም አቀፍ ተቋም እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቦ ነበር፣ “ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ከ2000 እስከ 2009 ባሉት ዓመታት ውስጥ ብቻ 11.7 ቢሊዮን ዶላር በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ምክንያት አጥታለች፡፡“

በኢትዮጵያ ቋንቋን እና ዘርን መሰረት ባደረገው በጎጥ እና በክልል የዘረኛ እና የአንድ ቡድን ወሮበላ የበላይነትን ስላሰፈነው የጫካ ወሮበሎች የሙስና አገዛዝ የተሻለ አማራጭ ነው እየተነጋገርን ያለነው? የዓለም ባንክ “በኢትዮጵያ ሙስናን መመርመር“ በሚል ርዕስ ባለ417 ገጽ ዘገባ አቅሮቦ ነበር፣ የዓለም ባንክ ሙስናን በሚመለከት እስከ አሁን ድረስ ባለው ተሞክሮው ይህን ያህል ጥልቀት እና ስፋት ያለው የሙስና ግምገማ በየትኛውም ሀገር አዘጋጅቶ አያውቅም!!!

እ.ኤ.አ በ2010 99.6 በመቶ እ.ኤ.አ ግንቦት በ2015 ደግሞ ለስሙ እንኳ አንድም የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ሳያስገባ 100 በመቶ የፓርላማ ወንበሮችን በቁጥጥሩ ስር ስላዋለው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የተሻለ አማራጭ ነው እየተነጋገርን ያለነው?

በእርግጥ የአንድን ሀገር ህልውና ከደፈረ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ውጭ ሌሎች በርካታ የተሻሉ አማራጮች አሉ፡፡

ሁሉም ነገር ቀላል ነው፡፡

ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የደቦ አመራር በምስል እንቅስቃሴ/ሲኒማ /ሙቪ ኢንዱስትሪው ታዋቂ የሆኑትን ለምሳሌ ያህል በመጥቀስ የተሻሉ አማራጮችን በሚከተለው መልኩ ለመጠቆም እችላለሁ፡

ዊሌ ኢ. ኮዮቴ (አሁን በህይወት የሌለውን መለስ ዜናዊን የሚወክል)፣ ሚኬይ ማውስ (ኃይለማርያም ደሳለኝን የሚወክል)፣ ኦይል ካን ሀሬይ (ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤልን የሚወክል)፣ ፒኖክዖ (በረከት ስምኦንን (የውሸት ጎተራ ከሆነው ከኮሚኩ እና እንደ አቡጅዲ ይቀደድ የነበረውን የኢራቅ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረውን ኬሚካል ዓሊን የሚወክል)፣ ኪንግ ሌዊ (ስብሀት ነጋን የሚወክል)፣ ፓትሪክ ስታር (ቴዎድሮስ አድሀኖምን የሚወክል)፣ ዮሴሚቴ ሳም (ዓባይ ወልዱን የሚወክል)፣ ዱፈስ ድሬክ (ደመቀ መኮንንን የሚወክል)፣ ክሩኢላ ዴቪል (አዜብ መስፍንን የሚወክል)፣ ባሉ (ሙላቱ ተሾመን የሚወክል)፣ ዶን ካርኔጅ (አርከበ እቁባይን የሚወክል)፣ ሲልቨስተር ዘ ካት (ዓባይ ጸሐየን የሚወክል)፣ ፎግሆርን ሌግሆርን (ሳሞራ ዩኑስን የሚወክል)፣ ጉፊ (አባዱላ ገመዳን የሚወክል)፣ ፖርኪ ፒግ (ግርማ ወልደጊዮርጊስን የሚወክል)፣ ኢልመር ቲ.ፉድ (አዲሱ ለገሰን የሚወክል)፣ በግስ በኒ (ስዩም መስፍንን የሚወክል)፣ ስፒዲ ጎንዛለዝ (ሬድዋን ሁሴንን የሚወክል)፣ ድሩፒ (አባዲ ዘሞን የሚወክል)፣ ፔፔ ሌ ፒው (ጸጋይ በርኸን የሚወክል)፣ ወዘተ፡፡

ሆኖም ግን የአዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ትንሿ ወፍ ስለተሻሉ አማራጮች የምትናገር ከሆነ ስለበርካታ ተግባራዊ የፖለቲካ አማራጮች ጥልቀት ያለው ትንታኔ መስጠት አስፈላጊ የሚሆንባቸው በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡

ተግባራዊ የፖለቲካ አማራጮች ስንል “ልማታዊ መንግስት” ማለታችን ነውን?

