መሳይ መኮንን
የዶ/ር አብይ አህመድን የአሜሪካን ታሪካዊ ቆይታ ለማሰናከል አንድ ሃይል ጉልበት ያገኘ ይመስላል:: በዋሽንግተን ዲሲና በሎስአንጀለስ ዝግጅቱን በበላይነት የሚመሩት አፍቃሪ ህወሀቱ ካሳ ተ/ብርሃንና ብርሃኔ ኪዳነማርያም ናቸው:: ይህን ታሪካዊ ጉብኝት በእነዚህ የህወሀት ወኪሎች እንዲመራ መደረጉ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል::
ታማኝ በየነን ከመርሃ ግብሩ የሰረዘው ኤምባሲው ነው:: ካሳ ተክለብርሃን የኮንቬንሽን ማዕከሉን መድረክ እመራለሁ ብሎ የታማኝን ቦታ አስለቅቋል:: ስለኤችአር 128 ማብራሪያ ለመስጠትና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ ለማቅረብ ፕሮግራም የተያዘላቸው ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪም በመጨረሻው ሰዓት ምንም ዓይነት ንግግር እንደማያደርጉ በኤምባሲ በኩል በተላለፈ ትዕዛዝ መሰረዙ ተሰምቷል:: የዲያስፖራው ድምፅ እንዲታፈን በካሳና ግብረአበሮቹ እየተደረገ ያለው ስውር ዘመቻ እየተሳካላቸው ነው::
ካሳ ተክለብርሃን በአፉ ጤፍ ሲቆላ: ሲያታልል ቆይቶ ባለቀ ሰዓት ያደፈጠበትን መረብ ዘርግቷል:: እየተጣጠፈ: በብልጣብልጥ ተራ የማታለል እንቅስቃሴው ውስጥ ቆይቶ: መሰሪ ባህሪውን ከሸለፈቱ በመፈልቀቅ በእኩይ ተግባሩ የዶ/ር አብይን ታሪካዊ ጉዞ እየበጠበጠው ነው::
እንደሰማነውም የ1500 ሰዎች የውይይት መድረክም በህወሀት ተጠልፏል:: ካሳ መድረኩን በህወሀት ደጋፊዎች እንዲሞላ በጀርባ ቲኬቶችን በትኗል:: የጠቅላይ ሚኒስትሩን ታሪካዊ ቆይታ ለማደብዘዝ የታቀደው የእነካሳ ሴራ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ካልተሰበረ ችግር ሊገጥመው እንደሚችል ይገመታል::
ይህ አጋጣሚ እንዳይሰናከል በቀረው ጊዜ ሁሉም የሚችለውን ማድረግ ይጠበቅበታል:: የካሳ ሴራ መክሸፍ አለበት:: ዶ/ር አብይ ይህን ሰው ዋሽንግተን ዲሲ ማስቀመጥ አልነበረባቸውም:: ለቀጣይ አብዝተው ቢያስቡበት ጥሩ ነው::
ታማኝን አግልሎ ለመንቀሳቀስ መሞከሩ ዋጋ ያስከፍላል!!
ተረፈ መኮንን
27 ዓመት ደከመኝ ሰለቸኝ፣ የክረምቱ ቁር የበጋው ሀሩር ሳይበግረው ከባለቤቱና ከልጆቹ እየተለየ ከአገር አገር በመላው ዓለም እየተንከራተተ ይህ የተስፋ ቀን እንዲመጣ ሲለፋለት የነበረውን ትግል እንደ አንዳንድ ሆዳም ለጥቅም ብሎ ሳይንሸራተት እንደ ስሙ ታማኝ ሆኖ የኢትዮጵያ ህዝብን ያገለገለውን በዋሽንግተን ዲሲ በዶ/ር አብይ ጉብኝት ታማኝ በየነንና ለበርካታ ዓመታት ለኢትዮጵያ ህዝብ የታገሉትን የለውጥ ሀይሎችን ማግለል በዲያስፖራ ያለውን የለውጥ ሀይሉን ማዳከም ስለሆነ አጥብቀን እንቃወማለን! በወያኔው አሻንጉሊት ካሳ ተክለ ብርሃን፣ በነ ዳንኤል ክብረትና አሳማው አሉላ ሰለሞን የሚሰራው ሸፍጥ ባስቸኳይ ይቁም ታማኛችን የኛ የኢትዮጵያኖች አምባሳደር ነው!! በዲሲው ስብሰባ ታማኝ በየነና ሌሎች በአገራቸው ጉዳይ የደከሙ እንደ ዲሲ ግብረ ሀይል የመሳሰሉት እንዲካተቱና ስለኤችአር 128 ማብራሪያ ለመስጠትና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ ለማቅረብ ፕሮግራም የተያዘላቸው ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪም ምንም ዓይነት ንግግር እንዳያደርጉ የተሰረዘባቸው ተነስቶ ለዶ/ር አብይ ገለፃ እንዲያደርጉ አጥብቀን እንጠይቃለን!!! የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ አይሁን::
“ትላንት የኢትዮጵያ ህዝብ ቁም ስቃዩን ሲያይ አንድም ነገር ወገንተኝነት ሳያሳዩና ከህዝብ ጋር ሳይቆሙ ከገዳይ ሰው በላ የሽፍታ የአፓርታይድ ስርዓት ጋር ሲያቦኩ የነበሩ ዛሬ የለውጥ ሀዋሪያት ነን ብለው ከፊት ብቅ ብቅ የሚሉትን በሁለት ቢላዋ የሚበሉትን ሙታኖች እንቃወማለን በየአካባቢያችን እነማ ምን እንደሆንን እንተዋወቃለን”
በዶ/ር አብይ የቀረበውን የዲያስፖራው በቀን 1 ዶላር ይህን ለአገር ልማትና ለወገን ከችግር ለማላቀቅ የታቀደ የተቀደሰ ዓላማ ከግቡ ለማድረስ አሁንም እስካልፀዳና ነገሮች ግልፅና ጥርት እስካላሉ ድረስ አላማው ከግቡ አይደርስም ሁላችንም በደስታ የምናደርገው ጥርት ብሎ የለውጡ መንገድ ሲስተካከል ነው ከቀን ጅቦቹ ጋር ሆነው አገራችንን አዘቅት ውስጥ የከተቷትን አሁንም ከፊት እፊት እያየን ግን ማንም አይተባበርም::