>

ጠ/ሚር አብይ አሀመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያቀረብት መግለጫ

ጠ/ሚር አብይ አሀመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያቀረብት መግለጫ

– ህዝብ ላሳየው ፍቅር አንድነት ጨዋ የሆነ የእንግዳ ተቀባይነቱ ምስጋና አቅርበዋል
–  በቅርቡ የሚጀመር ኦፕሬሽን ስለሚኖር ገንዘብ በብርም በዶላርም ቤታችሁ ያከማቻችሁ በፍጥነት ወደ ባንክ አስገቡ ሲሉ ምክር አዘል መመሪያም አስተላልፈዋል
– በየቦታው በግልም በቡድንም ክብሪት እና ቤንዚን እያቀበሉ እሳት የሚለኩሱ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ፤ በማሳሰብ ይህንን የጠብ የግጭትና የጥፋት መንገድ ለአመታት የሄድንበት እና ትርፍም የሌለው ያለፈበት ፋሽን በመሆኑ አዲሱን የፍቅር የእርቅ መንገድ እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ከዚሁም ጋር አያይዘው የጥቂቶች ክፉ ሀሳብ ብዙዎች ካልተቀበልነው ካልተገበርነው እዛው በክፉዎች ልቦና መክኖ ይቀራል። እባካችሁ ከክፋት ጋር አንደመር ህብረትም አይኑረን ብለዋል።
– ለመከላከያ ለፌደራል ፖሊስ ዛሬም ሰው እየሞተ ንብረት እየወደመ በመሆኑ ግጭት በሚነሳባቸው ስፍራዎች ሁሉ ፈጥነው በመድረስ ሙያዊ እና ጥበባዊ በሆነ መንገድ ብዙም ኪሳራ በማያደርስ መልኩ ግጭቶችን እንዲፈቱ መመሪያ አስተላልፈዋል።

ሌሎች መልዕክቶችም ኣላቸው ቪዲዮውን ይመልከቱ

https://www.facebook.com/FITIH1/videos/2076182465972245/

Filed in: Amharic