የተሻሉ የፖለቲካ አማራጮች ስንል በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ፕሮግራም ውስጥ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ አስተዳደርን ማስፈን ማለታችን ነውን?

የተሻሉ የፖለቲካ አማራጮች ስንል የተቃዋሚ ቡድኖች ህብረት በመፍጠር ኢትዮጵያን ከጥፋት/ምጽዓት ቀን ለማዳን የሚያቋቁሙት መንግስት ማለት ነውን?

የተሻሉ የፖለቲካ አማራጮች ስንል ዘርን መሰረት ያላደረገ መንግስት ማቋቋም ማለት ነውን?

የተሻሉ የፖለቲካ አማራጮች ስንል በኢትዮጵያ የለማኝ መንግስት ማቋቋም ማለት ነውን?

የተሻሉ የፖለቲካ አማራጮች ስንል በኢትዮጵያ በሕግ የበላይነት፣ በተጠያቂነት እና ግልጸኝነት ላይ መሰረት ያደረገ መንግስት ይቋቋም ማለታችን ነውን?

የተሻሉ የፖለቲካ አማራጮች ስንል በስደት ላይ ያለ መንግስት ማለታችን ነውን?

ልማታዊ መንግስት፡ ልማታዊ መንግስት ማለት ምን ማለት ነው? የማልማት አቅም በሌለው መንግስት የመልማት አቅም ለሌላቸው ህዝቦች የቆመ መንግስት ማለት ነውን?

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች ጤነኛ አስተሳሰብን በሚያውኩ እንደ ጥላቻ፣ እውነታን አዛብቶ የመመልከት አስተሳሰብ፣ በህልም ቅዠት (እነርሱ ነገሩን አዙረው ራዕይ ይሉታል)፣ ምናባዊ/ባዶ ሀሳባዊነት፣ ቁጣ በተቀላቀለባቸው የአስተዳደር ጉዳዮች፣ የጽንፈኝነት ስርዓተ አልበኝነት ችግር፣ በመሳሰሉት ዕኩይ ምግባሮች ላይ ተተብትበው ይገኛሉ፡፡

አሁን በህይወት የሌለው እና በኢትዮጵያ የልማታዊ መንግስት ቀማሪ ዋና መሀንዲስ አስመሳይ ምሁራዊ ሽፋን የተንጸባረቀበት፣ የማይሻሻል ዶግማ እና እውነት የሚያስመስል ባህሪን ተላብሶ ሲታልል በቆየው በመለስ ዜናዊ በተዘጋጀው ባለ51 ገጽ ጽሑፍ ሰነድ (ከዚህ ሰነድ ምንም ዓይነት ነገር እንዳይጠቀስ ማስጠንቀቂያ የተሰጠበት) እንዲህ የሚል የመከራከሪያ ጭብጡን አቅርቧል፣ “ልማት የፖለቲካ ሂደት ቀዳሚ ጉዳይ ነው፣ እናም የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ልማቱ ከፖለቲካው በኋላ በቀጣይነት የሚመጣ ነው፡፡ የልማት ኳሷ እንድትሽከረከር እና ልማትን ሊያፋጥን የሚያስችል ከባቢ አየር ለመፍጠር እንዲቻል መጀመሪያ የፖለቲካ ምህዳሩ መዋቀር አለበት፡፡ የልማታዊ መንግስት ባህሪያት ያሉት መንግስት ካለ ብቻ ነው ስለኪራይ ሰብሳቢነት መወያየት እና ትርጉም ባለው ሁኔታም ማስወገድ የሚቻለው፡፡“

