>
4:32 pm - Monday September 24, 3956

ፕሬዚደንት ፊደል ካስትሮ ሩዝ ማን ነበሩ [ነብዩ ሲራክ]

የቀድሞው የኩባ ፕሬዚዳንት ፊደል ካስትሮ ሩዝ ስንብት !

* ፕሬዚደንት ፊደል ካስትሮ ሩዝ ማን ነበሩ
* የኢትዮጵያ ባለ ውለታ … “ ቪቫ ካስትሮ ”
* “ዋንታናሜራ ዋህዳ ዋንታናሜራ ”
* አዎዛጋቢው ኮሚኒስት መሪ ፊደል ካስትሮ

ከቶ ፕሬዚደንት ፊደል ካስትሮ ሩዝ ማን ነበሩ ?

fidel-castro-by-nebiyu-sirakእአአ ነሀሴ 13, 1926 ዓም ትውልድ ሀረጋቸው ከእስፔን ከሚሳብ የገበሬ ቤተሰብ የተወለዱት ፊደል ካስትሮ ሩዝ ዓመታቸው ለሶሻሊስት እብዮት የቀና ልባቸው እስከ መጨረሻው አቀንቅነው ይህችን አለም እአአ ህዳር 25 ቀን 2016 ዓም ዘንድሮ ቁርጥ ሆኖ ወደ ዚህ አለም በመጡ በ90 ዓመታቸው ይህችን አለም ተሰናብተዋል 🙁

በወጣትነት እድሜያቸው ንቁና አርቆ አሳቢ የነበሩት ፊደል ከስትሮ በሀቫና ዩኒዘቨርሲቲ እየተማሩ “ተቃዋሚ ነህ !” ተብለው በአሜሪካ በሚደገፉት በጀኔራል ፍላጅዎ ባቲስታንን Fulgencio Batista አገዛ ዝ ለእስር ከተዳሩጉት በርካታ ኩባውያን መካከል አንዱ ነበሩ … እልህ ኛው ፊደል ካስትሮ እአአ በ1953 ከእስር እንደተፈቱ ግን ወደ ሜክሲኮ በማቅናት አለም በፍቅር የሚያወድሰውን ብርቱ የነጻነቱን ታጋይ ቸ ጉቤራንና ወንድማቸ ውን የአሁኑን ፕሬዚደንት ራዎል ካስትሮን ይዘው ህዝቡን ረግጦ የያዘውን አንባገነን መንግስት ለመታገል ቆረጡ … ጊዜ ሳይወስዱ በዚያው አመት በሀገረ ሜክሲኮ የሀምሌው 26 ንቅናቄ 26th of July Movement የሚል ግንባር መስርተው ነፍስ ወከፍ መሳሪያን ይዘው ወደ ኩባ በጀልባ ተመለሱ ፣ ከዚያም በገጠሩ የሀገሪ ቱ ክፍል እየተዘዋወሩና ትግሉን እያስፋፉ ለህዝብ ነጻነት የሽምቅ ውጊያ አፋፋሙት ፣ ካስትሮ እልህ አስጨራሹን ፍልሚያ ታገለው ያታገሉ ቆራጥ የጦር ገበሬም ነበሩ ! እአአ በ1959 ዓም ካስትሮና ጓዶቻቸው በለስ ቀንቷቸው በአሜሪካ የሚደገፈውን የጀኔራል ፍላጅዎ ባቲስታንን Fulgencio Batista አገዛዝ በመግልበጥ የስልጣን በትረ ሰሎሞኑን ጨበጡ ፣ ጀግና ተብለው ተወደሱ ተከበሩ ! ሟች ፊደል ካስትሮ ሩዝ እአአ ከ1959 እስከ 2008 ዓም በሶሻሊት ደጋፊ ዜጎቻቸ ውና በኩባ ደገፊ ሀገራት ዘንድ ተወዳጅ ዲሞክራት ታጋይ በኋላም ቆፍጣና ጠቅላይ ሚኒስትርና ፕሬዚደንት ነበሩ … !

