ሙስሊሙን ማህበረሰብ ዛሬም እንደ ትላንቱ መሸንገል ይብቃ….!!!
አብዱረሂም አህመድ
ከተምር በላይ በቤተመንግስትም በትልልቅ ሆቴልም ረመዷንን አስፈጥረውን ነበር :: ነገር ለሙስሊሙ ማህበረሰብ አንዳች ጠብ ያለለት ለዘመናት ብዙ ዋጋ የከፈለለት ተቋም ሽባ ከመሆን አልዳነም :: ሁሉን አቃፊ የሆነው ጠንካራ መጅሊስ ዛሬም ምንም የተለወጠ ነገር የለም :: ሙስሊሙ ኡማ እምነት ጥሎበት ለሀገር እድገት አስተዋፆ እንዳያደርግ ተቋሙን ሽባ አድርጎ ለማስተካከል የሚጥሩ ኡለማዎችን ገፍቶ ለኢፍጣር ተምር ሰጠ አሳዛኝ ቀልድ ነው :: የኡማውን አማና ልወጣ ያሉት ሼይኽ ሂዝቡሏህ ለጠቅላላ ጉባዔ በመጡበት ተጉላልተውና ተንከራትተው መሞታቸውስ እንደምን ይረሳል ?
ለራሱ ምርጫ የሙስሊም ኡለማዎችንና ምሁራንን ጭምር ፖርቲየን ወክላችሁ ካልተወዳደራችሁ ብሎ ግፊት ሲያደርግ የነበረ ተቋሙን ሽባ እያደረገ መቀለድ አስገራሚ ነው ::
ለማንኛውም ሁሉንም በልኩ ሁሉንም በመልኩ እንነጋገራለን !
አስፈጥራለሁ ካልክም በየቦታው በተነሱ ግጭቶች የሚበሉት የሚጠጡት ያጡ በየቦታው ወድቀው አሉ እንደ መንግስት ለነሱ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደርስ አድርግ
ይኼው ነው ! ሙስሊሙ ህብረተሰብ መቀለጃችሁ የፖለቲካ አጀንዳችሁ ማስቀየሻ አይደለም !