>

600 ሜትር የሚረዝም የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በካፋ ምድር  በቦንጋ ከተማ! (አቻምየለህ ታምሩ)

600 ሜትር የሚረዝም የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በካፋ ምድር  በቦንጋ ከተማ!
አቻምየለህ ታምሩ
ድንቁርናን እንደ እውቀት የሙጥኝ  አድርገው የያዙ የወያኔ ኮልኮሌዎችና ወሲባዊ ብስጭታቸውን ወደ ፖለቲካ የለውጡ  የጥላቻ ዶክተሮች የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ አዲስ አበባ፣ ባሕር ዳር፣ ወዘተ የሚሰቀልና  አማራ ብቻ የሚያውለበልበው  «የአማራ ባንዲራ»  እንደሆነ ሲነግሩን ሰንብተው ነበር።
የካፋ ልጆች ግን  ወያኔ በፋብሪካ ያመረታቸውን ኮልኮሌዎች ፕሮፓጋንዳና የኦነግ የጥላቻ ዶክተሮችን  ቡትቶ ፕሮፓጋንዳ አፈር ድሜ በማስጋጥ
ባሕር ዳር ከተውለበለበው የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ የሚረዝም  የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ  በቦንጋ ከተማ ከፍ ብሎ  እንዲውለበለብ አድርገዋል።
የሐድያ ልጆች በሆሳዕና፣ የጉራጌ ልጆች በወልቂጤ፣ የድሬ ልጆች በድሬ ዳዋ የጀግኖች አያቶቻቸውን  የኢትዮጵያን ሰንደቅ ሰንደቅ አላማ እያውለበለቡ ወደ አደባባይ ሲወጡ ሰንብተዋል።
ወጣቱ ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ  የፋሽስት ጥሊያን ባንዳ ልጆች ፍጡር የሆነው ፋሽስት ወያኔ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በአዋጅ ሲያግድ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በቀንስተ ዳመና ወይንም በተለምዶ የማሪያም መቀነት በሚባለው  መስሎ እንዲህ ብሎ ገጥሞ ነበር፤
የኛማ ባንዲራ የማርያም መቀነት፣ 
ብትቆርጥ ብትቀጥል ብትሸነሽናት፤
ከንቱ ነው ድካምህ፣
አጉል ነው ልፋትህ፤
ደመናና ፀሓይ እስካልተፋለሱ፣
ሰማይ ላይ ዝንታለም ትውለበለባለች ልጆቿ እስኪነሱ!
ይስማዕከ «ልጆቿ እስኪነሱ» ያለው  ነገር ጊዜው ደርሶ ልጆቿ ተንስተው ይሆን  የባንዳ ልጆችን እግድ ጥሰው  የጀግኖችን አያቶቻችንን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርገው እያውለበለቡት ያለው?
Filed in: Amharic