>
5:22 pm - Saturday July 21, 3866

"ህውሓት ሰርጎ በገባባቸው አካባቢዎች ሁሉ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት መጋዘኖች ዘርፏል...!!!" የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት

“ህውሓት ሰርጎ በገባባቸው አካባቢዎች ሁሉ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት መጋዘኖች ዘርፏል…!!!”

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ
(ኢ ፕ ድ)


አሸባሪው ህወሓት የአሜሪካ ተራድኦ ደርጅት መጋዘኖችን እንደዘረፈ በኢትዮጵያ የድርጅቱ ሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ተናገሩ፡፡

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ ህወሓት ሁኔታውን ያለአግባብ እየተጠቀመበት እንደሆነ እናምናለን ብለዋል፡፡

ከተረጂዎች ላይ እርዳታን በሃይል እየነጠቀ እንደሆነ ይሰማናል ያሉት ዳይሬከተሩ እርግጠኛ ሆነን መናገር የምንችለው ግን የአሸባሪው ህወሓት ቡድን አባላት ሰርገው በገቡባቸው አካባቢዎች ሁሉ ያሉትን የእርዳታ መጋዘኖቻችንን ዘርፈዋል፤ ይህ የምናውቀው ሀቅ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አሁን በግልጽ የምናውቀው ነገር የህወሓት ወታደሮች በገቡባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ሁሉ የእርዳታ መጋዘኖችን ዘርፈዋል፣ መኪኖችን ሰርቀዋል በየመንደሮቹ ብዙ ውድመትን አድርሰዋልያሉት ዳይሬክተሩ ይህ ለተጎጂዎቹም ሆነ ለእኛ ለረጂዎቹ እጅግ አሳሳቢ ነው ብለዋል፡፡

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ኢትዮጵያ ውስጥ የምንቀሳቀሰው ሀገሪቱ አሁን ችግር ላይ ስላለች አይደለም ብለዋል፡፡

ይልቁንም ኢትዮጵያ ዓለም ላይ ካሉ ምርጥ አጋሮቻችን መካከል አንዷ ነች ያሉት ዳይሬክተሩ ከኢትዮጵያ ጋር ስላለን አጋርነት በእጅጉ እንጨነቃለን ነው ያሉት፡፡

አንዳንድ ጊዜ ህብረተሰቡ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን የሚሰራጩትን ያልተረጋገጡ ወሬዎች በመያዝ የኢትዮ አሜሪካ ግንኙነት እንደሻከረ ያስባሉ ያሉት ዳይሬክተሩ ነገር ግን እንደአሁኑ ከኢትዮጵያ ጋር ተባብረን የሰራንበት ጊዜ የለም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

Filed in: Amharic