>

በጅምላ ገድሎ በጅምላ ቀብሮ ላዩላይ እስር ቤት ገንቢው ፋሽስቱ ህወሀት !!! (ደሴት ኢትዮፕ)

በጅምላ ገድሎ በጅምላ ቀብሮ ላዩላይ እስር ቤት ገንቢው ፋሽስቱ ህወሀት !!!
ደሴት ኢትዮፕ
በሚያሳምም ግርምትና ስቀት አየቃተትኩ በመንግስታዊ  “የፍትህ” ተቋም ውስጥ ባሉና “በሕግ” ጥላ ስር በወደቁ ዜጎች ላይ ሲፈፀም የነበረውን የእስረኞችና የተመርማሪዎች አያያዝ ሁኔታ በክፍል 2ቱ የአማራ ቴሌቪቪን ፕሮግራም ተከታተልኩ ።
.
መቼም ኢትዮጵያዊ ሰው ቀርቶ ዳቢሎስ እንኳ በእነዚህ የሕወሓት ማሰቃያ ካንፓችና ማእከላዊ ውስጥ ቢሾም አሁን እየሰማሁት ያለውን አይነት የግፍ ጫፍ  ስለመፈፀሙ እጠራጠራለሁ ።
.
ይህ የቀድሞ ቀኝ ገዢዎች በባሮቻቸው ላይ ፣ የጥንት ተዋጊዎችም  በምርኮኛ ጠላቶቻቸው ላይ ሲከተሉት ከነበረው ያልተናነሰ ግፍ ነው ።
.
ይህ እየሰማን ያለው የሕወሓት የእስር ቤቶች ስቃይ የጀርመን ናዚዎች…. የመግደያ ፣ የማምከኛ የመበለቻና የመግረፊያ ካምፓች ከነበሩት ከኦሽዊትዝና ከኦስሎ የተኮረጀ የሚመስል አይነት ነው ።
.
” ፍቅር ፣ ተስፋ ፣ እናት ፣ ጎጆ ፣ ጥላ ፣ ከለላ ገነት ” እያልን በምናሞካሻት ሀገራችን ውስጥ ፤ እነዚህን የመሰሉ መንግስታዊ የማሰቃያ  ተቋማትና በአሰቃይነትም ተመለምለው የሚያገለግሉ  አውሬዎች ጭምር  ፤ ለ27 አመታት  ተደላድለው  መኖራቸው  ያስገርማል ።
.
ይህ ጨቅላ ልጆቻችን ቁጭ ብለው ቢሰሙት በመንግስት ፣ በሀገር ፣ በሕዝብና በሌላው ብሄር ላይ የሚኖራቸው አዎንታዊ እይታን ያዛባል ብዬም አስባለሁ ።
.
መ/አ ማስረሻ ሰጤ ፣ አበበ ካሴ ፣ ደሕናሁን ቤዛና አሸናፊ አካሉ የተባሉት የስቃይ ሰለባዎች የተረኩልንን የእስር ቤት ስቃይ ስንሰማ …  በሕወሓት ገበና ውስጥ የተሸሸጉ ገና ብዙ የምንሰማቸው የግፍ ጉዶች እንዳሉም አመላክተውናል ።
.
አሁን ማን ያምናል ?..ሕወሓት በራሱ ሰንሰለት የጠፈራቸውና በታማኝ አንጋቾቹ የሚጠብቃቸውን እስረኞች ለመጨረስ እሳት መለኮሱን ?… ይህን በቂሊነጦ ፈፅሞታል ፤ በፍርግርግ ብረት ውስጥ ያሰራቸውን ዜጎች በሳት አንድዷል ፤ የተረፉትንም በጥይት ፈጅቷል ። በዚህም ለተሰው የአስረኛ  ቤተሰቦች “እንኩ ቅበሩ”ብሎ አስክሬን አልባ ሳጥን ሰጥቶ አስቀብሯል ።
.
በጅምላ የተገደሉ እሰረኞችም በጅምላ ተቀብረው በቀብራቸው ላይ የእስረኞች ቤት ተሰርቶበት እስረኞች ይኖሩበታል ። አሸናፊ አካሉ በዚህ ወገኖቹ በተቀበሩበት  ቦታ ላይ በተሰራ ቤት ውስጥ ለአንድ አመት መኖሩን ሀዘንና እልህ በዋጠው ስሜት አውግቶናል ። ይህ ቤትና ቦታም ዝንብ ዘንቦ ፀሐይ ሲወጣ በአስከፊ ሽታ እንደሚበከልም ጭምር ።
.
የትግራይ ወገኖቻችን ሆይ !… እናንተም ይህንን የልጆቻችሁን ጉድ በቅንነት ስሙት ። ቆም ብላችሁም  ” በርግጥም እነዚህ ሕወሓታውያን የእኛው የአብራክ ክፋይና እኛኑ የሚወክሉ ናቸው ወይ?”በማለትም ተወያዩ።
.
ኢትዮጵያችን ግን አምላክ ይጎብኛት!!!
Filed in: Amharic