>

በዚህ አገዛዝ ምን የማይፈፀም አስነዋሪ ተግባር አለ?!! (ኢ/ር ይልቃል ጌትነት)

 ወጣቶች የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ምስል ያለበት መለያ በመልበሳቸው ለእስር ተዳረጉ!!!

በዘመነ መሳፍንት ተከፋፍላና ተዳክማ የነበረችውን ኢትዮጵያን ወደ አንድነትና ጥንካሬዋ ለመምለስ ታላቅ ራዕይ የነበራቸው ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ዛሬ ላለችው ኢትዮጵያ ዋልታና ማግር ሆነው መስረት የጣሉና በኢትዮጵያውያን ተከታታይ ትውልዶች ውስጥ የሙል ልብነትና አሽናፊነት ስነልቦንስን ያጎናፀፋ ንጉስ ናቸው። ህወሃት/ኢህአዲግ ደግሞ ከዚህ ተፃራሪ በሆነ መንገድ ከቅኝ ገዎች የወረሰውን ኢትዮጵያን በጎሳ ከፋፍሎና አዳክሞ የመግዛት ዘዴ ሥልጣን ላይ ተቀምጦ እየከፋፈላት እና እያዳከማት ይገኛል። ይህ አዋራጅ ተግባሩ ራሱ ወያኔንም አዳክሞ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን ስጋት ላይ ጥሉዋል። ይሁን እንጅ በዚህ ውጥን ቅጥና አስጨናቂ ዘመንም ቢሆን የእነዚያ ታላላቅ ሰዎች ሃሳብና ተግባር እርሾ ሳይጠፋ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ወጣቶች ልብ ውስጥ አድሮ እያየነው ነው። እነዚህ ወጣቶች ከታሪክ እና ከእውነት ጋር በተጣላ የጨለማ ዘመን ውስጥ እየኖሩ በልባቸው ባለው የብርሃን ጭላንጭል አባቶቻቸውን መዘከራቸው እጅግ የሚያኮራ ተግባር ከመሆኑም በላይ ለአባቶቻቸው ክብር የለበሱትን መለያ በጠብምንጃ ተገደው እንዲያወልቁ ቢጠየቁም የሚደርስባቸውን እያወቁ እምቢ ማልታቸው እገሩን ለሚወድ እና ዋጋ እየከፈለ ላለ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ትልቅ ተስፋና የመንፈስ ብርታትን የሚሰጥ አኩሪ ተግባር ነው። የአገራችን እጣ ፈንታ በእነሱ እጅ ነውና እግዚአብሔር የወጣቶችን መንፈስ ያፅናልን።

Filed in: Amharic