>

ሞሳድ እና ካሳ ከበደ - ክፍል 2

ሞሳድ እና ካሳ ከበደ 
ሮነን በርግማን (Ronen Bergman)| 
ትርጉም፡ ካሳ አንበሳው ክፍል 2
ከኒታ ኢፍሮኒ ጋር የተጀመረው ፍቅርና የታቀደው ጋብቻ ጦስ ሁኖ በ1958 ካሳ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ተደርገ፤
በንጉሰ ነገስቱ የሚመራውን የበጎ አድራጎት እና የማህበራዊ ዋስትና ስራዎችን እንዲያስተባብር ተመደበ፤
ያ ወቅት ኢትዮጵያና እስራኤል ሲያደርጉት የነበረው የደህንነት እና ወታደራዊ ግንኙነት ከፍተኛ ደረጃ የደረሰበት ወቅት ነበር፤ አንዳንዶቹ የደህንነት ትብብሮች ቀጥታ ኢትዮጵያን የተመለከቱ አልነበሩም፤ የቡና ተልዕኮን (Operation Coffee) አንድ ምሳሌ ሊሆን ይችላል፤ የዚህ ተልዕኮ ዋና አላማ በደቡብ ሱዳን ላሉ ክርስቲያን አማጽያን ድጋፍ ማድረግ ነው፤ የእስራኤል የጦር አውሮፕላን (Boeing 377) ሱዳን ዘልቆ ለአማጽያኑ የተለያዩ የጦር ቁሳቁሶች ከአየር አዝንቦላቸው (መሬት ሳይነካ) ይወጣል፤ አውሮፕላኑ ይህን ስራ ለማከናወን አንድ ቦታ አርፎ ነዳጅ መሙላት ይጠበቅበታል፤ ለዚህ ደግሞ ከኢትዮጵያ የተሻለ ሀገር አልነበረም፤
በኢትዮጵያ የእስራኤል አንባሳደር የነበረው ዩሪያል ሉብራኒ (Uriel Lubrani) ንጉሰ ነገስቱ ጋር ቀርቦ የማረፊያ ቦታ እንዲያስፈቅድ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚንስቴር ሌቪ እሽኮል (Levi Eshkol) ተዕዛዝ ደረሰው፤
አንባሳደር ዩሪያል ወቅቱን እንዲህ ያስታውሳል;- 
“ተዕዛዙ እንደደረሰኝ ቀጥታ ወደ ንጉሰ ነገስቱ ቤተ መንግስት አቀናው፤ ለንጉሱ የጠቅላይ ሚንስትር እሽኮልን ጥያቄ አቀረብኩ፤ ምንም ሳያቅማሙ እሺ አሉኝ፤ የስልጣን ተዋረዱን ጥሼ ቀጥታ ከአገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስቴር ሚንስትር ከሆኑት ደጃዝማች ከበደ ተሰማ ጋር እንድጨርስ ነገሩኝ፤ እኔም ንጉሰ ነገስቱ እንደነገሩኝ ደህንነቱን፣ መከላከያውን፤ የኤርፖርት አስተዳደርን …… ሁሉንም ጣጥሼ ወደ ደጃዝማች ከበደ ቤት አመራው፤ ሁሉንም ነገር ደጃች ከበደ ጋር ጨረስኩ፤ ጉዳዬን ጨርሼ ከሚንስትሩ ቤት ስወጣ አንድ መልከ-መልካም ረጅም ወጣት ከጓደኞቹ ጋር ወግ ይዞ አየሁት፤ ደጃች ከበደ “አንባሳደር፣ ተዋወቀው ልጄ ነው፤ ካሳ ይባላል” ብለው ከወጣቱ ጋር አስተዋወቁኝ፤”
የ”ዮም ኪፑር” ጦርነትን (Yom Kippur war) ተከትሎ ኢትዮጵያ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት እንድታቆም በሙስሊሞች፣ በአረብ እና በአፍሪካ ሀገራት ግፊት ተደረገባት፤ ኢትዮጵያም ከእስራኤል ጋር የነበራትን ይፋዊ ግንኙነት አቆመች፤ [የዮም ኪፑር ወይም የረመዳን ጦርነት ግብጽና ሶሪያ የመሩት የአረብ ሀገራት ጥምረት ከእስራኤል ጋር ያደረጉ ጦርነት ነው፤ በጦርነት እስራኤል ተሸንፋለች]
