>
5:21 pm - Thursday July 20, 9324

ከሸዋ የአማራ ሕዝብ  ተጋድሎ አሰተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ  መግለጫ...!!!

ከሸዋ የአማራ ሕዝብ  ተጋድሎ አሰተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ  መግለጫ…!!!


እንደሚታወቀው በ አማራው ህዝብ እንቢተኝነት የመጣው ለውጥ ተብዬ ለአማራው ህዝብ ለውጥ ሳይሆን ነውጥ ይዞበት መቶ ይኸው እስካሁን ድረስ ማህበራዊ እረፍት አጥቶ በየቦታው እየተገደለና እየተፈናቅለ ይገኛል። 
ስለሆነም ይህ የዘር ማጥፋት ወንጀል ይቆም ዘንድ ይመለከተዋል ለተባለው አካል በተደጋጋሚ ቢጮህም ጩኸቱ እንደ ሙዚቃ ተቆጥሮ  ከመፍተሄ ይልቅ ችግሮች ከቀን ወደ ቀን እየከፉ በመሄዳቸው የሸዋ ህዝብ የማይጠፋ የትግል ችቦውን ለኩሷል።
ዱሮውንም ዶሮ በረጅሙ ሲያስሯት የፈቷት ይመስላታል ይሉ ዘንድ አበው እኛ ከቀን ወደ ቀን ትሻሻላላችሁ ፤ ትለወጣላችሁ፤  ግብር እየከፈለ  የሚያኖራችሁን ህዝብ ታገለግላላችሁ ብለን ብንመክር ብናስመክር በሰላማዊ ሰልፍ ብንናገር ልትሰሙን አልቻላችሁም።
ጭራሽ የተላላኪነት መንፈሳችሁ ጭንቅላታችሁ ውስጥ እንደ ጋንግሪን አድጎ ሊሻሻል እና ሊለወጥ የማይችል ደረጃ ላይ መድረሱን ታበስሩን ጀመር።
በመሆኑም ይህን አስመልክቶ  የደብረብርሃን እና አካባቢዋ ነዋሪዎች የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥተናል።
1) እስካሁን በተለያዩ አካባቢዎች ሲፈጸሙ የነበሩና አሁንም እየተፈጸሙ ያሉ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች መንግስታዊ መራሽ መሆናቸውን የአለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲያውቅልን እንፈልጋለን።
2) እስካሁን በግብር እና በታክስ ስም የምንከፍለው ገቢ ሃገር ከማልማት ይልቅ፤ ማጥፋት ህይወት ከማዳን ይልቅ መግደል፤ ከስላም ይልቅ ሽብር እየተፈጸመበት ስለሆነ እንደ አስፈላጊነቱ ግብር ያለ መክፈል እንቢተኝነት እንጀምራለን።
3) ህዝቡን በማይጠቅም ቢሮክራሲ እና በተጨማለቀ ወያኔ ወለድ መመርያ እና ህግ መሰል ጥልፍልፍ የማንገዛ መሆኑን እናሳውቃለን።
4) እየታረድን እየሞትን እና እየተፈናቀልን የምንኖርበት ሁኔታ ስለማይኖር ራሳችንን በመከላከል ማንኛውም ሁኔታውስጥ ለሚፈጠር ቀውስ ራሱ ህግ አስከባሪ ነኝ የሚለው አካል ሀላፊነትን ይወስዳል።
5) በሸዋ ላይ ልዩ ዞን የሚባል የዳቦ ስም ተሰቶት ለአማራው መታረጃ እና ቄራ የሆኑ  ርስቶቻችንን መልሰን የእኛ ለማድረግ እምደምንሰራ እናሳውቃለን።
6) በ ኮማንድ ፖስት ስም አማራው ከፈጣሪው ቀጥሎ መዳኛው የሆነውን ነፍጡን ለማስወረድ የሚደረግን ማንኛውም እንቅስቃሴ የምንቃወም መሆኑንና ትጥቅ እናስፈታለን የሚል ቅዠታችሁ እንደማይሰራ እናሳውቃለን።
7) ሰሞኑን በሰሜን ሸዋ ወረዳዎች ማለትም ኤፍራታና ግድም፣ ቀወት እና አንፆኪያገምዛ ከጥይት ተርፈው የተፈናቀሉ ወገኖች የአስቸኳይ እርዳታ በማድረግ ወደ ቀያቸው  እንድትመልሱ እናሳስባለን። ይህን በቸልታ የማታደርጉ ከሆነ ግን ወደ ሌላ የትግል ምዕራፍ እንደምንሸጋግር እናሳውቃለን።
ትመሩናላችሁ ብለን ብንተዋችሁም መምራት ስላቃታችሁ በመምራት ሂደት ውስጥ አጋዥና አስተባባሪ አካል ስለሚያስፈልግ የጎበዝ አለቃ እንዳለ እናሳውቃለን።
9)ማንኛውንም ወጣትን እንዲሁም የጎበዝ አለቃን በተናጠልም ይሁን በቡድን ለማሰር እና ለማስፈራራት ሙከራ ለማድረግ የሚሞክር አካል ላይ እርምጃ የምንውስድ  መሆኑን አስረግጥን መናገር እንፈልጋለን።
 ከሸዋ የአማራ ህዝብ አሰተባባሪ ኮሚቴ
 ሚያዚያ 14/08/2013 ዓ.ም
 ሸዋ ደብረ ብርሃን!!!
Filed in: Amharic