>

ሕወሓት በአሶሳ ሲነቃበት በሱዳን ሰራዊት የውክልና ጦርነት ከፍቷል!!! (ጌታቸው ሽፈራው)

ሕወሓት በአሶሳ ሲነቃበት በሱዳን ሰራዊት የውክልና ጦርነት ከፍቷል!!!
ጌታቸው ሽፈራው
* በርካታ ቁስለኞች ግንደውሀ ፣ ሸንዲና ጎንደር ሆስፒታል ገብተዋል። የመከላከያ ሰራዊቱ ባላየ ድምፁን አጥፍቷል
 
* ከሱዳን ሰራዊት ጋር ሆኖ የአማራ ገበሬዎችን እየጨፈጨፈ ያለው ህወሓት መሆኑን ቁስለኞቹ አረጋግጠዋል
 
*80 % የሀገሩን በጀት ለሰራዊቱ የሚያውለው የሱዳን ወታደራዊ አገዛዝ ድንበር ጥሶ 70 ገበሬዎችን አፍኗል።
 
* የሕወሓት ሚሊሻዎች ከሱዳን ሰራዊት ጋር ተቀናጅተው በድንበር ላይ ያሉ ገበሬዎችን እያስገደሉ ነው
 
*  መከላከያ ሰራዊት ወደ ደንበር ቢጠጋም የኢትዮጵያ ገበሬዎች በሱዳን ጦር ሲዘመትባቸው ዳር ዳር ተመልካች ሆኗል
በሱዳን ጦር ከባድ መሳርያ ተኩስ ተከፍቶባቸው የቆሰሉት አማራ ገበሬዎች ገንዳውሃ የሚገኘው መተማ ሆስፒታል ገብተዋል።እስካሁን በሁለት አንቡላንስ የመጡ ቁስለኞች ወደ ሆስፒታል ገብተዋል ተብሏል።
ሕወሓት በአጋዚ አልበቃውም! በአልበሽር ጦር የአማራ ገበሬዎችን እያስጨፈጨፈ ነው። በአሶሳ ሲነቃበት በሱዳን በኩል የውክልና ጦርነት ጀምሯል። በአማራ ገበሬዎች ላይ!
የአማራ ገበሬዎችን እያስጨፈጨፈ ያለው ትህነግ ነው ከሱዳን ሰራዊት ጋር ሆኖ የአማራ ገበሬዎችን እየጨፈጨፈ ያለው ህወሓት መሆኑን ቁስለኞቹ አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ የመጣው የሱዳን ጦር ጋር ገጥመው የቆሰሉት በግልፅ ተናግረዋል። የገጠማቸው ሕወሓት ነው። እነሱ የሕዝብ ስም ጠርተው ነበር የተናገሩት። ላኪው ትህነግ/ህወሓት ነው በሚል ነው። ጦርነቱን መርቶ የአማራ ገበሬዎችን እየጨፈጨፈ ያለው ትህነግ/ህወሓት ነው!
ከቁስለኞቹ ባሻገር የልዩ ሀይሉ ሃላፊ ለገንዳውሃ ኃላፊዎች ጦርነቱን እየመራው የሚገኘው ሕወሓት ነው ብሏል። ገንዳውሃ ሆስፒታል 7 ቁስለኞች ገብተዋል
አምስቱ ገበሬዎች ሲሆኑ ሁለቱ በሱዳን መከላከያ እና በገበሬዎቹ መካከል “ሽምግልና” አርፍዶ ዘግይቶ የገባው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ናቸው።
ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ገበሬዎች እንዳሉ ታውቋል። ሁለቱ የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት ወደ ጎንደር ሆስፒታል እንዲላኩ “ሪፈር” እንደተባለላቸው ተገልፆአል።
ከደደሎ ወደ ገንዳውሃ የሚመጡ ተጨማሪ ቁስለኞች እንዳሉ ተገልፆአል።
ብዙ ቁስለኞች ሸኸዲ ሆስፒታል ገብተዋል!
ከቆሰሉት ገበሬዎች መካከል አበጀ አንዱ ነው። አበጀ የ37 አመት እድሜ ያለው ሲሆን ቋራ ወረዳ ቁጥር አራት ነፍስ ገበያ አካባቢ ነዋሪ ነው።
ከሱዳን ሰራዊት በተተኮሰ ከባድ መሳርያ ብዙ አማራ ገበሬዎች ተገድለዋል። ቆስለዋል።
የሱዳን ሰራዊት የሁለት ገበሬዎችን አስከሬን ወደኋላ አሽሽቷል። የጠፉ ገበሬዎች እንዳሉም ታውቋል።
