>

ከተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ለመጀመርያ ግዜ ቀና የሆነ መግለጫ ተሰጠ..!!  (ደጀኔ አሰፋ)

ከተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ለመጀመርያ ግዜ ቀና የሆነ መግለጫ ተሰጠ..!!
 ደጀኔ አሰፋ

 

የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም/ቤት (UNSC) በኢትዮጵያ ጉዳይ ዛሬ ሚያዚያ 14/2013 ቀና መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫውም…፦
 
የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሰብዓዊ ዕርዳታ እያደረገ ላለው ከፍተኛ ጥረት እውቅና ሰጠ! (ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው!)
 
የፀጥታው ም/ቤት አክሎም እርዳታው ለሁሉም ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ እንዲዳረስ ይቻል ዘንድ የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ተጨማሪ የቁሳቁስ ድጋፍ ለኢትዮጵያ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል፡፡
 
ም/ቤቱ አክሎም፦ ትግራይ ውስጥ የሚሰሩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የአለም አቀፍ የሰብዓዊ መርሆዎችን ማለትም ሰብአዊነትን፣ገለልተኛነትን፣አድሏዊ አለመሆንን እና ነፃነትን ያከበሩ ሊሆን ይገባል ብሏል:: የተባበሩት መንግስታት (የ UN) የእርዳታ ጥረቶችም እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል!
 
ም/ቤቱ ይህን ካለ በኃላም… ከዚህ በፊት ሲባሉ የቆዩና የኢትዮጵያ መንግስትም ብዙ ያሳካቸውን ጉዳዮች (ለእኛ ምንም ማለት ያልሆኑ) ጥያቄዎችን አቅርበዋል
 
➢ለሰብዓዊ እርዳታ ክፍት እንዲደረግ (unhindered access) :- ክፍት ካደረግን ቆይተናል (March 3rd)
➢በትግራይ የተፈጠረው የፀጥታ ችግር ቀጣይ የሰብአዊ እንቅስቃሴዎች ላይ እንቅፋት ሊሆኑ እንደሚችሉ በመግለፅ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ​​(normalcy) እንዲመለስ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ (ይሄም እየሰራንበት ነው!!)
➢የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና የመብት ጥሰቶችን (በሴቶች እና ህፃናት ላይ) የፈፀሙ ጥፋተኞችን ለማጣራት እና ለፍርድ እንዲቀርቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ (ይህንንም ዶክተር አብይ በግልፅ ተናግሮታል)
➢ከዚህ አንፃር የ UN የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽ/ቤት እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በጋራ ምርመራ ለማካሄድ መስማማታቸውን የም/ቤቱ አባላት በደስታ መቀበላቸውን እና የአፍሪካ ህብረት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንም በዚህ ጉዳይ እየተሳተፈ መሆኑንም አድንቀዋል!!!!
.
አባል ሃገራቱ ይህን ካሉ በኃላም
 
የፀጥታው ም/ቤት ለቀጠናዊና ንዑስ ቀጠናዊ ተቋማት በዋናነት የአፍሪካ ህብረት እና ኢጋድ በቀጠናው ላይ የሚያደርጉትን ጥረት  እንደምናግዝ በድጋሚ አፅንኦት ሰጥተን እናስታውቃለን ብለዋል! “ይህ ማለት ግድቡን ሆነ የድንበር ውዝግቡን ለመፍታት አፍሪካ ህብረትን እንደግፋለን ከአፍሪካ ህብረት ጎን እንቆማለን እንደማለት ነው”!
 
በመጨረሻም እንዲህ ብለዋል
 
The members of the Security Council reaffirmed their STRONG commitment to the SOVEREIGNTY, POLITICAL INDEPENDENCE, TERRITORIAL INTEGRITY and UNITY OF ETHIOPIA 🇪🇹 
 
የፀጥታው ም/ቤት አባላት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ፣ ፖለቲካዊ ነፃነት ፣ ለግዛቷ አንድነት መከበር እና ለኢትዮጵያ አንድነት ያላቸውን ጠንካራ ቁርጠኝነት ዳግም አረጋግጠዋል!
Filed in: Amharic