>

ለመሆኑ ፣ሕዝብ ምንን መቼና እንዴት መስማት አለበት? ብሎ ነፃነትን በራሽን ለማደል ለነዘረዓይ ዉክልና የሰጠዉ ማነዉ? (በፈቃዱ ሞረዳ)

አራት ኪሎ እኮ ለኦሮሞ ወጣት ቢያንስ የአያት ቅድመአያቱ መቃብር ቤት ነዉ፡፡ ምን አለ ቢሸልልበት? መጤ ወራሪስ ይርመሰመስበት  የለ?(ወያኔን ማለቴ ነዉ እሺ?)
ለመሆኑ ፣ሕዝብ ምንን መቼና እንዴት መስማት አለበት? ብሎ ነፃነትን በራሽን ለማደል ለነዘረዓይ ዉክልና የሰጠዉ ማነዉ?
ከእንግዲህስ ሕዝብ ስለመብቱ የእነዘረዓይን ቡራኬ ይጠብቃል ባይ ማነዉ? ያ ዘመን እየመሸበት መሆኑን ንገሩልን እባካችሁ፡፡
‹‹ የጎንደር ሰዎችን ወደትግራይ ጉዞ አስመልክቶ የአማራ ቴሌቭዥን ዜና ተዘጋጅቶ ተሰጥቶት አላስታለልፍም አለ›› ይላል ዘረዓይ፡፡
ዜና በማዕከል ከዘረዓይ ቢሮ ነዉ እየተዘጋጀ የሚታደለዉ?የአማራ ክልል ቴሌቪዥን ደግ አደረገ፡፡ የአማራ ሕዝብ መስማት ስላለበትና
ስለሌለበት ዜና የእነዘረዓይ ፍቃድ አያስፈልገዉም፡፡ ምን አለበት ይኼን ጉዱን እንኳን ቅጠል አልብሶት ቢያልፍ?
ሚሚ ስብሃቱንም ‹‹ ማንን ከጀርባሽ ተማምነሽ እንደሆነ እናዉቃለን…›› አላት መሰል፡፡
ምቀኝነት፡፡ ‹‹ሚሚና አዜብ መስፍን አብረዉ ይጠጣሉ፤ አብረዉ ሺሻ ያጨሳሉ›› ብሎ እኮ ነዉ፡፡አሁንስ ይህች አዜብ ወርዶባት፡፡ የመለስ ሚስት መሆን ኃጥያት ነዉ እንዴ? ሚሚን እንኳን ምንም አያደርጋትም፡
፡ እርሷን በአዜብ ምክንያት ቢጠምዳት ባሏ ዘርይሁን ተሾመ የስብሃት ነጋ ሕልም ተርጓሚ ፣ ቺካ ከዳሚ እስከሆነ ድረስ አኩና ማታታ፡፡
ዘረዓይ አስገዶም የብሮድካስቲንግ ኤጄንሲ ሥራ አስኪያጅ፤ አርአያ ገ/እግዚአብሔር የብሔራዊ ፈተናዎች ዳይሬክተር( እንዲያዉ አፌ
ላይ መጥቶ ነዉ) የእንትና የበላይነት የለም እንጂ ቢኖርማ ኖሮ፣ ጉድ ሆነን ነበር ዘንድሮ፡፡
Filed in: Amharic