>

አቶ ስዩም የህወሓት ወታደራዊ ኃላፊዎችን ጋር በሚስጥር እየመከረ መሆኑ ተስምቷል (ጌታቸው ሽፈራው)

አቶ ስዩም የህወሓት ወታደራዊ ኃላፊዎችን ጋር በሚስጥር እየመከረ መሆኑ ተስምቷል

ጌታቸው ሽፈራው

አቶ ስዩም መስፍን የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ ኃላፊዎች ጋር መቀሌ ላይ በሚስጥር እየመከረ መሆኑ ተሰምቷል። አቶ ስዩም 102 የሚሆኑ ከፍተኛ መኮንኖችን ሰብስቦ “ህገ መንግስቱን የመጠበቅ ሀላፊነት የእናንተ ነው። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ህገ መንግስቱን እያስከበረ አይደለም። በመሆኑም ሁኔታዎችን በንቃት መከታተል አለባችሁ” በሚል በሚስጥር እየመከረ መሆኑን ምንጮች ገልፀዋል።

ስብሰባው ለ3ኛ ቀን እየተካሄደ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን በጦረታ እና በቦርድ መልክ የተሰናበቱት የህወሓት የሰራዊት አባላትም መጠራታቸው ተመልክቷል።

Filed in: Amharic