>

አብይ በኢትዮጲያዊያን ላይ ከጅምሩ ያሰላው ስሌት ሀዲዱን የሳተ ነበር...!!! (አህመዲን ሱሌይማን)

አብይ በኢትዮጲያዊያን ላይ ከጅምሩ ያሰላው ስሌት ሀዲዱን የሳተ ነበር…!!!

አህመዲን ሱሌይማን

*….አንድ መሪ ግን እንዴት አድርጎ ነገረ-አለሙን ቢያበለሻሽ ነው፣ ከ “ሙሴ”ነት ወደ ፈርዖን ነት በዚህ ፍጥነት ሊፈጠፈጥ የሚችለው? ምንስ ቢያደርግ ምን ቢሰራ ነው “አሻጋሪያችን” ከመባል “ገዳያችን” ወደ መባል በአንዴ የሚወርደው? 
 
*…. በነገራችን ላይ ንጹሀን ብቻ ሳይሆን ፕሬዝዳንት ይገደላል
ይድረስ ለጠቅላይ ሚኒስቴር፣
 
 
…አንተው እንዳሻህ ተብሎ በአብዛኛው Overwhelming majority በሚባለው በውስጥም በውጭም ባለ፣ አመኔታንና ይሁንታን አግኝቶ ሲያበቃ፣ ይሄን ሁሉ ድጋፍ እንዴት miscalculate ቢያደርገው ምን ያህል የከሸፈ ሒሳብ አድርጎ ቢያሰላው ነው በዜሮ የሚጣፋው? ዛሬ ይሄን ሕዝብ እየዛተ “እደመስሳችኋለሁ አታቅቱኝም” ለማለት ያበቃው እንዴት አድርጎ አያያዙን ሳይችልበት ቢሰብረው ነው? 
 
ከጅምሩ ሕዝብ እሱን በመደገፍ አላጠፋም። ሕዝብ እርሱ በተናገረው “እሺ እስካሁን የሰማነው ጥሩ ነው፣ እስኪ ቃልህን ወደ ተግባር ትለውጥ ዘንድ ዕድሉን እንስጥህ” ማለቱ ስህተት አልነበረም። ሕዝብ ይህን በማለቱ እርሱን ነበር ያሻገረው። ከትህትናው የተነሳ ግን ‘አይ አንተ ነህ አሻጋሪያችን’ አለው። ከዚህ በኋላ ቃሉን ቀርጥፎ በላው፣ የሕዝቡን እሺታ እንደ ፍራቻ አየው፣ የሕዝቡን ታዛዥነት እንደ ባርነት ቆጥሮ ጌታ ልሁንብህ አለው ይሄው እራሱ አሻጋሪያችን ተብሎ የተቀባው። የሙሴነት ካባ ቢሸለም አሽቀንጥሮ ጥሎ ፈርዖንነቱን ያወጀው፣ የእውነተኛ ውስጡን ገልጦ ማንነቱን ያሳየው አብይ አህመድ እራሱ ነው። አብይ እራሱን በእራሱ ጠልፎ ነው፣ በሙገሳ አብጦ ነው፣ በኋይሉ ተመክቶ ነው ዛሬ የተነፈሰው፣ በሕዝብ ያስጠላው ልወደድ ባይነቱ ነው፣ አስመሳይነቱ፣ በጣም ገብጋባነቱ ነው። ያየውን ሁሉ ኬኛ ማለቱ ነው። የማያደርገውን በመናገሩ ውሸታም በመሆኑ ነው። የገባውን ቃል ባለመጠበቁ፣ የሰው ልጆች መከራ፣ የእናቶችና የአዛውንቶች እምባ ምንም ሆኖ ያልታየው በመሆኑ ነው። 
 
አብይ በኢትዮጲያዊያን ላይ ከጅምሩ ያሰላው ስሌት ሀዲዱን የሳተ ነበር። ያዛልቀኛል ያለው ለዘመናት ያስነግሰኛል ብሎ የጎነጎነው ትብታቦ የሸረሪት ድር ነበር። 
 
በመጪው ምርጫ በጥይትም በቆመጥም ብሎ 90 በመቶ 95 በመቶ አሸንፌያለሁ ይላል፣ ይላል ይሄ አፍሪካ ነዋ። ግን በቃ ተነቃንቋል። የተነቃነቀ ደግሞ የጊዜ ጉዳይ እንጂ መውደቁ አይቀርም። የገረመኝ ይሄን ሁሉ ድጋፉን የናደበት ፍጥነት ነው።
 
 
የቻድ ፕሬዜዳንት ተገደሉ።
ላለፉት 30 ዓመታት ቻድን የመሩት ፕሬዝደንት ኢድሪስ ዴቢ በአማጺ ኃይሎች መገደላቸውን የሀገሪቱ መከላከያ ማስታወቁን አል ዓይን ዘግቧል።
 
ፕሬዝደንቱ የመንግስት ኃይሎች ከአማጺያን ጋር እያደረጉ ባለው ጦርነት ተመተው መገደላቸውን ነው መከላከያ ሠራዊቱ በሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ይፋ ያደረገው፡፡ 
 
ፕሬዝደንቱ በውጊያው ከቆሰሉ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ነው ህይወታቸው ያለፈው፡፡
 
ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ ፣ በቻድ ምርጫ እስካሁን ከተቆጠረው 80 በመቶ ድምጽ ከ79 በመቶ የሚሆነውን በማግኘት ማሸነፋቸው በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኖ ነበር፡፡
 
የቻድ አማጺያን በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ዋና ከተማዋ ኒጃሚና ከትናንት ጀምሮ በመቅረብ ላይ እንደነበሩ የሚገልጹ መረጃዎች ወጥተው ነበር፡፡
********
ይድረስ ለጠቅላይ ሚኒስቴር፣
 
ይህም ይገጥማል ለማለት ነው፣ ቤ/መንግሥት ደረትህን ነፍተህ በማንአለብኝነት እንሰባብረዋለን ማለት አያዋጣም። በቀይ ኮፍያ ለባሽ ወታደሮች ተከቦ መደንፋት ከመደፋት አያድንህም። Remember, This is Africa!! ነገሩ ይሄ በየትም ቦታ ይሆናል። ወጥ ረግጥሀልና ጭራህን በጊዜ እግሮችህ መሀል ቆልፈህ ወደ ቀልብህ ተመለስ ለማለት እወዳለሁ።
Filed in: Amharic