እለተ ሃሙስ እአአ ህዳር 24 ቀን 2016 ዓም ፕሬዚደንት ካስትሮ በህይ ዎት ከመለየታቸው አስቀድሞ ለህዝባቸው ቀርበው ኑዛዜ መሳይ ንግግር አድርገው ነበር… ፊደል ካስትሮ ሩዝ በዚሁ ንግግራቸው በመጨረሻው ሰአት አዲሱ ትውልድ ሀገሩን እንደሚረከብ ተናግረው ነበር … ይህን በተናገሩ ማግስት አፍቃሬ አሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ” ይህን ተናገሩ ” ብለው ሊሳለቁባቸው እንጣጥ እንጣጥ ሲሉ የ90 ዓመቱ አዛውንት ፊደል ካስትሮ ህዳር 25 ቀን 2009 ዓ.ም ሌሊት እስከወዲያኛው አንቀላፍተው ተገኙ ፣ ከሽምቅ ውጊያው ፈታኝ ከትጥቅ ትግል እስከ መጨረሻዋ እስትንፋሳቸው ቀን ያልተለዮዋቸው ታጋይ ታናሽ ወንድማቸው የአሁኑ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ራውል ካስትሮ መራራውን የካስትሮ ህልፈት መርዶ ነጋሪ ነበሩ 🙁 አዎ ” ፕሬዚደንት ፊደል ካስትሮ ሩዝ አርፈዋል ! ” ነበር ያሉት … 🙁

ፕሬዚደንት ፊደል ካስትሮ ከዚህ ቀደም ከ600 መቶ ጊዜ በላይ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው ተርፈዋል ፣ ካንድም አስር ጊዜ ያህል “ ካስትሮ አረፉ ! ” ተብሎ መርዶ ተነግሮ ሳይሞቱ የቀሩት የ90 ዓመት የላቲን አሜሪካ ጉምቱ አወዛጋቢ መሪ ፊደል ካስትሮ ሩዝ በእርግጥም እስትንፋሳቸው ከስጋቸው ተለያይታለች 🙁

የኢትዮጵያ ባለ ውለታ … “ ቪቫ ካስትሮ ”

በሶማሌው ፕሬዚደንት የዚያድባሬ መንግስት በ1969 ዓም ሶማሊያ በቀቢፀ-ተስፋ እስከ ሃረርና ድሬዳዋ ዘልቆ ሲወረን የደረሱልን በፕሬዚደንት ፊደል ካስትሮ መንግስት የታዘዙት ኩባዎች እንጅ ከፕሬዚ ደንት ካርተር የገዛነው የጦር መሳሪያና አሜሪካኖች አልነበሩም ! እነ ፕሬዚደንት ካርተር ፊታቸውን ሲያዞሩብን በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ፣ የጦር ሜዳ ደራሽ ሀኪሞችን ከኢትዮጵያ ጎን ያሰለፉ ኩባና ካስትሮ ነበሩ … የሶማሌ መንግስት የውስጥ መናቆራችን ሰልሎና አጥንቶ ጦርነት ሲሰብቅብንና በአሜሪካ እየታገዘ ሲዘምትብን የጀርባ አጥንት አጋርራችን ካስትሮ ኩባ ነበሩና ውለታቸው ከትውልድ ትውልድ ይተላለፍ ዘንድ ግድ ይላል !

ኩባዎች በክፉው ቀን በሶማሌ የጦርነት አውድማ ድል እንድንቀዳ ጅ ያደረጉት ድጋፍ የገዘፈ ነበር ፤ ይህ ብቻ አይደለም ፤ ለሃገራቸው ድንበር ደማቸውን ያፈሰሱትን የኢትዮጵያ ጀግኖች ልጆችን በማሳደግ ፣ በመደገፍ ፣ በመርዳት ፣ በማስተማር ፣ የተለያዩ ባለሙያዎቻቸው ወደ ኢትዮጵያ በማስገባትና ልዩ ደጋፍ በመስጠት ፤ በጤና ፤ በምህን ድስና ፣ በስነ ቴክኒክና በመሳሰሉት ሙያዎች ከታዳጊ እስከ አዋቂ በስኮላርሽፕ ወደ ኩባ ወስዶ በማስተማር የተማረ ዜጋን ለሀገራችን በማፍራት ትልቁን ሚና የተጫወቱት ፕሬዚደንት ፊደል ካስትሮና ኩባዎች ናቸውና እንወዳቸዋለን ! እናከብራቸዋለን ! የፕሬዚደንት ፊደል ካስትሮ ሩዝ ህልፈት ጥልቅ ሀዘናችንም ነው !