“ለሌላው አለም ግንኙነቱ የተበጠሰ ቢመስልም ሁለቱ ሀገራት የውስጥ ለውስጥ ግንኙነት ያደርጉ ነበር፤ ግንኙነቱ ሲደረግ የነበረው መቀመጫው አዲስ አበባ ባደረገው የሞሳድ ቡድን ነበር” ይላል ካሳ ከበደ፤
በስልሳዎቹ አጋማሽ ኢትዮጵያ ውስጥ ካባድ ድርቅ ተከሰተ፤ በድርቅ የተጎዱትን አካባቢዎች እንዲያስተባብር ካሳ ከበደ ተመደበ፤ ይህ አጋጣሚ ንጉሰ ነገስቱን በቀጥታ የሚያገኝበትን እድል ፈጠረለት፤
ስለ አዲሱ የስራ ምደባ ካሳ እንዲህ ይላል;-
 “ይህ የሰራ ምደባ አንድ ሚስጥር እንዳውቅ እድል ፈጠረልኝ፤ ንጉሰ ነገስቱ ጃጅተዋል፤ ሰራቸውን መስራት የማይችሉበት ደረጃ ላይ እንዳሉ ማወቅ ቻልኩ፤ ይህ አባቴ የሚመሩት የንጉሰ ነገስቱ የቅርብ ረዳት ቡድን ከኢትዮጵያ ህዝብ ለረዥም ጊዜ ደብቆ የያዘው ሚስጥር ነው”
ከጥር ወር 1966 ጀምሮ የንጉሰ ነገስቱ መንግስት ላይ አመጽ ተነሳ፤ ተማሪዎች ተከታታይ ሰልፍ ማድረግ ጀመሩ፤  ወታደሩ “ደርግ” የሚሰኝ ኮሚቴ አቋቁሞ የንጉሱን ዙፋን ገለበጠ፤ የካሳ አባት ደጃዝማች ከበደ ተሰማ ሳይገደሉ እና ሳይታሰሩ ቀሩ፤ ይህ ትልቅ እንቆቅልሽ ነው፤ “ከወታደሮቹ ጋር ተደራድሬ ነው አባቴ የተረፉት” ይላል ካሳ፤
እስራኤል [በሞሳድ በኩል] ከአዲሱ መንግስት ጋር ግንኙነት እንዲጀመር ጥያቄ አቀረበች፤ በ1968 መንግስቱ ኃይለማሪያም የእስራኤልን ጥያቄ ተቀበለ፤ ካሳ ከበደ የሂብሩ ቋንቋ አቀላጥፎ ስለሚናገር እና የእስራኤሎቹን ስነ ልቦናን ያውቃል ተብሎ ሰለታመነ በአዲስ አበባ እና ቴላቪቭ መካከል የሚደረገው ግንኙነት እንዲያሳልጥ ተመደበ፤
የኢትዮ-እስራኤል ግንኙነት ፍጹም ሚስጥርዊ ተደርጎ እንዲያዝ በእስራኤል እና በኢትዮጵያ ባለስልጣናት መካከል ስምምነት ተደርጓል፤ ካሳ ምክንያቱን እንዲህ ይስረዳል;-
“እኛ ሶሻሊስት ነን ብለን ለአለም አውጀናል፤ ወዳጅነት የፈጠርነው ከሶቭየት ኅብረት ጋር ነው፤ በዛ ላይ መንግስቱ ኃይለማሪያም መታየት የሚፈልገው እንደ ጸረ-ኢምፔሪያሊዝም ጸረ-አሜሪካ ነው፤ ከእስራኤል ጋር ያለን ግንኙነት ይፋ ቢሆን ነገሩ ሁሉ ይበላሻል፤ ጸረ-ኢምፔሪያሊዝም ጸረ-አሜሪካ ሁነህ የእስራኤል ወዳጅ ልትሆን አትችልም”
በሚስጥር እንዲያዝ የተደረገው ስምምነት ሳይዘልቅ ቀረ፤ በ1970 የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሙሼ ዳያን (Moshe Dayan) እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት እንዳላት በአንድ መድረክ ይፋ አደረገው፤ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴሩ ለምን ይፋ ማድረግ እንደፈለገ እስከ ዛሬ በግልጽ አይታወቅም፤ ይህን አስመልክቶ ካሳ እንዲህ ይላል;-
“በዳያን መግለጫ ምክንያት የኢትዮ-እስራኤል ግንኙነትን ሲያወግዙ የነበሩ ባለስልጣት መፈንጫ አደረጉኝ፤ ቀድሞውኑ ይህ ግንኙነት ይቅር ብለን ነበር ብለው አሳጡኝ፤ መንግስቱ ኃይለማሪያም አበደ፤ በጣም ተበሳጨ፤ እስራኤላዊያን ተጠራርገው ከአዲስ አበባ እንዲወጡ ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላለፈ፤ ሙሼ ዳያን ሆን ብሎ ከሶቭየት ኅብረት ጋር የነበረንን ጥሩ ግንኙነት ለማበላሸት ይፋ እንዳደረገው ነው መንግስቱ ያመነው፤ በእርግጥ የአፍ ወለምታ አልነበረም፤ ሆን ተብሎ የተደረገ ነገር ነው”
