>

 በጨካኙና ነውረኛው ኮሎኔል አጥናፉ አባተ ትዕዛዝ የተረሸኑት ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ! (አቻምየለህ ታምሩ)

 በጨካኙና ነውረኛው ኮሎኔል አጥናፉ አባተ ትዕዛዝ የተረሸኑት ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ!
አቻምየለህ ታምሩ
አጥናፉ አባተ የሚባለው ደም የተጠማ ግለሰብ ደርግ የሚባለው የጥፋት ቡድን እንዲፈጠር ግንባር ቀደም ሚና የተጫወተ ነውረኛ ወታደር ነው። ደርግን የመሰረቱት የበታች መኮንኖችና አስር አለቆች ወደ አራተኛው ክፍለ ጦር መርምሪያ ማዕከል ከአራቱም አቅጣጫ የጎረፉት አጥናፉ አባተ በጻፈው ደብዳቤ ነው።
ነውረኛው መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ሕዳር 13 ቀን 1967 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ ያለ ወንጀላቸው ታስረው የነበሩ የኢትዮጵያ አገልጋዮች በግፍ እንዲረሸኑ ማዘዘኑን ከዚህ በፊት ተናግረንና ማስረጃውንም አውጥተን ነበር። እነዚህ በኅዳር ፲፬ ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. የተጨፈጨፉት የኢትዮጵያ የስለት ልጆች በአንድ ምሽት በነውረኛው መንግሥቱ ኃይለ ማርያም አስፈጻሚነት ተረሽነው ያደሩት ያለምንም ጥፋታቸው በንጽህናቸው ነበር።
የጭፍጨፋው አስፈጻሚ ጨካኑ አውሬ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ራሱ ከደሙ ለማድረግ ከገነት አየለ አንበሴ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ «እነዚህ ሰዎች ሙቶች ናቸው። በቁጥጥራችን ሥር፣ በጫማችን ሥር ያሉ ሰዎች ናቸው። ትላንት ለፍርድ ይቀርባል ብለን ተናገረን ዛሬ ይሄ ዓይነት ውሳኔ ስንወስንባቸው ሕዝቡስ ምን ይላል” ብዬ ስል ለታሰሩ ፊውዳሎች ጥብቅና ቆመሃል ተብዬ ተከሰስሁኝ. . . እኔን በሚመለከት ከጠቀቅሽኝ የሰዎቹን ግድያ አልደገፍሁም» ብሏል።
ነውረኛው መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ከገነት አየለ አንበሴ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ በስድሳዎቹ የግፍ ግድያ እጁ እንደሌለበትና የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ፍጻሜም ደርጎች እንዳልገደሏቸው ክዶ ነበር። ሆኖም ግን በደርግ ላይ የተከፈተውን ክስና ፍርድ በማጠናቀር አቃቢ ሕግ ባሳተመው «ደም ያዘለ ዶሴ» መጽሐፍ ላይ እንደወጣው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የሕይወት ፍጻሜ መንግሥቱ እንዳለው ታመው የሞቱ ሳይሆን የደርግ የቋሚ ኮምቴ ተሰብስቦ እንዲገደሉ እንደወሰነባቸው አጋልጦ ነበር።
በማይዋሽበት ዘመን ስለምንኖር ዛሬ ደግሞ የደርግ የቋሚ ኮምቴ ተሰብስቦ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ላይ የወሰነው የሞት ቅጣት ውሳኔና በጨካኙ ነውረኛ ኮሎኔል አጥናፉ አባተ የተፈረመውና የሌላው የደርግ ነፍሰ በላ በኮሎኔል ዳንኤል አስፋው እንዲፈጸም የተደረገው የግፍ ግድያ ትዕዛዝ ዶሴ እነሆ! ጨካኙ አትናፉ በደብዳቤው ንጉሠ ነገሥቱን አንተ እያለ እያዋረደ የግድያ ትዕዛዙን አስተላልፏል።
ጨካኙ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም እንዲገደሉ እጁን ወደላይ አብሮ የወሰነባቸውንና ያስመሰነባቸውን ንጉሠ ነገሥት እውነቱ የማይገለጥ መስሎት ሲክድ ቢኖርም እነሆ ነውረኛነቱ ሊጋለጥ ዶሴው ለሕዝብ ይፋ ሆኗል።
ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ የያ ትውልድ ፋኖዎች በግፍ ለረሸኗቸው የኢትዮጵያ አገልጋዮችና በነ አጥናፉና መንግሥቱ ለተረሸኑት ለታላቁ በ የኢትዮጵያ ንጉሥ ነገሥት!
Filed in: Amharic