>

የፕሬዚዳንቱ መመሪያ "እንዳያማህ ጥራው እንዳይበላ ግፋው" እየሆነ ይመስላል!!! (ኢ/ር ይልቃል ጌትነት) 

ከኦሮሚያ ክልል በተለያየ ጊዜ ስለሚገደሉትና ስለሚፈናቀሉት አማራዎች ህዝብ እንዲያውቀው በመረጃ ይፋ በማድረጋችን የዶ/ር አብይና የአቶ ለማ ተከታዮች የስድብ ውርጅብኝ እና ስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍተውብን ከርመዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተፈናቀሉ ሰዎች በአካል በባህር ዳርና ወሎ በመጠለላቸውና መፈናቀላቸው በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በመዘገቡ እነ አቶ ለማ ችግሩ መኖሩን አምነው እርምጃ መውሰዳቸው ሰሞነኛ አጀንዳ ሆኑዋል። ይሁን እንጅ መሬት ላይ ያለው ሃቅ አሁንም እንዳልተቀየረና አማራዎችም ቀያቸውን ጥለው እንዲወጡ እየተደረጉ ነው።
 ዛሬ ሰኔ 9 ቀን 2010 ዓ.ም በቡኖ በደሌ ዞን ደዴሳ ወረዳ የአማራ አርሶ አደር ከብቶች በስለት መወጋታቸውንና ውጡ መባላቸውን ገልፀውልኛል። በትናንትናው ዕለት በተደራጁ ወጣቶች ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው እንደሆነና ሰብላቸውን መሰብሰብ እንዳልቻለሁ ለወረዳ አስተዳዳሪው አቶ በድሩ ሙዘይን በቃል አቤቱታ ቢያቀርቡም “እና እናንተ መሬቱን ለምን አትለቁም ” የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ነግረውኛል። በክረምት ሜዳ ላይ የሚወድቁ የአማራ ገበሬዎች ከፕሮፓጋንዳ ያለፈ የተግባር ምላሽ ያስፈልጋቸዋል።
Filed in: Amharic