“በ1970ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ አንድ የንግድ ድርጅት አዲስ አበባ ውስጥ ተቋቁሞ ስራ ጀመረ፤ በጊዜው ሂደት ይህ “የንግድ” የተባለው ድርጅት የሞሳድ ቢሮ መሆኑን መንግስት ደረሰበት፤ በንግድ ድርጅት ሽፋን ሞሳድ ተሰግስጎ ቁጭ ብሏል፤ ፕሬዝዳንቱ አይቶ አንዳላየ አለፈው”
የኢትዮ-እስራኤል ግንኙነት መልሶ የተቀጠለበትን አጋጣሚ ካሳ እንዲህ ያስታውሰዋል;-
“በ1973 ነው፤ እኔ የሰራተኞች ጉዳይ ሚንስትር የሆንኩበት ወቅት ነበር፤ የግብርና ማሰልጠኛ ተቋም በስምጥ ሸለቆ ክልል ማቋቋም አሰብኩኝ፤ የአካባቢው አፈር ጨዋማ እንደሆነ በጥናት አረጋገጥን፤ ሰለሆነም አፈሩ መታከም እንዳለበት ግንዛቡ ተያዘ፤ ለዚህ ስራ ባለሙያዎችን “Bet Dagan Volcanic Institute” ከሚባል የእስራኤል ተቋም ማስመጣት ፈለኩ፤ ይህን ለመንግስቱ ኃይለማሪያም አስረድቼ እንዲፈቀድልኝ ጥያቄ አቀረብኩ፤ ተፈቀደ፤ “ሞክር፣ እስራኤል ሚስጥር መቋጠር እንደምትችል አሳየኝ” አለ;- መንግስቱ ኃይለማሪያም፤
“ይህን ጉዳይ በሞሳድ በኩል ለመጨረስ ወሰንኩ፤ ሞሳድ ናይሮቢ ውስጥ ሚስጥራዊ ጽ/ቤት እንዳለው አውቅ ነበር፤ ሰለሆነም ከቅርንጫፉ አዛዥ ጋር ቀጠሮ እንዲያዝልኝ አደረኩ፤ በተያዘልኝ ቀጠሮ መሰረት ወደ ናይሮቢ አቀናው፤ የተነገረኝ ህንጻ መግቢያ ላይ ቆሜ መጠባበቅ ጀመርኩ፤ አንድ ሰው መጥቶ ወደ ውስጥ ይዞኝ ዘለቀ፤ አንድ ቢሮ ከፍቶ አስገባኝ፤ ፊት ለፊት የተቀመጠውን ሰው አየሁት፤ እይኔን ማመን አቃተኝ፤ ክው ብዬ ቀረው፤ ኔታኒያ ከተማ ውስጥ “አኪቫ አልፓ” በሚባል ተቋም የሂብሩ ቋንቋ ሳጠና የማውቀው የልብ ጓደኛዬ ነው፤ 1960ዎቹ አዲስ አበባ ድርስ እየተመላለሰ ሲጠይቀኝ ነበር፤ የወጣትነት ጓዴን በናይሮቢ የሞሳድ ቅርንጫፉ ጽ/ቤት አዛዥ ሁኖ አገኝሁት፤”
“ትንሽ ከተጨዋወትን በኋላ ስለመጣሁበት ጉዳይ አስረዳሁት፤ አዎንታዊ ምላሽ ሰጠኝ፤ ከ“Bet Dagan Volcanic Institute” አንድ የሮማኒያ ደም ያለው ባለሙያ አስመጣ፤ ለሰውየው የውሸት (fake) ፓስፖርት ሰርተው ሰጡት፤ ሰውየውን ይዥ ወደ አዲስ አበባ ተመለስኩ፤
(ይቀጥላል
የፎቶ መግለጫ፤ 
**በግራ በኩል፡ ደጃዝማች ከበደ ካሳን ያስተዋወቁት የእስራኤሉ አንባሳደር ዩሪያል ሉብራኒ (Uriel Lubrani) ከእስራኤል ጠ/ሚ ቤንጃሚን ኔታንያሁ (Benjamin Netanyahu)
**በቀኛ፤ ካሳ ከበደ ሞሳድ ደረጃ አንድ (finest) ከሚለው ልጁ ኢላይ ኢላይዝሪ (Eli Eliezri)
 
ሁለተኛው ፎቶ መግለጫ;- የውጭ ጉዳይ ሚንስትር [የእስራኤል የጦር ገብሬ] ሙሼ ዳያን
ክፍል አንድን ያላነበባች ሁ
Filed in: Amharic