ካስትሮና ኩባውያን ስለ ዋሉልን የከበደ ውለታ እንደ ሀገር ተረካቢ ትውልድ የታሪክ ሰነድ አገላብጠን ከነበሩት የነበረውን እውነተኛ ገጽታ መረዳት ግድ ይለናል … ይህን ከማድረግ ባሻገር ባለ ውለታውን መሪና ህዝቡን ከደርግና ከሹማምንቱ እኩል አይተን ውለታቸውን ማርከስ ተገቢ ነው አልልም … ዛሬ ላይ ሆነን የፊደል ካስትሮንና የኩባውያንን ውለታ ስናስታውስና ስናወድስ ፣ ለመሪያቸው ህልፈት ሀዘናችን ስንገል ጽ ከጨቋኙ የደርግ መንግስት ጋር አዳብለን አይደለም ፤ ለነገሩ የሶማ ሊያ ወረራ ሲነሳ ደርግም ብሔራዊ ክብራችን በማስከበር በታሪክ በበጎ ጎኑ ሲዘከር ይኖራል ፣ ከምንም በላይ የደርግ ጨቋኝነት እንዳለ ሆኖ ሀገር በውጭ ወራሪ ስትከበብ ስልታዊ ሽርክናን ከኩባ መንግስት ጋር መስርቶና ጀግናውን ሰራዊት በማስተባበር ትልቅ ስራ ሰርቶ በማለፉን ክብር እናወሳዋለን !የዚያን ጊዜ ተጋድሎ ጀግኖቻችንም የእውነት ጀግኖች ነበሩ ፣ ለሀገራቸው ድንበር መከበር ታግለው መስዋዕት የሆኑትን ምንጊዜም በክብር ሲዘከሩ ይኖራሉ !!ወደ ካስትሮና ኩባ ስንመለስ ” ኩቫ ቪቫ ፤ ካስትሮ ቪቫ “ ብሎ ያ ትውልድ ኩባና ካስትሮ ለፈፀሙት ውለታ ምስጋና እንደቸራቸው እኛም ኩባና ከስትሮ ላደረጉልን ድጋፍ ኩቫ ቪቫ ፤ ካስትሮ ቪቫ እንላለን! ዛሬም ሌላ ቀን ነውና የኩባ ህዝብ በፕሬዚደንት ካስትሮ ህልፈት ለደረሰበት ሀዘን ፈጣሪ እንዲያጽናናቸው ፣ የካስትሮም ነፍስ ይማር ዘንድ ጸሎታችን ነው !

“ዋንታናሜራ ዋህዳ ዋንታናሜራ ” …

ረዥም ዲስኩርን በማድረግ ተወዳዳሪ ያልነበራቸው የኩባ ፕሬዚደ ንት ካስትሮና ኩባ ሲነሱ ኢትዮጵያውያን ትዝታችን ብዙ ነው ፤ በተለይ ያለፈውን የሚያጫውቱን የ ያ ትውልድ ምስክሮች ለዛሬ ያደረሱን ብዙ ትዝታ አላቸው … ከምንም በላይ ሶሻሊስት ኩባ የኢትዮጵያ ወዳጅ ነበረችና ኩባውያን ሊረዱን ሲመጡ የሃገሬውን ሰው ተመሳስለው እየደገፉት ተዋልደው ሳይቀር ኖረዋል ! በዚያ አሁን በራቀው ዘመን “ዋንታናሜራ ዋህዳ ዋንታናሜራ “ የሚለውን ዜማ ትርጉሙ ሳይገባው ያላንጎራጎረ እንዳልነበር ከዚያ ትውልድ ታሪክ ወራሾች በእንጉርጉሮ የታጀበውን ዜማ ሰምቸ አውቃለሁ… በዚያ የዘመን ጫፍ ነፍስ አውቄ ሰምቸ የማልጠግበው የኩባዎች ” ዋንታናሜራ“ ዜማ እንደነበርም ብልጭ ድርግም የሚል ትዝታ አለኝ!

አዎዛጋቢው ኮሚኒስት መሪ ፊደል ካስትሮ …

የፊደል ካስትሮ ህልፈትን ተከትሎ ዘጠና ብሔራዊ የሃዘን መታወጁን ፕሬዚደንት ራውል አስታውቀዋል፡፡ የካስትሮ ህልፈት ከተሰማበት ሰዓታት ጀምሮ ደግሞ አለም ለሁለት ተከፍሎ ማመስገን ማውገዙን ቀጥሏል … በመላ ሀገረ አሜሪካ በሚያሚ ለከተሙት ትውልደ ኩባውያን የካስትሮ ሰብዕና ሲገለጽ ከአስፈሪ ጭራቅን የከፋ ነው …” ያሰደዱ ፣ ያሸሹንና ያፈናቀሉን ካስትሮ ናቸው! ” በማለት የካስትሮ ህልፈተ ዜና ደስታ ሆኖ ሲያስፈነጥዛቸው ተመልክተናል ፤ ለሃቫናና ለቀሪው ግዛት ፣ የሶሻሊስት ሀገሯ ኩባ እና ወዳጆቿ ደግሞ በአንጻሩ በሀዘን ተውጠው የመሪያቸው የፕሬዚደንት ካስትሮ ህልፈት የከበደ ሃዘን ሆኖ ደመናው የሃዘን ድባብ መልበሱ አልቀረም… እንዲህ አለም ለሁለት ሲከፈል ሀበሾችም ለሁለት ተከፈለን የቁርጥ ቀን ባለ ውለታችን በክፉ ደግ ማንሳታችን አልቀረም … የአቅም መረጃችን ፣ የጥላቻ ፍቅራችን ያህል የካስትሮን ህልፈት ተከትሎ ማወደስና ማውገዝም ይዘናለል … !

