>
9:15 pm - Wednesday February 8, 2023

ታላቅ አደራ በታላቅ ሰው !! (ይድነቃቸው ከበደ)

የኔታ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም !
በጀግኖቻችንን ቤት በመገኘት እንኳን ከእስር ተፈታችሁ በማለት አባታዊ መልእክታቸውን አሰተላልፈዋል። እጅግ በጣም ትሁት የሆነው ፤ እውቁ ፓለቲከኛ አንዱዓለም አራጌ ፣ እንዲሁም አለም አቅፍ ታዋቂ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ፤ ከእስር መፈታታቸው አስመልክቶ በመኖሪያ ቤታቸው በመገኘት እንኳን ደስ አላችሁ ያሉ ሲሆን ፤ በነበራቸው አጭር ቆይታ እጅግ በጣም ሚዛን የሚደፋ ሃሳቦችን አንስተው ተነጋግረዋል። በስተመጨረሻ ጀግኖች አባቶቻችን እና እናቶቻችን መሰዋዕትነት የከፈሉበት የእናት ሃገር ኢትዮጵያ መለያ ባንዲራ በክብር ለጀግኖቻችን በአደራ ሰጥቷል።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!
Filed in: Amharic