>

3ቱ ንጉሶች እና የታሪክ እውነታዎች፣ አጭር ዳሰሳ [ቬሮኒካ መላኩ]

Emye Minilikየአለም ጥቁር ህዝቦችን ታሪክ የቀየረው ኢትዮጵያዊው ንጉስ የነበረው የአፄ ምኒልክ ልደት እየደረሰ ነው ። የልደት ቀኑ ደርሶ በድምቀት እስክናከብር ድረስ  በአንዳንድ የታሪክ እውነታዎች እናሟሙቅ ። እስኪ በጨረፍታ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ስለነበሩት ሶስቱን ንጉሶች ፖለቲካዊ ሁኔታ በጨረፍታ እንዳሰው።

1 ~ ከእንግሊዝ እንጀምር ። የእንግሊዝ ነገር ሁሌ ይገርመኛል ። ያኔ በ18ኛው ክፍለዘመን መደምደሚያና በ19ኛው ክ/ዘ መባቻ ከደምቢያ  የተነሳው ካሳ ሀይሉ የተባለው  ሰው የዘመነ መሳፍን የአካባቢ ገዥዎች በጦርነት እየደረማመሰ ካሸነፈ በኋላና አፄ ቴዎድሮስ ብሎ ከነገሰ በኋላ አፍሪካ ቀንድ እና ቀይ ባህር አካባቢ ስታንዣብብ የነበረችው እንግሊዝ ቀልጠፍ ብላ አምባሳደሮቿን ጆን ቤልንና ፕላውዴንን ወደ ጎንደር ላከች።

ቴዎድሮስም ከእንግሊዝ አምባሳደር ፕላውደን ጋር በጣም ተስማምቶ ከእንግሊዝ ጋርም ወዳጅነት መሰረተ ። ይሄንም ወዳጅነት ምክንያት በማድረግ የእንግሊዟ ንግስት ቪክቶሪያ ገና በጠዋቱ በ1854  ለቴዎድሮስ ስጦታ ላከችለት ።
ያ ስጦታም “ሪቮልቨር ” የተባለ ሽጉጥ ነበር ። የእንግሊዝ ንግስት ለቴዎድሮስ ስጦታውን ከላከችለት  14 አመታት በኋላ መቅደላ ላይ ቴዎድሮስ ራሱን በራሱ ከሰዋ ከደቂቃ በኋላ  የእንግሊዝ ወታደሮች ሮጠው  ቴዎድሮስ የወደቀበት ሲደርሱ ቴዎድሮስ እጅ ላይ ያገኙት ሪቮልቨር  ሽጉጥ በወርቅ ፅሁፍ እንደዚህ የሚል ተፅፎበት ነበር …..”
PRESENTED
BY
VICTORIA
QUEEN OF

GKEAT

BRITAIN AND IRELAND T0
THEODORUS
EMPEROR OF ABYSSINIA
AS A SLIGHT TOKEN OF HER GRATITUDE
FOR HI4 KINDNESS TO HER SERVANT PLOWDEN
1854 >>
Commasie &

Magdela

Page 449.

2~ አሁንም የእንግሊዝ ነገር ይገርመኛል ። ቴዎድሮስ ራሳቸው እንግሊዞች በሰጡት ሽጉጥ ራሱን ካጠፋ በኋላ ። ለሌላው የትግራዩ ካሳ ምርጫ 90 መድፍና ብዙ ሺህ መሳሪያ በመስጠት ንጉስ እንድሆን አደረጉት ። ከነገሰ ከ10 አመታት በኋላ እንግሊዝ ሪር አድሚራል ሮበርት ሂዎት የሚባል ጀኔራል  ወደ አድዋ ከተማ በመላክ አንድ አደገኛ ውል እንድዋዋል አደረገችው ። የዚህ ውል ዋና ጭብት ሱዳን ውስጥ መሃድስት በሚባለው የነፃነት ተዋጊ ተከብቦ መውጫ ያጣው የግብፅ ጦር በኢትዮጵያ በኩል እንድወጣ አፄ ዮሃንስ እንድፈቅዱ የሚያደርግ ውል ነበር።  የእንግሊዙ ጀኔራል አፄ ዮሃንስን ጉድ ሰራው። ጠላቶቻቸው የሆኑት ግብፆች   በኢትዮጵያ በኩል ማምለጣቸው እጅግ ያበሳጫቸው መሃድስቶች ለበቀል ኢትዮጵያን ወረሩ ወረራውን ለመመከት ዮሃንስ ዘመተ ። ይሄ ሁሉ ሲሆን እንግሊዞች በዛው አካባቢ ሰፍረው ይታዘቡ ነበር ። በመጨረሻ ዮሃንስ በመሃድስት ጥይት ቆስሎ ሞቱ። እንግሊዝ አነገሰችው እንግሊዝ አስገደለችው።


