የባልደራስ ፕሬዚደንት እስክንድር ነጋ ከእስር ተፈቱ !!! (ኢትዮጲስ)

የባልደራስ ፕሬዚደንት እስክንድር ነጋ ከእስር ተፈቱ !!!

(ኢትዮጲስ፤ አዲስ አበባ )
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ፕሬዝደንት እስክንድር ነጋ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ ከእስር ተፈተዋል።  ከበላይ የመንግስት አካል በመጣ ትዕዛዝ  መፈታታቸውም ታውቋል።
በተመሳሳይ የእስክንድር ነጋን ጉዳይ ለመከታተል በአዲስ አበባ ኮልፌ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው የኢትዮጵስ ጋዜጣ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ቢንያም ዓሊ ለጥቂት ጊዜያት በፖሊስ መምሪያው ታግቶ ቆይቶ ተለቋል። ቢኒያም የታገተው ‘አካባቢውን በምስል ቀረፅህ’ በሚል ምክንያት ነበር።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.