>
3:17 am - Tuesday January 31, 2023

ምንም ቢሆን የዘንዶን ልጅ አላምደህ ቤትህን እንዲጠብቅልህ አታደርገውም!

                                                                              ከሚሊዮን አየለች

ዘንዶ በባህሪው አውሬ ነው። የሚፈለፍላቸውም ልጆች ዘንዶ እንጂ እርግብ ሊሆኑ አይችሉም።  አሁን ላይ ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ስርአታዊ ለውጥ እንጂ እየተቀደደ እንደሚሰፋ መልሰን እንደምናደርገው ኩታችን አልያም ሱሪ አይደለም።  ሁሉንም በአዲስ መልክ መቀየር ነው የሚገባን። አሁን አሁን ላይ የህውሀት ኢህአዲግ አጀንዳ ሆኖ ልህዝቡ እየሰጠው ያለው በመልሶ መጠቃት እንደገና ህዝቡን መቆጣጠር ነው። ይህ ያልገባው ኢትዮጵያዊ ደግሞ ሙክታርን በኦቦ ለማ ሲቀይር እና ሚኒስተሮቹን አንስቶ ከእውቀትም ከፖለቲካም ነጻ የሆኑ የዋህ ኢትዮጵያዊያኖችን ሲያስቀምጥ ኢህአዲግ የተቀየረ እየመሰለው እልልታውን ከጫፍ እጫፍ ያዳርሰዋል።