የቱንም ያህል ፍሬከርስኪ ትርጉም ቢሰጠውም ቅሉ ልማታዊ መንግስት የማታለያ ዕቅዱን በማዘጋጀት የቻይናን ሞዴል በመከተል በሚል ስውር ደባ የአፍሪካ አምባገነኖች ኩባንያዎች የመጨረሻ ግባቸው ለመሆን በቅቷል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ልማታዊ መንግስት ግልጸኝትን እና የተጠያቂነት አስተዳደርን፣ ነጻ ውደድርን፣ ነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫዎችን እና ሀሳብን በነጻ የመግለጽን እና የነጻውን ፕሬስ ለማኮላሸት የሚጠቀምበት ማደናገሪያ ዘዴው ነው፡፡ በህዝቡ ላይ ፍጹም የሆነ ቁጥጥር የማድረግ ዓላማን የያዘ እና በአጠቃላይ የፖለቲካ ታዛዥነትን ለማንገስ፣ ሁሉንም ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች በእንጭጫቸው ለመቅጨት እና የወያኔውን የሙስና እና የዘረፋ ከፋፍለህ ግዛ ጠቅላይ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ስርዓት ለመመስረት የተዘየደ የማታለያ ስልት ነው፡፡

የብዙሀን ፓርቲ ስርዓት ልማታዊ አቅም ለሌለው እና ለተሽመደመደው መንግስታዊ አመራር ፍቱን ተመራጭ ስርዓት ነው፡፡

በውል ተጠንቶ የተዘጋጀ የፖለለቲካ ፍልስፍና እና ፕሮግራምን መሰረት ያደረጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፡ በርካታ የፓርቲ ፕሮግራሞች አሉ፡፡ የቅንጅትን ፕሮግራም/ማኒፌስቶ አንብቢያለሁ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲን ፕሮግራም አንብቢያለሁ፡፡ የአንድነት ፓርቲን ፕሮግራም አንብቢያለሁ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የኢህአዴግን እና የሌሎችን የበርካታዎችንም አንብቢያለሁ፡፡

ሰፊ መሰረት ያላቸው ዓላማዎች እና መግለጫዎች፣ የመልካም አስተዳደር ቃልኪዳኖች እና ሰብአዊ መብትን ለማክበር የሚገቡ ቃል ኪዳኖች እጅግ ታላቅ ነገሮች ናቸው፣ ሆኖም ግን እንደዚህ በማለት ብቻ ለእውነተኞቹ የተግባር ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ መስጠት ይቻላልን?

ለምሳሌ ያህል ፓርቲዎች የጎሳ ፌዴሪያሊዝም የሚባለውን ሰይጣን እንዴት አድርገው ነው ሊቋቋሙት እና ሊያስወግዱት የሚችሉት?

በአንድ ላይ ህብረት በመፍጠር ሁሉም ተባብሮ እግሩን አንሰራፍቶ ተቀምጦ የሚገኘውን የጎሳ ፌዴሪያሊዝም ቀንዳም ሰይጣን ከተቀደሰችዋ የኢትዮጵያ ምድር ላይ ለዘላለም ሊያንሰራራ በማይችልበት መልኩ ተጠራርጎ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ መወገድ አለበት እላለሁ!

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ይቅርታ ኤህአዴግ ማለቴ ነው) የጎሳ ፌዴሪያሊዝም በማለት እራሱ የፈጠረው ዘንዶ ስርዓት እራሰን ሊውጠው አፉን ከፍቶ እያዛጋ መሆኑን በውል ተገንዝቦታል፡፡

ከጥቂት ቀናት በፊት የይስሙላው እና አሻንጉሊቱ የወያኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው ኃይለማርያም ደሳለኝ እርዳታ እድርጉልኝ በማለት ጩኸቱን አሰምቷል፡፡

የጥላቻ መርከቡ እየሰመጠ መሆኑን የሚያስገነዝብ መልዕክት ነበር ያስተላለፈው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የጥላቻ መርከብ እየሰመጠ ነውን…? በማለት በመገረም ጥያቄዬን አቀረብኩ፡፡

የተቃዋሚ ፓርቲዎች ህብረት፡ አሁን የዚህ ሀሳብ ጊዜው እየመጣ እና እየደረሰ ነው፡፡ እንደገና ሀሳቡን አጥኖ ወደ ህብረት ምስረታ መመለስ ያስፈልጋል፡፡

