የሱዳን ሰራዊት የኢትዮጵያ ገበሬዎችን ሰብል አወደመ
ጌታቸው ሺፈራው

የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን ከተሰጠ በኋላ ድንበሩን መጠበቅ ያቆመው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዛሬ ሰኔ 18/2010 ዓም ከቦታው በመድረስ የኢትዮጵያ ገበሬዎችን ወደኋላ እንዲመለሱ አድርጓል ተብሏል።
በተመሳሳይ በትናንትናው ዕለት በቋራ ወረዳ በሱዳን ጦርና በገበሬው መካከል ተኩስ እንደነበር ተገልፆአል። መሬታቸው ለሱዳን የተሰጠባቸው ገበሬዎች መሬቱን በኪራይ ሲያርሱ የቆዩ ሲሆን ከ2008 ዓም ጀምሮ “በራሳችን መሬት ኪራይ አንከፍልም” በማለታቸው ከሱዳን ጦር ተደጋጋሚ ጥቃት ሲፈፀምባቸው ቆይቷል። በአንፃሩ የኢትዮጵያ ጦር ድንበሩን በመጠበቅም ሆነ ገበሬዎችን ከሱዳን ጦር ጥቃት በመከላከል ተግባር ላይ እንዳልሆነ ተጠቁሟል።
