>

'' መፍትሄው ቆራጥ አመራርን የሚጠይቅ ነው'' [ኣቶ ተመስገን ዘውዴ የቀድሞው የፓርላማ ኣባል]

በቅርቡ ስለ መልካም አስተዳደር በገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ተጠንቶ ጠ/ሚኒስቴሩ በመሩት ስብስባ ላይ የተካሄዴው ውይይት የሚያበረታታ ነው።

ገዥው ፓርቲ ህዝቡ ለ25 አመት ያወቀውን በጥናትና ምርምር ማግኘቱ ቢዘገይም ወደ መፍትሔ ፍለጋ ሊያመራው ስለሚችል እስየው የሚያስብል ነው።
Ato Temesgen Zewdeእኔ ግን በየመስሪያ ቤቱ ጉዳይ አስፈጻሚ ነን በማለት ከባለስልጣናት ጋር በሚልዬን ብር ሙስና የሚያንቀሳቅሱ ደላላዎች ማንነትን አስመልክቶ ጠ/ሚኒስትሩ ግር ያላቸው ይመስላል።

እነዚህ ደላላዎች ባብዛኛው የዛሬ 25 አመት ገደማ “ነጻ” ሊያወጡን ከተማ የገቡት የእህአዴግ ባለስልጣናትና፣ የጦር መኮንኖች፣

1. ልጆች
2. ወንድም/እህት/ሚስት/ጋደኛ
3. ዘመድ…..ወዘተ
4. ሌሎች እነዚህን “ነጻ” አውጪዎች በአሽከርነት የሚያገለግሉ ጥገኞች ናችው።

ለረጋግጥልዎ የምፈልገው በሙስና ጉዳይ ላይ ከውጭ የመጣ ጠላት የለም። ሁሉም በየቀኑ የሚያነጋግራቸው፣ ስለ ሙስና አስከፊነትና፣ አስጸያፊነት በEBC በየቀኑ የሚያደነቁሩንና ምሽቱን ደግሞ በዘመዶቻቸውና በጥገኛ አሽከሮቻቸው ሀገሪቱን በመዝረፍ ላይ ያሉ መንግስትን እናገለግላለን የሚሉ ባለስልጣናትና መኮንኖች ስራ ነው። ቅንነቱና ስልጣኑ ካልዎት ችግሩ ከቤት ነው፤ መፍትሄው ቆራጥ አመራርን የሚጠይቅ ነው።

Filed in: Amharic