የተቃዋሚ ፓርቲዎች ህብረት ምስረታ ስኬትን ሊያጎናጽፍ እንደሚያስችል ቀደም ሲል ተረጋግጧል፡፡ እ.ኤ.አ ግንቦት 2005 ቅንጅት (የ4 የፖለቲካ ፓርቲዎች ህብረት) የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን በህዝብ የምርጫ ድምጽ አፈር ድሜ አብልቶት ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ ቅንጅት በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከ138 ወንበሮች 137ቱን በዝረራ አሸንፎ ነበር፡፡

አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ የቅንጅት አመራሮችን ትምህርት ለማስተማር ፈለገ፡፡ ሁሉንም ሰብስቦ በማጎሪያው እስር ቤት ውስጥ ከተታቸው፡፡ ያ ድርጊት የዚያን ህብረት ህልውና እስከ መጨረሻው እንዲያከትም አደረገው፡፡

የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአሁኑ ጊዜ ህብረት የማይፈጥሩት እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት የማይታገሉት ለምንድን ነው?

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እ.ኤ.አ በ2005 በዝረራ ከተሸነፈ በኋላ የተንኮል እና የማጭበርበር ዕኩይ ምግባር ማራመዱን ቀጠለ፡፡

እባብ ያዬ በልጥ በረዬ ወይም ደግሞ ያበራሽን ጠባሳ ያየ በእሳት አይጫወትም እንዲሉ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ምንም ዓይነት የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህብረት እንዳይፈጠር እና ከተፈጠረም እንዲኮላሽ ሌት ከቀን አብርትቶ ይሰራ ጀመር፡፡ ያንን ሊያኮላሹ የሚችሉ አዲስ ለስርዓቱ ተገዥ የሚሆኑ ተለጣፊ ህብረቶች እንዲመሰረቱ ያደርጋሉ፡፡ ያ ባይሰራ እና ህብረቱ ቢፈጠርም እንኳ አመራሩን እና አባላቱን የማስፈራራት፣ የማሸማቀቅ፣ በይስሙላው የዝንጀሮ ፍርድ ቤት የአሸባሪነት የፍብረካ ክስ እየተመሰረተ የማሰቃዬት እና በእስር ቤት እያስገቡ የማማቀቅ ስልትን መተግበር ጀመሩ፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በእርሱ የዕይታ አድማስ ስር ምንም ዓይነት የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህብረት እንዲፈጠር አይፈቅድም፡፡

የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህብረት መመስረት የኢትዮጵያን ህዝብ ለነጻነቱ የሚያበቃው ፍቱን መድኃኒት እንደሆነ ጥያቄ የሚቀርብበት ጉዳይ አይደለም፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የማታለል ስልት እና ሸፍጥ እስካለ ድረስ አሁንም ቢሆን የተቃዋሚ ፓርቲዎች ህብረትን መመስረት ይቻላልን?

የተቃዋሚ የዴሞክራሲ ኃይሎች የተባበረ ህብረት፡ በበርካታ ሀገሮች የዴሞክራሲ ኃይሎች በአምባገነኖች ላይ የተባበረ ጡንቻቸውን ለማሳረፍ በማሰብ ህብረት ይፈጥራሉ፡፡

በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጎራ ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም በማሳተፍ የጋራ የሆነ የመግባቢያ ፕሮግራም በመንደፍ አጠቃላይ ህብረት በመፍጠር አንድ በመሆን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን መገዳደር ይችላሉ፡፡

