ፓስተር ቢኒያም ታሰሩ…!!! (ዮሴፍ ይጥና)

ፓስተር ቢኒያም ታሰሩ…!!!

ዮሴፍ ይጥና

*…. በሃይማኖት ሽፋን ቅጥ ያጣው የተረኝነት አባዜ በየቀኑ ነውር እየፈለፈለ ቀጥሏል ። ደመነፍሳዊው መንጋ በዚህ የእውር ድምብር አካሄድም የጌታን ስም እየጠራ ደስታውን ሲገልፅ ማየት ያሸማቅቃል ። ይህ የለየለት ኤልዛቤላዊ ብልግና አክዓባዊ ድንቁርና ነው !!!
 
ለእነርሱ ያላጨበጨበ ፣ ለእነርሱ ያላሸረገደ ፣ እንደ እነርሱ ግጭት ያልቀሰቀሰ ፣ እንደ እነርሱ በስሜት ዳንኪራ ያልረገጠ ፣ እንደ እነርሱ በተረኝነት ያላበደ ፣ እውነትን የሚናገር ፣ ከተበደሉት ጎን የሚቆም ፣ በማስረጃ የሚሞግት ይታሰራል !!!
በሃይማኖት ሽፋን ቅጥ ያጣው የተረኝነት አባዜ በየቀኑ ነውር እየፈለፈለ ቀጥሏል ። ደመነፍሳዊው መንጋ በዚህ የእውር ድምብር አካሄድም የጌታን ስም እየጠራ ደስታውን ሲገልፅ ማየት ያሸማቅቃል ። ይህ የለየለት ኤልዛቤላዊ ብልግና አክዓባዊ ድንቁርና ነው !!!
ፓስተር ቢኒያም የያዘው እውነት ነው ። እውነት በመናገሩ ሲዝቱበት የነበሩ በርካቶች ናቸው ።እሱም ማንንም ሳይፈራ እውነትን የሙጥኝ አለ ። በተረኝነት የሰከሩር ቅርብ አዳሪዎች ፣ ከትላንት ገዢዎች ያልተማሩት ፣ በሃይማኖት ውስጥ የተሸሸጉ ወንበዴዎች ፣ በጌታ ስም የሚሸቅጡ ጋንግስተሮች ፣ በወንጌል ስም ወንጀል የሚፈበርኩ ጥጋበኞች ፓስተር ቢኒያምን አሳስረውታል ።
ተረኝነት እዚህ ደርሷል ፣ በሃይማኖት ሽፋን የተባባሰው እብደት ፈውስ እርቆት ቀጥሏል ።ሁሉን የሚያውቅ  ፣ በሁሉም ላይ የሚፈርድ እግዚአብሔር ደግሞ  ከመንበሩ ሆኖ እየተመለከተ ነው !!!
ወየው ለነጋችሁ !!! ይህ ጥጋብ ይበርዳል !!!
በሃይማኖት ስም የሚካሄድ ዘረኝነትና ተረኝነት የተወጋ ይሁን !!! አሜን !!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.