…
2 ~ ዛሬ ደሞ ቤኒሻንጉል ውስጥ ተመሳሳይ ሴራ እንደ ጀመሩ እየሰማን ነው ። ሌላም ቦታ መቀጠሉ አይቀርም ። ህውሃት የረገጠው መሬት እየሸሸ እና እየተናደበት ሲመጣ የሚተገብረው ተመሳሳይ ስልት ነው። የታረደች ዶሮ መሞቷ ላይቀር እየተንደፋደፈች በዙሪያዋ ያሉ ሰዎችን በደም መበከሏ አይቀርም። ህውሃትም እያደረገች ያለችው እንደ ዶሮዋ ነው።
…
3 ~ ሰሞኑን በጠራራ ፀሀይ ባሩድ እየተኮሰ ህይወት የሚያጠፋው የስርአቱን ጄስታፖ የሆነውን መከላከያ ህዝብ ይወደዋል እየተባለ እየተቀለደ ነው።
የዚች አሰቃቂ ቀልድ ፖለቲካዊ አንድምታ ሌላ ነው ። ከቀናት ወይም ከሳምንታት በኋላ ደሞ ” ህዝቡ መከላከያ ሰራዊቱን በጣም እንደሚወደው ስለተረጋገጠ አገሪቱን ሙሉ በሙሉ እንድያስተዳድር ተወስኗል ።!” ብለው መናገራቸው አይቀርም።
አሁን ቢያንስ መፈንቅለ መንግስት ካልሆነም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ይች አገር እንደማይቀርላት ግልፅ እየሆነ ነው። ከዚህ በኋላ ህውሃት በህዝብ ውስጥ ተቀባይነቱ እየጨመረና ጥርስ እያወጣ ያለውን እንደ ኦህዴድ ያለውን ፓርቲ ደፍቃ መግዛት የምትችለው መከላከያና ደህንነት ሙሉ በሙሉ የአገሪቱን ስልጣን ከተቆጣጠረ ብቻ ነው። ነገር ግን ይሄም ሌላ የፖለቲካ ኢንፌክሽን ፈጥሮ አገሪቱን Full fledged ወደ ሆነ ቀውስ መውሰዱ አይቀርም።
…
4 ~ ማንኛውም ስርአት ተወልዶ ፣ አድጎ በመጨረሻ ይሞታል ። ይሄ የማይገሰስ የፖለቲካ ህግ ነው። ህውሃት ደደቢት ውስጥ ተወልዶ ኢትዮጵያ የምትባለውን ላም ብቻውን ጠጥቶ ፋፍቶ አድጎ ፣ ጎልምሶ አሁን አድሜውን ጨርሶ በመሞት ላይ ነው። ነፍስ እስክትወጣ መንፈራገጥ የተለመደ ነው ። የተፈጥሮን ህግ በመቃረን ከሞት ማምለጥ አይቻልም። ህውሃት ይሄን ሀቅ ተገንዝቦ አሟሟቱን ቢያሳምር መልካም ይሆናል።