>

የዋህ ፖለቲካኛ እንደ መዘውር በየሴኮንዱ ይለዋወጣል (ቶሎሳ ሌቤሳ)

እሲቲ በዝርዝር ስለዚህ ሰው ማንነት በጽሁፍ ላስረዳችሁ 
1. ለማ መገርሳ የተወለደው ወለጋ ባኮ ከተማ ላይ ነው የተወለደው ከዝያም ወደ አድዋ ህውሃት ኦህዴድ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ተቀላቀለ እዝህ ላይ ከፍተኛ የሆነ ግድያ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ኦኔግ ናችሁ ብምል ብቻ በጭካኔ ብዙ ሺ የኦሮሞ ወጣት ከአብሮ አበሮቹ ጋር የገደለ ሰው ለአድዋ ህውሃት ወያኔ ታማኝ አገልጋይ ሆኖ በመለስ ዜናዊ/ በደብረጽዮ ገብረሚካኤል /በእሳያስ ወልደ ግዬርግስ/ ተመልምሎ የደህንነት የስልክ የውግያ ሬዲዮ ጠለፋ ላይ እንድሰራ ተመደበ። ከዚያም ኢሉባቡር የሸዋ የጅማ ላይ በሀይማኖት ቤተክርስቲያን ማቃጠል ዘመቻ ላይ እንዲሳተፍ ግዳጅ ተሰጠው። እዚህ ጋር ንጽሀን ኢትዮጵያዊ በማያውቁት ቀን ለቀን ደማቸው ፈሰሰ። በተለይ አጋሮ ከተማ ላይ ደንቢ ከተማ ላይ ቡዙ ሰው ህይዎት አለፈ። እንግድህ ይሄንን ወንጀል በተግባር ሚሽኑን ከፈጸመ በኋላ ደግም ወደ ደህንነት በ3ኛ ደረጃ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ ስራውን በጭካኔ ቀጠለ።
አሁንም የኦሮሞ ወጣት ላይ የኦነግ ደጋፊዎች ናችሁ በማለት ከሀረርጌ ከአርሲ ከየቤታቸው ታፍነው የመጡት ላይ የውሻ መርዝ አሰጥቶ በጅምላ አስገደላቸው። ይሄንን ሚሺን ካጠናቀቀ በኋላ የፖሊስ ኮሚሽነር ሆኖ ለተወሰነ ግዜ አገለገለ። ከዝያም የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆኖ አስቀመጡት። ከዝያም የዛሬ አመት ሙኩታር ከድር አውርደው ትክክለኛውን በአድዋ ህውሃት ወያኔ ተጠፍጥፎ የተሰራውን ወንጀለኛ የኦሮሞ ክልል ፕረዚዳንት ነው ብለው የኦሮሞ ህዝብ ሳይመርጠው ሰየሙት። ጫንካችን ላይ አስቀመጡት። ከዝያም እሬቻ ላይ የተገደሉትን በድንገተኛ ነው የሞተው ብሎ ሀውልቱን መርቆ በይፋ አወጀ። የሞቱት ወገኖቻችን ደም ላይ ተሷለቀብን። ይሄም አልበቃ ብሎት በማስተርስ ፕላን ላይ ጥያቄ ያነሱት ተማሪዎች ላይ በየእስር ቤቱ ግድያ ስቃይ እንድፈጸምባቸው ተዋንያን ሆኖ ቀጠለ። ከዝያም ሀገሪታዋ በኩማንድ ፖስት አዋጅ ለ10 ወር ካሳለፈች በኋላ ልክ አዋጁ እንደ ተነሳ ቄሮ ትግሉን አቀጣጠለው። አቶ ለማ መገርሳ ታይቶ የማይታወቅ ሜሺን ተሰጣቸው። አንድነት የሚል የአድዋ ህውሃት ወያኔ ተልዕኮ ይዘው ሚዲያ ላይ በጩቤ ምላሳቸው ምን መናገር እንዳለባቸው አጥንተው ለየት ባለመልኩ ዘመቻ ተከፈተ። ከትንሽ ሳምታት በኋላ የቄሮ ትግል እየተፋፋመ ስመጣ ትግሉን ወደራሱ አዙሮት ቁጭ ለማድረግ ደፋ ቀና ማለት ጀመረ ከዝያም ሻሸመኔ ላይ 7 ሰዎሽ በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ ተፈጸመባቸዉ እያየ እየሰማ እንዳልሰማ ምንም አይነት መግለጫ ሳይሰጥ በዝምታ አለፈ ከዚያም በአንቦ ላይ 22 ሰው በአጋዚ ልዩ ሀይል ትእዛዝ የተገደሉቱን ምንም አይነት የሀዘን መግለጫ አዝኛለሁ ሳይል ምንም አይነት ጽህፍ ሳይጽፍ ይሄው አንድነት ልሰብክ ወደ ባህርዳር አቀና ይሄ ነው እንግድህ በአጭሩ የዝህ ሰው ታሪክ ታዲያ እውነት ይሄ ሰው ለኦሮሞ ህዝብ ነው የቆምኩት ካለ ለምን ያለፍርድ የሚሰቃዩትን አያስፈታም ?
ለምን የኦሮሞ ህዝብ በከሰል ማእድን የሚወጣውን ተጠቃሚ አያደርገውም? ከዚያ ቦታ ላይ በግዳጅ የተፈናቀሉትን ተለዋጭ መሬት ካሳ ለምን እንድከፈላቸው አያስደርግም? እንግድህ የዋህ ፖለቲከኛ ይሄንን ወንጀለኛ ከበስተጀርባው ምን ይዞ እየመጣ እንደሆነ ሳያውቅ ዛሬ በ160% ዲግሪ እንደ ወዘር ተገልብጦ ደግፈው ሳይ ለምን ወያኔ አይደግፉም የሚል ጥያቄ መጠየቅ ጀመርኩ። ለማንኛውም ይሄ ሰው ከአድዋ ህውሃት ኦህዴድ ውጭ አዲስ ፓርቲ አለው እንዴ ? 
Filed in: Amharic