የተባበረው የተቃዋሚ ኃይል ከልብ በመወያየት የሽግግር መንግስት ማቋቋም ይችላል፡፡

እንደ ታሪክ ማስታዋሻነት ብንወስደው እ.ኤ.አ በ1991 የሸፍጥ ድርጅቱን ኢህአዴግ በሚል የማስመሰያ ስም ሆኖም ግን አድራጊ ፈጣሪው እና አመራር ሰጭው እራሱ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሆኖ የአምባገነኑን ወታደራዊ መንግስት ለመተካት የይስሙላ ህብረት ፈጥሯል፡፡ ይህንን አሻንጉሊት የይስሙላ ህብረት እስከ አሁንም ድረስ እየተጠቀመ የኢትዮጵያን ህዝቦች ነጻነት ገፍፎ በመግዛት እና ኢኮኖሚውን በብቸኝነት በመቆጣጠር በመመዝበር ላይ ይገኛል፡፡ በዚያን ወቅት የተኩስ አቁም ስምምነትን በመፈረም ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎችን (በኋላ እነርሱ የማይፈልጓቸውን የተለያዩ ምክንያቶችን እየፈጠሩ እንዳይሳተፉ ቢያደርጉም) እንዲሳተፉ በማድረግ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም አድርገው ነበር፡፡

በእርግጥ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እያንዳንዱን ሰው እያታለለ፣ እያሞኘ እና እያጭበረበረ በስልጣን ላይ የሙጥኝ ብሎ ቆይቷል፡፡ በዚህም የሸፍጥ ድርጊት እየተመሩ እ.ኤ.አ ከ1991 ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጥጠው ይገኛሉ፡፡

ለዘራፊ ወሮበላ የዘራፊ ብድን ስብስብ የማፊያ መንግስት የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ህብረት መመስረት ተመራጭ እና ፍቱን መድኃኒት ነው፡፡

ለማኝ መንግስት በኢትዮጵያ፡ ከአንድ ዓመት በፊት “ለማኝ መንግስት” የሚለውን ጽንሰ ሀሳብ በማገናኘት አገዛዞች እና መንግስታት ዓለም አቀፍ እርዳታን (እርዳታ + ብድር) በዋናነት በመሳሪያነት በመጠቀም በህዝብ ስም የሚመጣውን እርዳታ እና ብድር እንዴት አድርገው እንደሚዘርፉት እና እያጭበረበሩ ለግል ጥቅማቸው እንደሚያውሉት እና በስልጣን ላይ ለመቆየት ጥረት እንደሚያደርጉ (ለሕገወጥ ዓላማ ሕጋዊነትን የተላበሱ ድርጅቶችን እየተጠቀሙ) በርካታ የሙስና እና የዘረፋ ተግባራትን እንደሚፈጽሙ በዝርዝር ትንታኔ አቅርቤ ነበር፡፡

ቀደም ሲል ሳቀርበው እንደነበረው የክርክር ጭብጥ ሁሉ የአፍሪካ አምባገነኖች የመጨረሻ ደረጃ ወሮበላ ዘራፊነት እንደሆነ ግልጽ አድርጊያለሁ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ለማኝ መንግስት የፖለቲካ ስልጣኑን በመጠቀም በርካታ የአፍሪካ በሙስና የተዘፈቁ እና በዘር የተዋቀሩ መንግስታትን በማዋቀር የህዝቡን ንብረት ወደ ግል ይዞታ በማዛወር ሂደት እና የሀገሪቱን ሀብት ወደ ውጭ በህገወጥ የገንዝብ ዝውውር አማካይነት ከሀገር እንዲወጣ በማድረግ አፍሪካውያንን እስከ አጥንታቸው በመጋጥ የገዥው አባላት የህዝብን ሀብት ሙልጭ አድርገው በመዝረፍ የግል መጠቀሚያቸው በማድረግ ግላዊ የሀብት መድለብን እንደሚፈጥሩ ትንታኔ አቅርቤ ነበር፡፡

በለማኝ መንግስት ላይ ህልቆ መሳፍርት የሌላቸው አማራጮች አሉ፡፡

ከጥቂት ሳምንታት በፊት የተባበሩት መንግስታት እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቦ ነበር፡

በተከሰተው የዝናብ እጥረት ምክንያት በዚህ ዓመት መጨረሻ የምግብ እርዳታ የሚፈልጉት ኢትዮጵያውያን ቁጥር ቀደም ሲል ከተተነበየው በ1.5 ሚሊዮን እንደሚበልጥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለፈው ሰኞ ግልጽ አድርጓል፡፡

በዚህ ዓመት እርዳታ ያስፈልገዋል ተብሎ ለተተነበየው 4.5 ሚሊዮን ህዝብ ኢትዮጵያ ከእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች 230 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ይፋ አድርጓል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከለጋሽ ድርጅቶች እርጥባን ለማግኘት አንድ ቀጥታ መንገድ አላቸው፡፡ ልመና፡፡ እባካችሁ ማለት!