3~ አፄ ቴዎድሮስ ወደ ሸዋ ዘምቶ ሲመለስ  ምኒልክን ወደ ጎንደር በመውሰድ እያስተማረ አሳድጎታል።  ምኒልክ ከቴዎድሮስ ጋር ከሸዋ  ወደ ጎንደር  ሲሄድ የ10 አመት ታዳጊ ነበር። ምኒልክ ለአቅመ አዳም ሲደርስ የቴዎድሮስን ሴት ልጅ አልጣሽን አግብቷል ። በመጨረሻ ምኒልክ ከመቅደላ ወደ ሸዋ ሲገባ ቴዎድሮስ በሀዘን  “ለምን አልጣሽን ይዟት አልሄደም? ” የምትል ብቻ ቃላት ነው የተነፈሰው ። አንዳንድ ፀሃፊዎች እንደፃፉት ቴዎድሮስ ከመሞቱ በፊት ምኒልክን አልጋ ወራሹ ለማድረግ ወስኖ ነበር ።
ምኒልክም ለቴዎድሮስ እስከመጨረሻው ከፍተኛ ፍቅር ነበረው ።
ከምኒልክ ጋር በሸዋ አብሮ ብዙ አመታት የቆየው ጣሊያናዊ መነኩሴ አባ ማስያ እንደፃፈው ምኒልክ መሃላ ሲፈፅም እንኳን  << ቴዎድሮስ ይሙት  !!>> በማለት ነበር ብሏል ።  የቴዎድሮስ የመጀመሪያ ልጅ መሸሻ ቴዎድሮስ አባቱ ከሞተ በኋላ ወደ ሸዋ በመሄድ ከምኒልክ ጋር አብሮ መኖሩ የሚያመለክተው በቴዎድሮስና በምኒልክ መካከል የነበረውን ከፍተኛ ፍቅር ነው።

4~ ህውሃት ወደ ትግል ለመግባት ታሪካዊ መሰረት አድርጎ የሚተርከው በትግሬው ተወላጅ አፄ ዮሀንስ ከደርቡሾች ጋር ሲዋጋ ከመሞቱ በፊት ለልጁ ለራስ መንገሻ ያወረሰውን ዙፋን አማሮች ካላግባብ በምኒልክ አማካኝነት ወደ ሸዋ አዛውረውታል  በዚህም የተነሳ የትግራይ ህዝብ በአማራ ጨቋኝ ስርአት ለመቶ አመታት ስለተበደለ መበቀል አለብን የሚል ነው።

5~ ይሄን የተፋለሰ ታሪክ እንመርምረው ካልን ታሪክ ተቀይሮ ዮሀንስ መተማ ላይ የመሃድስትን ጦር አሸንፎ ባለድል ቢሆን ኖሮ እንኳን የንጉሰ ነገስትነቱን ስልጣን ምኒልክ በሀይል አስገድዶ  ከዮሃንስ መውሰዱ የማይቀር ነበር።  አፄ ዮሃንስ ንጉሰ ነገስት በነበረበት ወቅት የሸዋው ምኒልክ በሚገዛው አገር ስፋት ፣ ባለው ጦር ጥራትና ብዛት እንድሁም በህዝብ ፍቅር ከዮሃንስ እጅጉን እየበለጠ ነበር ።
ለምሳሌ ዮሃንስ ከ1879 በኋላ ወደ ወሎና መሃል አገር ለመምጣት ሲፈልግ ለሚንልክ ” ልመጣነውና ፍቀድልኝ ” የሚል የልመና ደብዳቤ ከፃፈ በኋላ እንደነበር  ዮሃንስ ለምኒልክ የሚፅፋቸው ደብዳቤዎች ያረጋግጣሉ።

6 ~ በወቅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ አውሮፓውያን የሁለቱን ተቀናቃኞች ሀይል ከገመገሙ በኋላ ለመንግስቶቻቸው በሚፅፉት ሪፖርት << ከ1262  ጀምሮ እስከ 1868 ድረስ በሰለሞናዊው የአማራ ስርወ መንግስት  በመሃል በእንግሊዞች እርዳታ ጣልቃ የገባውን ዮሃንስን በቅርቡ ምኒልክ ጦርነት በመግጠም አሸንፎ የአባቶቹን ዙፋን እንደሚረከብ ስለማያጠራጥር ፖሊሲያችንን በዚህ ሃቅ ላይ መቅረፅ አለብን> > በማለት ይፅፉ ነበር።

7~ ከ1878 በኋላ የአፄ ዮሃንስ ንጉሳዊ ሀይል በፍጥነት እየተዳከመና እየተሽመደመደ ነበር ። ይባስ ብሎም ብቸኛ ወንድ ልጃቸው የነበረው አርአያስላሴ ዮሃንስ በ20 አመት እድሜው በህመም በመሞተ ከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ነበሩ ።
ከዚህ በተጨማሪ በፊት እርስ በርስ ባላንጣና የስልጣን ተቀናቃኝ ከዛም አልፈው ውጊያ ያደረጉት ምኒልክና የጎጃሙ ንጉስ ተክለሃይማኖት አስደናቂ አጋርነትና ወዳጅነት ከመመስረት አልፈው ጠላትን በጋራ የመከላከል ውል ተዋውለው ነበር።


8 ~ አፄ ዮሃንስ መተማ ቆስለው በሚያጣጥሩበት ወቅት ዙፋናቸውን ለወንድማቸው ልጅ ለራስ መንገሻ ቢያወርሱም የትግራይ መኳንንት ከእነአሉላ አባነጋ ጀምሮ የሀይል ሚዛኑን በመገምገም  መንገሻን መተው ጀመሩ።
እርስ በርሳቸውም መራኮት ጀመሩ ። በጎጥ መጠዛጠዝ ጀመሩ ። አሉላ አባ ነጋ እና የሽሬው ደጃች ሀጎስ እርስ በርስ ውጊያ ጀመሩ። አሉላ አባነጋን ራስ ሀጎስ ገደለው ፣የአሉላ ወታደር  ራስ ሀጎስን ወድያው ተኩሶ ገደለው ። የኢትዮጵያ የተከፋፈሉ ገዥዎች
ወደ ሸዋ በመሄድ ምኒልክ  ጋር መግባት ጀምሩ። ሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብ የምኒልክን ንግስና በደስታ ተቀበለው።

Filed in: Amharic