ኢትዮጵያውያን አንዳንድ አስገራሚና አብረቅራቂ ለውጥ ሲመጣባቸው ይህ ሆነው ከእግዚአብሔር ነው ወይስ ከሰይጣን ብለው ይጠይቃሉ። ከእግዚአብሔር ከሆነ የመጣው ለውጡ እንደሚፈልጉትና እንደአሰቡት ሀሳብ እንደሚሳካላቸው ስለሚያምኑ ነው። ከሰይጣን ከሆነ ግን ምንም አይነት አስገራሚ ለውጥ ያምጣ አውሬነቱን በምንም ምክንያት አይቀይርም። ከዛ ይልቅ አዘናግቶ ለክፋት ተግባሩ ቦታና ጊዜ አመቻችቶ ይጠብቃል እንጂ።
አንድ የመጸሀፍ ቅዱስ ታሪክ አለ። አዳምና ሔዋን አምላካቸው እግዚአብሔርን በሰይጣን ተንኮልና መጥፎ ተግባር ከካዱ በኌላ ተጸጽተው ከአምላካቸው ለመታረቅ በየፊናቸው ሱባኤ ይገባሉ። ሱባኤው የሚፈጅባቸው ጊዜ  በአጠቃላይ 40 ቀን ነበርና ልክ በሰላሳምስተኛው ቀን ሰይጣን እራሱ ብርሀናዊ መላእክ መስሎ በመምጣት ከእንግዲህ ወዲህ የሰራችሁት ክደትና ሀጥያት ተሰርዮላችሀልና እግዚአብሔር አምላካችሁም መጸጸታችሁንና ንስሀ መግባታችሁን አይቶ ስለተደሰተ ኑ እና ወደቀድሞ መኖርያችሁ ልወሰዳችሁ በማለት ይነግራቸዋል። እነሱም እኛ የያዝነው ሱባኤ ሊጠናቀቅ ገና አምስት ቀናት የቀሩናል ስለዚህ እስቱን ቀናት ልንጨርስ ይገባል ብለው ቢሞግቱትም እኔ የመጣሁን አምላካችሁ ልኮኝ ነውና እንዴት እኔን አታምኑኝም?… አምላካችሁ ይህንን ታሪክ የመቀየር ችሎታ የለውም እንዴ? ሲላቸው ከፊታቸው የቆመውን ብርሀናዊ መላእክ መስሎ የታያቸውን ሰይጣን በተናገረው ቃላት ተሽውደው ተከትለውት ሱባኤያቸውን አቜርጠው ወጡ። ጥቂት እርቀት ከተጔዙ በኌላ ብርኀኘ መልዐኽ የመሸላጨ ከመቅስፈት ጥልመታነቱን ተላብሶ ከፊታቸው ቆመና ያስጨንቃቸው ጀመር…
እንዲሁ ነው የዘመናችን ህውሀታዌው አስተሳሰብ ለይስሙላና ከላይ ለመታየት በህዝቡ ያጣውን የመመለክ እና በሀይል የመግዛት ነገር መልሶ ላማግኘት ሲል በየቦታው በራሱ አምሳል የፈለፈላቸውን የዘንዶ ልጆች በማስቀመጥና ኢትዮጵያውን ዳግም በሀይል ለማስጨነቅ የተለየ ስትራቴጄ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ነው። ይሄንን በሚገባ ልናውቀው ይገባል።
ኢትዮጵያ አሁን ላይ በአንድም በሌላም መልኩ የሚያስፈልጋን አጠቃላይ የስርአት ለውጥ ማድረግ ነው የስርአት ለውጡ ደግሞ ጥቂት ሰዎችን በማሸጋሸግና ህዝቡን የሚያታልሉ ቃላትና ድርጊቶች ከህዋታዊያን ስለመጣ የሚገኝ ነገር አይደለም ህውሀትም አጋር ብለው የተሰለፉት ኢህአዲግን የመሰረቱትም ድርጅቶች ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚገባውንና የሚፈልገውን ለውጥ ሊያመጡ አይችሉም።
ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት የስርአት ለውጥ ህገ መንግስቱን ከመቀየር አንስቶ የሚተዳደርበትን የፌደራል ስርአትን ከተራራላይ ፈጥፍጦ እስከመጣል የሚያደርስ ለውጥ ያስፈልገናል የምንመረባት የኢኮኖሚ ስርአታችን የደሀው ገበሬን መሬት እየመዘበረና ገበሬውን መሬት አክባ እያደረገ በኖረበት በተከበረበት ቀዬው ተመልሶ የሸጠው መሬት ላይ በዘበኝነት ለመቀጠር እየተገደደ ያለበተስርአት ነው ገበሬው ካለመደበት ካልኖረበት የከተማ ነሮ በግድ እንዲለምድ በማድረግ መድረሻ ያጣ ባይተዋር አድርጎታል። ከጥቂት ከተሞች የሚገኘው የማእድን ሀብታችንም ሌሎች ከተሞችን ከማልማት ይልቅ ለጥቂት ግለሰቦች ሀብት ማካበቻ የሆነ ኢኮኖሚ ነው ያለን። ጥቂቶች የሚበለጽጉባት በሀብት ላይ ሀብት እየደረቡ የተራውን ኢትዮጵያ ሀብት እየመዘበሩ እንዲኖሩ የሚያደርግ ኢኮኖሚ ሊቀየር የተገባ ነው። ከዛ በላይ ደግሞ ኢህአዲግ ከመጣ ጀምሮ ሀገሪተ አይታው በማታውቀው መልኩ ምንም ተጨባጭ መሰረታዊ ልማቶች በሌሉበት ሁኔታ ከዓለም ሀገራት የተበደርነው ብድር ሶስት ትውልዶች ከዚህ በሀላ መሰረታዊ ፍላጎታቸው ሳይመላ ዕንኴን ቢኖሩ ከፍለው የማይጨርሱት እዳ ውስጥ ተዘፍቃለች። በዚህም ሀገሪተን ዳግም  አቆርቁዞ ከማንኛውም ሀገር በታች እንድትኖር የሚያደርግ የኢኮኖሚ ግንባታ ስርአት ነው እየተከተለ ያለው። ስለዚህ ሊቀየር የሚገባው ስርአቱ ነው ስንል ወደን አይደለም። ስርአቱ ያመጣው ችግር አሁን ላይ ላለነው ብቻ ሳይሆን ከዚህ በኌላም ለሚመጣው ትውልድ እዳ አሸክሞ የሚያልፍ በእዳ የተያዘች ሀገር አድርጎ ነው ያስቀራት። ስለዚህ በዚህ ሁናቴ ውስጥ ሆነን የራሳቸውን ስልጣን ለማስጠበቅ እና በራሳቸው ዛቢያ ብቻ ለመዞር የሚዳዱትን ሹማምንቶቻችን ከወዲሁ ነቅተን ይብቃችሁ ልንል ይገባል። ሰው ቢቀያይሩ ስርአቱ ከነሙሉ ማንነቱ እስካልተቀየረ ድረስ የሚፈይድልን ምንም ነገር የለም። ሊቀየር የሚገባው ስርአቱን የገነቡት ሹማምንቶቹም ጭምር እና የሚከተሉት ስርአትም ጭምር ነው።

Filed in: Amharic