>

ህወሓት በኮምቦልቻ ከ100 በላይ ደሴ ከ150 በላይ  የከተማዋን ወጣቶች መጨፍጨፉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ

የአሸባሪው ህወሓት ሀይል  በኮምቦልቻ ከ100 በላይ ደሴ ከ150 በላይ  የከተማዋን ወጣቶች መጨፍጨፉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ
(ኢ ፕ ድ)

የአሸባሪው ሕወሀት ሀይል በኮምቦልቻ ከተማ  ሰርጎ በመግባት ዛሬ  ሌሊቱን ከ100 በላይ ደሴ ከ150 በላይ የከተማዋን  ወጣቶችን አሰልፎ መጨፍጨፉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
የሽብር ሀይሉ ሰርጎ በገባበት በደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች የግል እና የመንግስት ሀብቶችን እየዘረፈ እና እያወደመ ነው ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ተናግረዋል።
በቦርከና ዳዋ ጨፌ አካባቢዎች ሕወሀት እየመጣ ነው በሚል የአሸባሪው ሸኔ ሀይል መንገድ የመዝጋት እና ሌሎች አፍራሽ ድርጊቶችን  ለመፈፀም ቢሞክርም በአካባቢው ወጣቶችና በጀግናው መከላከያ ሰራዊት አላማው ከሽፎበታል ብለዋል።
መከላከያ ሰራዊቱ በክህደት የተፈጠሩበትን የውጊያ መዛነፎች እንደገና በማስተካከል አሁንም ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረገ ይገኛልም ተብሏል።
“መንግስት ተዳክሟል፣ ሕወሀት አሸንፎ እየመጣ ነው” በሚል ደሴ ላይ እንደተፈፀመው ሁሉ አዲስ አበባን ጨምሮ ወደ ጭፈራ የገቡ ሀይሎች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባም አሳስበዋል።
እንድ ኢቢሲ ዘገባ፤ ይህንን አስመልክቶ መንግስት እርምጃ እየወሰደ ነው ብለዋል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትሩ።
Filed in: Amharic