ፊደል ካስትሮ ለባላንጦቻቸውና ለሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ” አለም አንቅሮ የተፋው ሶሻሊስት አብዮት አራማጅ ! ” ነበሩ ፣ ” ፊደል ካስትሮ ሀገር ወዳድ ፣ ፍትህን እኩል ለዜጎች ለማዳረስ ተግተው ለውጥ ያመጡ ፣ መሀይምነትን ያጠፉ ፣ ኩባውያን ትምህርትና ጤና በሰፊው ማዳረስ የቻሉ ፣ የአሜሪካን ጫና ተቋቁመው ለሶሻሊስት አብዮት ታግለው ያታገሉ ፣ ብሔርተኛና ብቸኛው የኮሚኒስት መሪ” እየተባሉም በደጋፊዎቻቸው ይወደሳሉ … በእርግጥም ፕሬዚደንት ፊደል ካስትሮ ሩዝ አወዛጋቢ መሪ ነበሩ !

ፊደል ካስትሮ ላመኑበት ወደ ኋላ የማይሉት እንደ ጎረቤት ኤርትራው መሪ ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከዘመኑ ጋር የሀገራቸውን ፖለቲካውን ማዘመ ን ያልቻሉ ፣ ለውጥ ፈላጊ ዜጎቻቸውን ያሳደዱ ፣ ያሰሩና የገደሉ ” የምከተለውን ካልተከተልክ እርጉም ነህ ” በሚል መንፈስ ሀገረ ኩባን ባረጀ በሰፈጀ ርዕዮት መምራታቸው እሙን ነው …ካስትሮ ሀገራቸውን ከዘመነው አለም ጋር እንዳይገናኙ ያደረጉ ፣ የፖለቲካ ብልጣብልጥነት የማይነካካቸው ግትር መሪ በመባል በስልጡን ፖለቲከኞች የሰላ ሂስ ይቀርብባቸዋል ፣ ይነቀፋሉም …!

ካስትሮ የኢትዮጵያ የቀድሞ ብርቱ ወዳጅና ባለውለታ በመሆናቸው ብንወዳቸውም የአሜሪካ ቁጥር አንድ ቀንደኛ ባላንጣ እንደሆኑ በ20 ኛው ክፍለ ዘመን ነጻነትን ለሃገሬው ከልክለው ፤ የመድብለ ፖለቲካን ፖለቲካ ስርአት ፈንግለው፣ በአንድ አውራ ሶሻሊስት ፖርቲ የፖለቲካ ምህዳ ሩን አጥብበው የኖሩ አንባገነን መሪ ነው ስለመሆናቸው በርካታ ሰነዶች ያትታሉ ። የካስትሮ መንግስት ዛሬ ለሀገሬው በጤናና በትምህርትን ማስፋፋቱ ረገድ ያሳየው እመርታ ቢወደስም የጤናና ትምህርት መስፋፋቱ ኩባውያን ከተነጠቁት የሰብአዊ መብት አንጻር በዲሞክራሲ ናፋቂያን ዘንድ ” አንባገነን! ” እየተባሉ ከፍ ያለ ትችት ሲሰነዘርባቸው የሚባጅ አወዛጋቢ መሪ ተብለው በታሪክ ይዘከራሉ ! አዎ በክፉ መዘከራቸው እያደር የሚገን ቢሆንም በሰሩት መልካም ስራ ከኩባ አልፎ እንደ ኢትዮጵያ ባሉት የኩባ ወዳጅ ሀገራት ህዝብ ልብ ውስጥ ካስትሮ ሁሌም አሉና በክብርም ይዘከራሉ ! ክብር ለሚገባው ክብር እሰጣለሁ !

ወዳጃችን ፕሬዚደንት ፊደል ካስትሮ ፣ ነፍስዎን ይማር !

ነቢዩ ሲራክ
ህዳር 18 ቀን 2009 ዓም

Filed in: Amharic