በስደት ላይ ያለ መንግስት፡ ሌሎች ወገኖች ደግሞ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ላይ ሌላ በውጭ ሀገር በስደት ላይ የሚገኝ መንግስት አሁኑኑ ማቋቋም አስፈላጊ እና የተሻለ አማራጭ እንደሆነ አድርገው የሚናገሩ አሉ፡፡ በስደት ላይ የሚኖሩ እና በዓለም አቀፉ ሕግ እውቅና ያላቸው የበርካታ መንግስታት ምሳሌዎች አሉ፡፡ ዋና ሊነሳ የሚችለው ጥያቄ ለዓለም አቀፉ ሕግ መስፈርት መሟላት ያለባቸውን ጉዳዮች እንዴት በማድረግ ማሟላት ይቻላል የሚለው ነው፡፡ በስደት ላይ የሚገኝ መንግስት በእርግጠኝነት አንድ ሌላ የተሻለ አማራጭ መንገድ ነው፡፡

የሕግ የበላይነት ወይም የደናቁርት ሕግ፡ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች ስለሕግ የበላይነት መስበክ መጽሐፍ ቅዱስን ለአሕዛብ እንደመስበክ ወይም ደግሞ በጥቁሩ የባልጩት ድንጋይ ላይ ውኃ እንደማፍሰስ ነው፡፡ ይህንን ድርጊት መፈጸም ለምንም ነገር የማይጠቅም እርባና የሌለው ከንቱ ነገር ነው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሕገ መንግስት ሰነድ አለው፡፡ ሆኖም ግን በተግባር የማይፈትሹት ባዶ ሰነድ ነው፡፡ በአስቂኙ የጸረ ሽብር ሕጉ አንድን ግለሰብ ለመወንጀል እና የፍብረካ ክስ እንዲመሰረትበት ሲያስቡ ብቻ ነው ሰነዱን ማገላበጥ የሚፈልጉት፡፡

ዓይን ባወጣ መልኩ ሕገ መንግስቱን እና የወንጀል ተጠርጣሪ ዜጎችን ሰብአዊ መብት ወደ ጎን አሽቀንጥረው በመጣል የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች የእራሳቸውን ሕገ መንግስት የማያከብሩ አስፈሪ፣ ጥልቅ ድንቁርና እና ምንም ደንታ የሌላቸው መሆናቸውን ማንም ቢሆን ለመገንዘብ የሚያዳግተው አይደለም፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሕገ መንግስት አንቀጽ 20 ንኡስ አንቀጽ 3 የሚከተለውን መብት ያጎናጽፋል፡ “ማንም ቢሆን በፍርድ ቤት ጥፋተኝነቱ እስካልተረጋገጠ ድረስ ነጻ ነው፡፡“ የዞን 9 ወጣት ጦማሪያን በመገናኛ ድረ ገጽ ሀሳቦቻቸውን በመግለጻቸው ምክንያት ብቻ እ.ኤ.አ ከሚያዝያ 2014 ጀምሮ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤት የሸፍጥ ክስ ተመስርቶባቸው (33 ጊዜ የጅንጀሮ ፍርድ ቤት አየተመላለሱ ) በመሰቃየት ላይ ናቸው፡፡ በቅርቡ “ኢትዮጵያውያን ጦማሪዎች በዝንጀሮው ፍርድ ቤት“ በሚል ርዕስ ትችት በማቅረብ እየደረሰባቸው ያለውን ሕገ ወጥ ድርጊት አጋልጨ ነበር፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሕገ መንግስት አንቀጽ 19 ንኡስ አንቀጽ 5 የሚከተለውን መብት ያጎናጽፋል፡ “በወንጀል ተጠርጥሮ ጉዳዩ ለፍትህ አካል የቀረበ ማንም ቢሆን የግዳጅ የእምነት ቃል ማስረጃ እንዲሰጥ አይገደድም ወይም ደግሞ በግዳጅ የተገኘ የእምነት ቃል ማስረጃ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡“ እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ዘገባ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዜጎችን በወንጀል በመጠርጠር ከያዘ በኋላ የሸፍጥ የፍብረካ የውንጀላ ክስ በመመስረት የማሰቃየት ድርጊት በመፈጸም በግዳጅ የእምነት ቃል እንዲሰጡ ያደርጋል በማለት ይፋ አድርጓል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሕገ መንግስት አንቀጽ 21 ንኡስ አንቀጽ 2 የሚከተለውን መብት ያጎናጽፋል፡ “በወንጀል ተጠርጥሮ በሕግ ከለላ ጥላ በቁጥጥር ስር የዋለ ማንም ሰው የሕግ አማካሪ ጠበቃ የመወከል … እንዲሁም በጠበቃው አማካይነት ግንኙነት የማድረግ መብት አለው፡፡“ ዎቼ ጉድ፣ ድንቄም መብት! መጽደቁ ቀረና ባግባብ በኮነነኝ አለ!

