እስኪ ዛሬ እንኳን ስለ እነ ኡስታዝ አቡበከር ንጽህና እውነቱን ተናገሩ!
ውብሸት ሙላት

እስኪ አሳሳ (አርሲ) የሞተ ፖሊስ ነበር ወይ? አንዋር መስጊድ ላይ ወረቀት ሲበትን ተያዘ የተባለው የውጭ ዜጋ እና የዕለቱ ዕለት ወደ ውጭ deport መደረጉን በኢቲቪ የተዘገበውን ሰው እውነት እነ አቡበከር ነበሩ ወይ ያመጡት? ለምን ማታ ላይ ተመልሶ እንዲወጣ ተደረገ የእውነት ቢሆን ኖሮ? ነገሩ ብዙ ነው። ግን እውነት ነጻ ታወጣለችና እነ ኡስታዝ አቡበከር ነጻ ናቸው አሁን ላይ።
ለማንኛውም የሽብር ተግባር ሳይሆን የፈጸሙት እጅግ ጥንቃቄ የተሞላበት ሰላማዊ ድርጊት እንደነበር ታውቁት ነበር። አሸባሪ ስላልሆኑ ይኸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ጋር በቤተ መንግሥት!
እውነትም ፍቅርም አሸናፊ ነው።