>

እንደምን ከረምሽ ኤርትራ?  (ሎሬት- ፀጋዬ ገብረ መድህን)

እንደምን ከረምሽ ኤርትራ? 

ከሎሬት- ፀጋዬ ገብረ መድህን
የአመፅዋ ልጅ መሰዋ ፣ የመስዋዕት ልጅ ኤርትራ ፣
ካ-ከእግዛብሔር ባ -ከመንፈስ ራ -ከፀሐይ ልደት ጣራ ፣
አበክሮ የወለደሽ የበኩር ልጅ የካባራ ፣
እንደምን ከረምሽ ኤርትራ ?
አጥንትሽ የኔው የእናትሽ ፣ ደምሽ የእኔው የኢትዮጵያ ደም ፣
ህይወትሽ ዞሮ ሕይወቴ ፣አለምሽ ዞሮ የኔ ዓለም፣
ቆስለሽም ቁስልሽ ቁስሌ፣ ስትታገም እምታገም፣
ቂም አርግዘሽ እማዋልድ፣ እማርስሽ የአንቺን ህመም፣
ከእኔ ከናትሽ በስተቀር፣ የምያውቅልሽ ሌላ የለም።
እንደምን ከረምሽ ኤርትራ?
ኤርትራ ድባብሽ ሶራ፣ የውቅያኖስሽ ክልሉ፣
ባህር ድንበርሽ አጥሩ፣ ሰንጋ ፈረስሽ ማዕበሉ፣
የፈርዖን ስያሜ ነሽ፣ ኤርትራ ባህር ማዕዘኑ፣
የካማ ልጅ ካማሴኑ፣ የአዱሊስ አዱኛ ስኑ፣
የአመ ፅዋ፣ አመ-ፅኑ።
እንደምን ከረምሽ ኤርትራ?
የአትባራ ልጅ ኦራስ ኦራ፣ የማለዳ ምስራቅ ጮራ ።
ማተኮርያው ነሽ ብለኑ፣
ለኢትዮጵያ ማህፀን ብስራት፣ ላራ ፀሐይ ቀኝ አይኑ።
አጥንትሽ የኔው የእናትሽ፣ ደምሽ የኔው የኢትዮጵያ ደም፣
ግፍሽ ወጋኝ እንጂ ልጄ፣ ልብሽ ከልቤ አልተለየም፣
ህይወትሽ ዞሮ ሕይወቴ፣ አለምሽ ዞሮ የኔ ዓለም።
እንደምን ከረምሽ ኤርትራ?
የአትባራ ልጅ አነስ ኦራ ፣ የማለዳ ምስራቅ ጮራ ።
Filed in: Amharic