እ.ኤ.አ ጥቅምት 2013 “የፖሊስ መንግስት የግዳጅ የእምነት ቃል“ በሚል ርዕስ በኢትዮጵያውያን ላይ ዓይን ያወጣ የፍትህ ስርዓት ጉድለት እየተፈጸመ እና መብቶቻቸው እየተረጋገጡ መሆናቸውን ግልጽ አድርጌ ነበር፡፡ ለደናቁርት ሕግ በርካታ የተሻሉ አማራጮች አሉ፡፡

የምጽዓት ቀን አማራጭ ዕድሎች፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኢትዮጵያ ከእርሱ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ውጭ ልትኖር አትችልም ይላል፡፡ ወያኔ ከሌለ ኢትዮጵያ በድንጋይ አለሎ እንደተመታ ብርጭቆ ስብርባሪ ብትንትን ትላለች ይላሉ፡፡ (በእርግጥ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የታሪክ ሰዎች ኢትዮጵያ የበርካታ ሺህ ዘመናት ህልውና ያላት መሆኗን አይገነዘቡትም፡፡ ኢትዮጵያ የተፈጠረችው ከ100 ዓመታት ወዲህ ነው የሚል የጠባብነት እና የድንቁርና የሸፍጥ እምነት አላቸው፡፡)

እ.ኤ.አ ሕዳር 2014 “የኢትዮጵያውያንን ኢትዮጵያዊነት ማጥፋት“ በሚል ርዕስ ትችት በማቅረብ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን የቅዠት ሀሳብ ግልጽ አድርጌ ነበር፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኢትዮጵያ ከወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የልማት ጥረት ውጭ አደጋ ውስጥ በመግባት ትጠፋለች እናም ወደ ድህነት ትመለሳለች ይላሉ፡፡

(የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለታሪክ መዝገብ ሲል እንኳ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2014 ሁለተኛው አጋማሽ በዓለም ከሚገኙ ሀገሮች ሁሉ በድህነት ከመጨረሻዎቹ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ መሆኗን በምንም ዓይነት መልኩ በፍጹም በፍጹም ትንፍሽ ብሎ አያውቅም!)

ነገር እና ቅጥፈት አያልቅብሹ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በአፍሪካ ቀንድ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከሌለ ሰማይ እና ምድር ይገለባበጣል፣ እንደዚሁም ምስራቅ አፍሪካ ህንድ ውቅያኖስ ውስጥ ይሰጥማል ይላል፡፡

በቀላሉ አነጋገር ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የኢትዮጵያን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በኃላፊነት መስጠት ማለት አንድ ዝንጣፊ ሙሉ ሙዝ በኃላፊነት እንዲጠብቁት ለጦጣዎች/ዝንጀሮዎች  ስብስብ (በዝንጀሮው ፍርድ ቤት ያሉትን ሳይሆን) እንደመስጠት ማለት ነው፡፡

ይቀጥላል…

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

መስከረም 4 ቀን 2008 ዓ.ም 

Filed in: Amharic