>

ህወሓት ልትነጣጥለን ስትጥር የበለጠ ተጋመድን!! (ሃብታሙ አያሌው)

ኦላን ይዞ

ከመሐል ያለው ዬናታን ወልዴ ከዳር የሺዋስ አሰፋ፤ ማዕከላዊ እኔ ሰባት ቁጥር ዮናታን ዘጠኝ ቁጥር የሺዋስ ሦስት ቁጥር ነበርን። ቂሊንጦ ወህኒ ቤት ስንወርድ ሁላችንም አንድ ዞን ተመደብን ዞን ሶስት፤ እኔ ሁለተኛ ቤት የሺዋስ ሰባተኛ ቤት ዮናታን ስድስተኛ ቤት። ከኛ ቀደም ብለው ከታሰሩት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን መካከል ከእኛ ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ ሶስቱ የተመደቡት ዞን ሶስት ነበር።

ዞን ሶስት አጠቃላይ ስምንት ቤቶች ነበሩት አኔ በተመደብኩበት 2ኛ ቤት ናትናኤል ፈለቀ (በእስረኛ አጠራር
ናቲ የደሃ አባት)፤ ዬናታን በተመደበበት 6ኛ ቤት ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዬርጊስ፤ የሺዋስ በተመደበበት 7ኛ ቤት ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ አስቀድመው ተመድበው ጠበቁን። የሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አመራሮች ከነበሩት መካከል አህመዲን ጀበል፤ ሼህ መከተ ሙሄ ፤ እና ከትላንት በስቲያ የተፈታው ጋዜጠኛ ዳርሰማ ሶሪ፤ 6ኛ ቤት ዬናታን ክፍል አህመድ ሙስጠፋ እና መሐመድ አባተ የሺዋስ ክፍል ሳቢር ይርጉ ተሰይመው ነበር።

መቼም ህወሓት ለፍርሃቷ ልክ የላትም በሶስት ከፍል አስልታ የመደበችን ለስለላ እንዲያመቻት ነበር። ህወሓት አስራ እንኳን የማታምን ስትባንን የምታድር ድርጅት ናት። በእስር ቤት እስረኛ መስለው ወይም እውነተኛ እስረኛ ቢሆኑም ተገዝተው የሚሰልሉ በእስር ቤት አጠራር (አስጠጪ ) ይባላሉ፤ ያስጠጡን አላፅፍ አላናግር ያሉን በመከራ ፅፈን ያጠራቀምነውን ያስቀሙን የማታ ማታ የእጃቸውን አገኙ፤ ዝርዝሩን ጊዜው ሲደርስ እመለስበታለሁ። ህወሓት ግን ከየቦታው ሰብስባ ልታፈርሰን ስታስብ ተሰራን ልትነጣጥለን ስትጥር የበለጠ ተጋመድን።
በእስር ያሉ ነፃ ወጥተው እስክንገናኝ
እንናፍቃለን !!

Filed in: Amharic