>

በዘር በብሄር ዜጎች በመከፋፈል በሃገራቸው እንደባእድ በጥይት በድንጋይ በግፍ መግደል ይቁም!!” (ኣስገደ ገብረስላሴ)

በሀገራችን በዘመነ ኣገዛዝ ኢህኣደግና ኣባል ፓርቲዎች በህወሓት ባኣዴን ኣማራ ትግራይ በሚሊ ልዩነት የሁለቱ ፓርቲውች እጅ ማስገባት ተጨሙሮበት በጎንደር ፣በኣርማጭሆ ፣በመተማ ፣ በወልቃይት ፣ በጎጃም ባህርዳር የተቀጠፉ ዜጎች ቁጥር ስፍር የለለው የወደመውና የተወረሩ በህዝቦች መካከል ቂም በቀል ጥላቻ ከፈጠሩ በኃላ በመጨረሻ የኣባይ ወሉና የገዱ እንዳርጋቸው ቡዱኖች የውሼት የህዝቦች ጉባኤ ኣድርገናል ብለው ኣጭበረብሮውናል ።

ቀጥሎ በባኣዴንና ኦሆዴድ ባለው የውሼት ጠብ በማስነሳት የብልሽታቸውን ለመደበቅ ሲሉ በኦሮሞና በኣማራ ፣በትግራይና በኦሮሞ ቢሄር በመጋጨት የግጭቱ መነሳት የራሳቸው ሴራ እያለ ለተቃዋሚዎች በመለጠፍ እጅግ ቡዙ የኣማራ የትግራይ ፣የእሮሞ ወገኖች እርስ በእርሳቸውና በጸጥታ ሃይሎች ተገድለዋል ሃብት ወድሟል ።

የበዚህ ሳምንት ደግሞ በኦሮሞና በኢትየጱያ ሱማሌ ህዝቦች ጎንጽ በመፍጠር እንሆ የማያቋርጥ ግጭት ተፈጥሮ ዜጎች በየቀኑ እየተገደሉ ፣እየተፋናቀሉ ይታያሉ ። በየኣካባቢው ያሉ ዩንቨርሲቲዎች በተለይ በጅጅጋ ዩንቨርሲቲ በፓርቲ መሪዎች ግፊት እንዲፈናቀሉና ቂም በቀል እንዲስፋፋ ያደርጉ ኣሉ ።ይህም ሴራ ነው ።

ኣሁን ደግሞ በኦሮሞ ህዝብ በሁሉም ዞኖች በዩንቨርስቲዎች ሳይቀር የትግራይና የኣማርኛ ተናገሪዎች ያናጣጠረ የሞት ሰለባ ሆነው ሰዎች እንደእባብ በድንጋይ ተቀጥቅጠው የሚገደሉበት ሁኔታ ይታያል ።

የዚህ ግጭት ሁሉ ኣቃጣጣዮች ከላይ እንደገለጽኩት ዋናዏቹ ተዋናዮች የኢህኣደግ ኣባል ፓርቲዎች የባኣዴን የህወሓት ፣የእሆዴድ ፣የሱማል ፣እና የሌሎች ኣጋር ፓርቲዎች ውስጣዊ ቀውሲ ነው ። ምክንያቱ የሁሉም ፓርቲዎች መሪዎችና ቅጥረኛ ተላላኪ ካድሬቻቸው የስልጣን ሽኩቻና በሙሱና መበላላሸታቸው ምክንያት ኣገር ያባላሸ ወንጀላቸው ደብቀው ለመኖር እና የተባላሸ ስርኣታቸው እድሜ ለማራዘም ታሳቢ በማድረግ በዜጎች መካከል የዘር ፣የብሄር ፣ የማንነት ፣ የሃይማኖት የወሰን ወይ ጠረፋ ፣ የኣከላለል ጥያቄ እንዲነሳ ወዘተ እየኣነሳሱ ህዝብ እርሱ በእርሱ እያጋጩና እንዲገዳደሉ በማድረግ ገበናቸው ለመሸፈን በግጭቱ ይፈጠርና እያጋጠመ ያለው መተላለቅ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች በወንጀለ በመፈረጅ ያጭበረብራሉ ።

የሀገራችን ሙሁራን ተመራማሪዎች ቀለም የቆጠራችሁ በሙሉ ተቆርቃሪ የሆኑ ያገር ሽማግሌዎች በሃገራችን ተፈጥሮ ያለው ኣደጋ ኣይተውና ተገንዝበው ያገባናል ብለው በተቆርቋሪነት በኣንድነት በመንቀሳቀስ በተናሳሽነት በመነሳት የኢህኣደግና ኣባል ፓርቲዎች ሴራ ነቅተውበት የዜጎች ግድያ ሀብት ውድመት ይቁም !! ኣንድነታችን ወደቦታው ይመለስ በሚል ሞፈከርና እምነት ኣገራችን ህዝባችን ፣ሃብታችን እናድን !! ሁሉም ክልሎች የ100 ሚሊዮን ህዝባችን እኩል መኖርያ ነች ብለን በሰላማዊ መንገድ በኣደባባይ ሰልፍ ወጥተን ለለውጥ ንዝመት ።

ኣማራ ተገደለ ፣ትግሬ ተገደለ ፣ኦሮሞ ሱማል ተገደለ እያለቹ ህዝብ ብድር እንዲመልስ ፣ በማለት ቤት ለቤት እየተሽለኮለኳችሁ ዘረኝነት እየቀሰቀሳችሁ ዜጎች የምታስጨፈጭፉ ፣ የኑጹሃን ዜጎቻችሁ ሃብት ከማስወርሩ ተቆጠቡ።
ከኣስገደ ገብረስላሴ
መቀለ
21 / 02 / 2010

Filed in: Amharic