ሙስሊሙን ማህበረሰብ ዛሬም እንደ  ትላንቱ መሸንገል ይብቃ….!!! (አብዱረሂም አህመድ)

ሙስሊሙን ማህበረሰብ ዛሬም እንደ  ትላንቱ መሸንገል ይብቃ….!!!

አብዱረሂም አህመድ

ከተምር በላይ በቤተመንግስትም በትልልቅ ሆቴልም ረመዷንን  አስፈጥረውን ነበር :: ነገር ለሙስሊሙ ማህበረሰብ አንዳች ጠብ ያለለት ለዘመናት ብዙ ዋጋ የከፈለለት ተቋም ሽባ ከመሆን አልዳነም :: ሁሉን አቃፊ የሆነው ጠንካራ መጅሊስ ዛሬም ምንም የተለወጠ ነገር የለም :: ሙስሊሙ ኡማ እምነት ጥሎበት ለሀገር እድገት አስተዋፆ እንዳያደርግ ተቋሙን ሽባ አድርጎ ለማስተካከል የሚጥሩ ኡለማዎችን  ገፍቶ ለኢፍጣር ተምር ሰጠ አሳዛኝ ቀልድ ነው :: የኡማውን አማና ልወጣ ያሉት ሼይኽ ሂዝቡሏህ ለጠቅላላ ጉባዔ በመጡበት ተጉላልተውና ተንከራትተው መሞታቸውስ እንደምን ይረሳል ?
 
ለራሱ ምርጫ የሙስሊም ኡለማዎችንና ምሁራንን ጭምር ፖርቲየን ወክላችሁ ካልተወዳደራችሁ ብሎ  ግፊት ሲያደርግ የነበረ ተቋሙን ሽባ እያደረገ መቀለድ አስገራሚ ነው ::
ለማንኛውም ሁሉንም በልኩ ሁሉንም በመልኩ እንነጋገራለን !
 
አስፈጥራለሁ ካልክም በየቦታው በተነሱ  ግጭቶች የሚበሉት የሚጠጡት ያጡ በየቦታው ወድቀው አሉ እንደ መንግስት ለነሱ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደርስ አድርግ
ይኼው ነው !  ሙስሊሙ ህብረተሰብ መቀለጃችሁ የፖለቲካ አጀንዳችሁ ማስቀየሻ አይደለም !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.