>

የወንበዴው ወያኔ የጭንቅ አማካሪዎች የስብሰባ ጥሪ በደቡብ አፍሪካ ! (ኪሩቤል ካሳዬ - ዶ/ር)

“መሄድ እንኳን አልፈለኩም ነበር ግን የጀመርኩት ቤት አፈር ሊበላ ነው” :: ከስብሰባው ታዳሚዎች አንዱ ::
ዛሬ 27/01/2018 ከቀኑ ከ6: ሰዓት ጀምሮ የወያኔ ኢምባሲ የአዞ እንባውን ሊያዝረከርከው የልመና እንጉርጉሮ በዜማ ሸክፎ ከትላንትና 26/01/2018 ለየት ባለ መልኩ ምስኪኑን ስደተኛ በልመና ሊወጥር ሰዓት ቆርጠው በመጠባበቅ ላይ ናቸው :: የዛሬውን ለየት የሚያደርገው? እንደትላንትናው የሐይማኖት አባቶችን እና ፓስተሮችን ሳይሆን እንደአጠራራቸው ከሆነ ታማኝ አቀንቃኞቻቸውን … በውክልና …. በኮንዲሚኒየም….. በፍርድ ቤት ክስ ….. በሰራተኞች በወያኔ ተያዥነት ዘመድ ማስመጣት የሚፈልጉን ….. እንዲሁም ስደት ከብዶዋቸው አገራቸው መመለስ የፈለጉትን በሊሴ ፓስ ምክንያት ….. ያለምንም ታክስ ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ መላክ የሚፈልጉትን ….በገንዘብ ወይንም በትዳር አለመግባባት ተጣልተው ሚስጥራቸው የታወቀባቸው ምስኪኖችን … ተስፈኞችን …. ባልቴቶችን …. እና የመሳሰሉትን ናቸው::

አጀንዳ (1) ….. በእቁብ ወይንም በእድር መልክ ገንዘብ ማሰባብሰብ የሚቻልበትን ዘዴ መንደፍ (ለሕወሃት)

አጀንዳ (2)….. የተወሰነ ገንዘብ ያላቸውን የቦታ እና የባንክ ብድር ለማመቻቸት ቃል መግባት (የህወሃት አባል ማድረግ)

አጀንዳ (3) … በዘር ለተደራጁ ማህበራት የሪል እስቴት (የቤት) ጥናት ማቅረብ ቃል መግባት ( ሕወሃታዊ የክፍፍል ዘዴ ወጥመድ)

አጀንዳ (4) … በደቡብ አፍሪካ ያሉትን የሕዝባዊ ነጽኣነት ታጋዮችን ለይቶ በማወቅ ከተቻለ በመደለል ካለቻለ ደግሞ በተጠናጠል በተጠና ተንኮል ከስራ አለም በማራቅ በኢኮኖሚ በመደቆስ ከትግል ማደናቀፍ

አጀንዳ (5) ላለፉት 4 አመታት በታታሪነት ለሕወሐት ያገለገሉ ባንዳ የወንበዴ ልጆችን መምረጥ መሾም::

ይህን እና መሰል አጀንዳኦችን ይዘው እንደሚቀርቡ ተሰምቷል:: እግረ መንገዳቸውንም ግብጽ የምታመጣውን ችግር መቋቋም ከቶ እንደማይችሉ እና ትላንትና ለሰበሰቧቸው ፓስተር እና ቄስ መሰል ፖለቲከኞች ጋር አብሮ ለመስራት መማማላቸውን ዛሬ ለጠሩት ምስኪን አገር የለሽ ስደተኛ ለመናገር እንደሆነ ተደርሶበታል::

በኢትዮጵያ ኢምባሲ ውስጥ የተሰበሰቡት የወያኔ ስራ አስኪያጆች ትላንት ማታ በነበራቸው አጭር ስብሰባም በተቻላቸው መጠን የመጣውን ማንኛውም ተሰብሳቢ ፎቶ ግራፍ በማንሳት የራሳቸው የፌስ ቡክ እና ዌብ ሳይት ላይ በመለጠፍ ከሕብረተሰቡ ጋር አብረን እየሰራን ነው ብሎ ለመደስኮር እንደሚረዳቸው እና ይህ አንደኛው የውስጥ አሰራር ዘዴ እንደሆነ ተደርሶበታል ::
ድል የህዝብ ነው ( ሞት እና ውርደት ለሕወሐታዊያን በሙሉ )
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !

Filed in: Amharic