>

የታክሲ ጥቅሶቻችን ከመደመር በኋላ ... !

የታክሲ ጥቅሶቻችን ከመደመር በኋላ … !
    
 ከናቲ ቪሎፒያ (ጋዜፀሃዲዛ)
፩. የቀን ጅቦችን አንጭንም !
፪. መደመር ያዋጣልና ጠጋ ጠጋ በሉ !
፫. ስንጀምር ወያላ ስንጨርስ ሹፌር ነን !
፬. ጥያቄዎቻችንን አብይ መልሷልና መልስ አጠይቁን !
፭. ሴቶች ሆይ በፍቅር እና በመደመር ሰአት ሹፌሩን መጥበስ ይቻላል … መጀመሪያ ግን ሂሳብ ክፈሉ።
፮. ቦንብን እንደ ማስታወሻዎ ደብተር ኪሳቸው ውስጥ ይዘው ለሚሄዱ ሰዎች እንፀልያለቸው እና ይታሰሩ።
፯. አብያችን ሆይ የመደመር መንታ ወንድም “መቀነስን” በአግባቡ ይጠቀሙበት።
፰. ወያላውን መደመር ይቻላል … “መልስ ስጠኝ”  እያሉ መነዝመዝ ግን የቀን ጅብነት ነው።
፱. ታክሲ ውስጥ ሰልፍ ማካሄድ ይቻላል።
፲. ታክሲ ውስጥ ስለ ዘር የሚያወሩ ሰዎችን ወፍጮ ቤት እናደርሳለን።
፲፩.  ሚስት ሆይ በመደመር ሰአት ባልሽን አትቀንሺ።
፲፪. ባል ሆይ የአለም ዋንጫ ትዳር አይሆንም።
፲፫. ጠጋ ጠጋ በሉ … ETV ልንከፍት ነው።
፲፬. ETV ለሚያይ ተሳፋሪ ESAT’ን እንጨምራለን።
፲፭. እስከ አስመራ መንገድ በነፃ እናሳፍራለን።
፲፮. አባዱላዊ ሂሳብ እየመቱ ወያላን በታሪፍ መጨቅጨቅ የቀን ጅብነት ነው።
፲፯. ስንኖር ወያላ እና ሹፌር … ስንሞት ታክሲ ነን !
፲፰. የ27 አመት ዱንዙዝ ታሪክ ያላቸውን ሰዎች መምህር ግርማ ጋር እንወስዳለን።
፲፱. በመደመር አስታኮ ታክሲ ውስጥ መጀንጀን ሂሳብ ያስጨምራል።
፳. ታክሲ ውስጥ አለመቆም ክልክል ነው።
፳፩.  ታክሲ ውስጥ ስለ አስመራ ለሚያወሩ ሰዎች ባድመን እንመርቃለን !
፳፪.  እንደምራችሁ ብለን ነው እንጂ መቀነስ አያቅተንም !
፳፫. ETV’ን ያደሰ አብይ … እግርኳሳችንንም ያድሰው!
፳፬. የሸገር ሴት አግብቶ … የአስመራ ሴትን መናፈቅ መልካም አይደለምና “ሞኖፖላዊ አስተሳብ” ይቅር …
፳፭. የአስመራዋን ቆንጆ ላላገቡት ሸገሮች ይልቀቁ እንጂ “ሹገር ዳዲ” እየሆኑ እንደ እነንትና አያስቸግሩ።
፳፮. EBS ሆይ የት ነህ ? …
፳፯. ኬምስትሪን ለዘር መጠቀም ባይሎጂካዊ እብደት ነው።
፳፰. ኤፈርት እና ኢትፍሩት የሃገር ንብረት ናቸው …
፳፱. ባለ ራዕይ መሪዎችን ራዕይ እናስተምራለን !
፴. ማሽላ ከጤፍ ማህፀን ዱቄት የሚወጣ አይመስላትምና ትንቃታለች … የቀን ጅቦቹም እንደዛው !
፴፩. የሃገር እዳችንን ሳይመልሱ አንደመርም !
፴፪. ተራራን ያንቀጠቀጠ ትውልድ ለምን ይንቀጠቀጣል ?
፴፫. ወያላን ከፖለቲካ ጨዋታ ማግለል የቀን ጅብነት ነው።
፴፬. ላወቀበት እና የግራ ጎኑን ላጣ ሰው ታክሲ ጥሩ ካፌ ነው … ሰልፍም ጥሩ መናፈሻ !
Filed in: Amharic