>
1:45 pm - Saturday October 23, 2021

"go fund me" አይዞህ ሙሉቀን! ኢትዮጵያ የምታኮራ ውለታ የማትረሳ እናት ናት..የእሷ ልጆች ነን!

Alemneh Wasse News
ታላቁ የኢትዮጵያ ሮማንቲክ ዜማዎች ተገዳዳሪ የሌለው ንጉስ(በሴቶች አስቴር አወቀ መሆኗን ተንዘቡልኝ።ሙሉቀንና አስቴር ያለ ፍቅር ሌላ አጀንዳ አፋቸው ገብቶ አያውቅም ቢኖርም ኢምንት ነው።)ሙሉቀን መለሰ በዕድሜያችን ሲያስኮመኩመን ለኖረው ኪነቱ አክብሮታችንንና ፍቅራችንን የምንገልፅበት ትልቅ ዕድል ፈጥሮልናል።እንደ በጋ ፏፏቴ ኩልል ብሎ በሚፈስና የገፁን ውበት ጭምር በሚያስከነዳ ብርቅ ድምፁ፣ማለፊያ ግጥሞቹና አማላይ ዜማዎቹ የሴትን ልጅ ውበት የቀደሰው ሙሉቀን መለሰ “ስጋዬን አሞኛል!ታስፈልጉኛላችሁ!”ሲል ጠርቶናል።በዕምነቱ የተነሳ ከቀደሙ ስራዎቹ ጋር በመንፈስ የተፋታው ሙሉቀን የዕምነት ነፅነቱንና የህይወት ምርጫውን እንደምናከብርለት ያውቃል።እኛም የሱ ጥዑመ ዜማዎች የዓለማዊ ህይወታችን የማይጠገብ ስንቅና የጋራ ኪናዊ ቅርሳችን አካል መሆኑን ያውቃል።ተግባብተናል።

“አንበሳን በጡጫ እለው የነበረ
ዝሆንን። “” ” ” “”
ነብርን። ” ” ” ” “
እባብ። ጭንቅላቱን እለው የነበረ
ምነው ከአንቺ ስደርስ ልቤ ተሰበረ

አይ ሰውነቷ!እንደው ሰውነቷ!

ከሙሉ ቀን ሰውነቷ በፊትም ሆነ በኊላ የእግዚአብሄር ዕፁብ ድንቅ ፍጡርና የዚች ዓለም ፀጋ ለሆነችው ሴት ልጅ እንደሙሉቀን አምጦ ያቀነቀነ የለም።ስለ ሴት ልጅ ብስራትነት ሲነሳ ግር የሚላችሁ ካላችሁ አንዳፍታ እናትህን አስባት!ገነት ናት!!ፀሀይ ናት—–የምንጊዜም የጠዋት ፀሀይ!!የአሜሪካንን ኒውክሌር ቦምብ የምታስንቅ የደህነትህ ዋስትና ናት!ካላንተ ጥጋብና እርካታ አጀንዳ የሌላት የእግዚያብሄር እጅ ናት!ንፍጣምነትህ፣ጭባነትህ፣ቅልጣንህና ብልግናህ በቸርነቱ ዓይኗ ብሌን ላይ በተጋረደ የፍቅር መንፅሯ የተነሳ የማይታያት በምንም መለኪያ የማይደረስባት ጥልቅ ፍቅር ናት!of course ሰውነቷ ተዓምር ነው።እንደሷ የሚያምር ሌላ ታውቃለህ?እህትና ሚስትነቷ ሂደት ነው….መድረሻዋ እናትነት!!የእህትነት አብሮነቷ፣የፍቅረኛነት የህይወት ጥም አርኪነቷ በሂደት የእናትነት sublime ውበቷ መጠንሰሻዎች ናቸው።

የሙሉቀን ዜማዎች በሙሉ ስለሷ የተጠበቡ፤በምንም ዓይነት ስካር ደፍረው ቀሚሳን ያልነኩ ቅዳሴዎች ናቸው።

“ቤቷን አሰርታ ከቤቴ በላይ 
ዓይኗን እንኲ እንዳላይ አለብኝ ከልካይ
እፍ ብለው ጠፋ፤ባነደው ከሰለ፤
ከወዴት ይገኛል እሳን የመሰለ!
×××
በርግጥ አገኘሽ ወይ አገኘሽ ይሉኛል 
ስው በድሎ ሄዶ ደስታ መች ይገኛል
ክፉ ይንካሽ አልል ሀዘኑ የኔ ነው 
እንደተበደለ መሆንሽ ለምነው?
×××
አንቺ ደማም ጎኔ 
መጥተሽ አነጋግሪኝ ታሜአለሁ እኔ
×××
አዎ ኢትዮጵያዊት ወጣት የሆንሽ፤ኢትዮጵያዊት እናት የሆንሽ፤ኢትዮጵያዊ ጉብል፤ኢትዮጵያዊ መኲንንት/gentleman/ከያኒያችን ሌጀንዳሪው ሙሉቀን “ታሜአለሁ እኔ”እንሆ መልክት ልኮብሀል!!እሱ ከዚህ ቀጥሎ በጠየቀው መንገድ ብቻ ሳይሆን በአሜሪካ የምትኖር የኢትዮጵያ ሰው ሁሉ የየእጅህን ይዘህ የሙሉቀንን ቤት ወደ ባንክ ቤት ቀይረው!!በአዲስ አባ ደሀው ወገኔ ደምሴ ዳምጤ ቤት የቆርቆሮ የውጭ በሩን እየቆረቆሩ በመሀረባቸው ይቊጠሩትን እየፈቱ ሰጥተው የሄዱ እመበለቶችን አይቻለው!!እንደኮታቸው ያረጀ ቆብ ያደረጉ አባወራዎች ስኲር ዓይኑን ከልሎት ጋቢ ለብሶና ሶፋው ላይ ተቀምጦ ለሚጠብቃቸው የብሄራዊ ስፖርት አርበኛቸው ጎንበስ ብለው ጉልበቱን ስመው ከኮታቸው የውስጥ ኪስ የቊጠሯትን ሲሰጡት አይቻለሁ!!አደራ ወገኖቼ በሙሉቀን ስም የተከፈተ “go fund me “ውለታ-ቢስና ንፉግግነትን በሚያሳይ ሁኔታ እንዳያሳጣን አደራ!!!ብድር እንክፈል አደራ!!!ሙሉቀን ፍፍፍፍፍቅቅቅርርርርርር ነነነነህህህህ!!!!!!አይዞህ ወንድማለም!!!ኢትዮጵያ የምታኮራ ውለታ የማትረሳ እናት ናት..የእሷ ልጆች ነን!!!!!የእግዚአብሄር ጥበቃ አይለይህ! https://www.youtube.com/watch?v=QuGFWIW6xCg&sns=fb&app=desktop

Filed in: Amharic