የአማራ ገበሬዎች ወረራውን ሲመክቱ፣ ሲገደሉ ለበርካታ ጊዜ ከደንበር ርቆ ገበሬዎችን ለጠላት ጦር አሳልፎ ሲሰጥ የቆየው መከላከያ ሰራዊት በመጨረሻ ከሱዳን ጦር ጋር ለአጭር ጊዜ ውጊያ አድርጓል። እስካሁን ከአማራ ገበሬዎች ጋር በመሆን የሱዳን ወራሪ ጦር ሲከላከል የቆየው የአካባቢው ሚሊሻ ነው።
ዛሬ ሕዝብ በመኪና እየተጫነ ወደ ጦርነቱ መሄዱን የሰማው መከላከያ ከአጭር ጊዜ ከሱዳን ጦር ጋር ተታኩሶ እንደገና ገበሬው አጋፍጦ ተመልሷል ተብሏል።
ለአጭር ጊዜ በተደረገ ውጊያ ሁለት የመከላከያ አባላት ሲቆስሉ አንድ ተገድሏል ተብሏል። ገበሬዎቹ ሲዋጉና የሱዳን ሰራዊት መግደያ ቦታ ሲይዝ ዝም ብሎ ለጠበቀው መከላከያ ሰራዊት የሱዳን ጦር “ስትገለግል ነበር” ብሎ አልተወውም። የሱዳን ጦር ምቹ ቦታ በመያዙም መከላከያ ሰራዊት ለመግባት አልቻለም ተብሏል።
አሳፋሪው የ”ኢትዮጵያ መከላከያ” ሰራዊት በገዳዩ የሱዳን ጦር እና ከባድ መሳርያ በሚተኮስባቸው የአማራ ገበሬዎች መካከል ሽምግልና ጀምሯል።
የእነ ሳዕረው የመከላከያ ሰራዊት ሰሞኑን በአማራ ገበሬዎች ላይ ከባድ መሳርያ ሲተኮስባቸው ድምፁን አጥፍቶ ዛሬ ሽምግልና የጀመረው ሕዝብ የሱዳን ጦር ጋር ለመግጠው ወደ ደለሎ እየሄደ መሆኑን በማወቃቸው ነው።
የሱዳን ሰራዊት የሁለት አማራ ገበሬዎች አስከሬንን አልሰጥብም ብሏል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሚባለው የትህነግ ጦር ደግሞ ሕዝብ አስከሬን እንዳያስመልስ፣ ወደኋላ እንዲመለስ እየሸመገለ ነው።
በአሁኑ ወቅት የቆሰሉ ገበሬዎች በሁለት አንቡለንስ ወደ ጎንደር ከተማ እየተወሰዱ መሆኑም ታውቋል።
ትናንት ሰኔ 25/2010 ዓም ገበሬዎች ከሱዳን ሰራዊት ጋር ውሏቸውን ሲታኮሱ ውለዋል። የሱዳን ጦር አፈና የፈፀመባቸውን 70 ያህል ገበሬዎች ነፃ ለማውጣት በተደረገ ጦርነት ብዙ ገበሬዎች ተገድለዋል። ቆስለዋል።
በጦርነቱ የተሰውት ላቀው ሰለሞንና ገብሬ አውለው አስከሬን ወደ ቤተሰብ ሲላክ ከአምስት በላይ ገበሬዎች ቁስለኛ ሆነዋል።
የአቶ ለቀው ሰለሞን እና የገብሬ አውለው መገደል ከተሰማ በኋላ የመተማ፣ የሸህዲና የአርማጭሆ ህዝብ ከሱዳን ጦር ጋር ለመግጠውም መወሰኑ ተሰምቷል። በዛሬው ዕለት የመተማ ነዋሪዎች በአይሱዚ መኪና ጦርነት ወደተነሳበት ደለሎ እየሄዱ መሆኑን ገልፀውልኛል።
የ”ኢትዮጵያ መከላከያ” ሰሞኑን ወደ ደንበር ቢጠጋም የኢትዮጵያ ገበሬዎች በሱዳን ጦር ሲዘመትባቸው ዳር ዳር ተመልካች ሆኗል። ዛሬ ሰኔ 26/2010 ዓም የአማራ ልዩ ሀይል ከሕዝቡ ጋር ወደ ደለሎ መሄዱም ተጠቁሟል።
የአማራ ገበሬዎች የሀገር ዳር ድንበር ጥሶ የመጣው ጦር ጋር ፊት ለፊት ገጥመው የመከላከያ ሰራዊቱ ከድንበር ርቆ ከርሟል። መንግስት ነኝ የሚል አካልም ሆነ ስለ ሀገር ዳር ድንበር ያገባኛል የሚል አካል ስለ ገበሬዎቹ ሞት ጆሮ አልሰጡም። የአማራ ገበሬ የድጋፍ ሰልፍ ሲወጣ ኢትዮጵያዊ ይባል፣ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በቃታ ብረት እየጠበቀ ሲሰዋ ግን ሞቱን የሚያወራ የለም። በወራሪ ጦር ሲገደል አማራ ነው!

 

Filed in: Amharic