>

በግፈኞች የተገፉ የፍትህ ጀግኖቻችንን በፍቅር እንመልሳቸው!!! (አርአያ ተስፋማርያም)

በግፈኞች የተገፉ የፍትህ ጀግኖቻችንን በፍቅር እንመልሳቸው!!!
አርአያ ተስፋማርያም
ጠ/ሚ/ር ዶ/ር አብይ በከፍተኛ የለውጥ ሂደት እየተጓዙ ይገኛሉ! በዚህ ሂደት ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገቡ ሶስት ወሳኝ ጉዳዮች አንዱ የፍትህ ማለትም የፍርድ ቤቶች ነፃነት ዋነኛው ነው! የፍትህ ጉዳይ ሲነሳ ሁለት የፍትህ ጀግኖች ስማቸው በጉልህ ሊነሳ ግድ ይላል! ፈረንሳይ ለጋሲዮን ያፈራቻቸው ጀግናዋ ብርቱካን ሚዴቅሳና አለማየሁ ዘመድኩን ናቸው! ብርቱካን ከስራ ከመባረር ባለፈ ከፍተኛ እስር፣ እንግልትና ግፍ ተፈፅሞባታል። አለማየሁ ደግሞ ለእውነት ዘብ በመቆም ዋጋ ከፍሏል። ሁለቱም በስደት አሜሪካ ይኖራሉ። ብርቱካንም ሆነች አለማየሁ ነፃ የፍትህ ስርአት በኢትዮጵያ እንዲኖር የታገሉ እንጂ ስልጣን ፍለጋ አልነበረም! የፍትህ ነፃነት እንዲረጋገጥ ዶ/ር አብይ ትኩረት ሊሰጡ ይገባል ስንል ሁለቱን የፍትህ ጀግኖች ጠ/ሚ/ሩ ለብርቱካንና አለማየሁን ለመሰሉ ጥሪ አድርገው ባካበቱት ልምድና ችሎታ በፍትህ መድረክ የሚያገለግሉበት ሁኔታ እንዲያመቻቹ ጭምር ለመጠቆም ነው! የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትና የዶ/ር አብይ አማካሪዎች ወይም ቅርበት ያላቸው ወገኖች ለጠ/ሚ/ሩ ይህን ጥቆማ እንዲያደርሱ በዚህ አጋጣሚ ማስገንዘብ ያሻል!

Filed in: Amharic