>

ህወሀቶቹ ምን ነካቸው?  በአንድ ወር ውስጥ ብቻ አራት ጊዜ እርስ በርሱ የሚቃረን መግለጫ....!!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

ህወሀቶቹ ምን ነካቸው? 
በአንድ ወር ውስጥ ብቻ አራት ጊዜ እርስ በርሱ የሚቃረን መግለጫ….!!!!
ቬሮኒካ መላኩ
የትግራይ ክልል መንግስትና መሪ ፓርቲው ህውሃት የኤርትራን ጉዳይ በተመለከተ የሚያወጣው መግለጫና ውሳኔ በሚያስገርም ሁኔታ የሚቀያየር ሆኗል። ፈፅሞ ሊረጋጉ አልቻሉም።
በአንድ ወር ውስጥ ብቻ አራት ጊዜ እርስ በርሱ የሚቃረን መግለጫ አውጥተዋል።
1~ የመጀመሪያው መግለጫ ከወር በፊት ለመጀመሪያጥሪ ጊዜ ጉዳዩ ሲፈነዳ የኢህአድግ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ህውሃትና ሌሎች ፓርቲዎች የአልጄርሱን ስምምነት ካለምንም ቅድመ ሁኔታ እንደሚቀበሉ አሳወቁ ። ጠ/ሚ አቢይ አህመድ ይሄንኑ ውሳኔ ተከትሎ ለኤርትራ መንግስት ኢትዮጵያ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ የአልጀርሱን ውሳኔ እንደምትቀበል በይፋ ለኤርትራና ለአለምአቀፉ ማህበረሰብ በሚዲያ  አቀረበ።
2~ የጠ/ሚሩን ይፋ መግለጫ ተከትሎ የትግራይ ህዝብ ማጉረምረም ሲጀምር ህውሃት አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ ውሳኔውን እንደሚቃወሙ በመግለፅ “ጠቅላይ ሚኒስትሩም ለፓርላማ ሳይቀርብ በይፋ መናገሩ ስህተት ነው ” የሚል መግለጫ አወጡበት። እንደውም ከዛ አልፈው ህውሃት የኢህአድግ ምክር ቤት በአስቸኳይቤት እንድሰበሰብለት ጥሪ አቀረበ። በትግራይ ክልልም ሰፊ ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ ።
3ኛ ~ በህውሃቶች ቃል ማጠፍ የተበሳጨው ጠ/ሚ አቢይ አህመድ ፓርላማ ቀርቦ አስደናቂውን ንግግርና ለህውሃት ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ተከትሎ ውሳኔውን በአጠቃላይ
ሁኔታ እንደሚደግፉት ተናግረው የትግራይ ህዝብ ሳይወያይበት የተወሰነ ውሳኔ ስለሆነ እንደሚቃወሙት ከ2 ቀን በፊት የትግራይ ምክር  ተሰብስቦ ሪዞሊዩሽን አወጣ ።
4ኛ~ ዛሬ ደሞ የትግራይ ምክርቤት ያወጣው የተቃውሞ ሪዞሊዩሽን ቀለም ሳይደርቅ ውሳኔውን ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፉትና በውሳኔውም ደስተኞች እንደሆኑ መግለጫ አውጥተዋል።
ህውሃቶች እንደዚህ የሚያርበተብታቸውና መረጋጋት ያቃታቸው ለምን ይሆን ? ትናንት አቢይ አህመድ አስመራ በሰጠው መግለጫ ድንበር ማስመር እንደማያስፈልግ ቢናገርም ኢሳያስ ግን በሰጠው መግለጫ ይችን ነገር አላረጋገጠም። እንደውም ዛሬ ከተደረጉት የሁለትዮሽ
ፊርማ ውስጥ የድንበር ጉዳይ አንዱ እንደሆነ ታውቋል።
ይሄ ማለት ከሁለቱ አገራት ሁለገብ ግንኙነት ባሻገር በአልጄርስ ስምምነት መሰረት የሁለቱን አገሮች ድንበር የሚለየው ችካል ይቸከላል ማለት ነው። በዚህ የድማርኬሽን ችካል መሰረት ባድመ እና ሌሎች ቦታዎች ወደ ኤርትራ በቅርቡ እንደሚካለሉ ግልፅ ነው ። ያኔ
ደሞ ህውሃት አምስተኛውን ምናልባትም አስረኛውን እርስበርሱ የሚቃረን መግለጫ ሊያወጡ ነው ማለት ነው።
በነገራችን ላይ ህውሃቶች እኛን ከሸወዱን የበለጠ ኢሳያስን በነፍሱ ስለተጫወቱበት በዛም 25 አመታት ሙሉ ቅጥል ስላለ አሁን ኤርትራውያን ህውሃቶችን በተመለከተ በጥንቃቄ ነው እንደገና ላለመሸወድ እያንዳንዷን ለራሳቸው ጥቅም ብቻ እንደሚያደርጉ ግልፅ ነው ። ለአፍ ድንበር አያስፈልገንም ይባል እንጅ የችካሉን ነገር ኤርትራውያን ከሁሉም በፊት እንድቸከል ይፈልጋሉ።
በነገራችን ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ አስመራ ሲጓዙ ቀጥታውንና ጭሩን በትግራይ በኩል ያለውን የአየር መስመር መከተል ሲገባቸው በሌላ ሶስተኛ የውጭ አገር ዞረው መሄዳቸው ብዝዎችን እያነጋገረ ነው።
Filed in: Amharic