ያሬድ አማረ
* ይሄ ዘንበል ያለው የኢንጅነር ስመኘው አንገት ብቻ አይደለም! የኢትዮጵያ ህዝብም አንገትም ህልውናም ጭምር ነው!
* ይሄ ያቀረቀረው የኢንጅነር ስመኘው ጭንቅላት ብቻ አይደለም! የኢትዮጵያውያን ህዝብ ተስፋ የያዘ ጭንቅላት ነው ያቀረቀረው!
ነፍስ ይማር!
የአባይ ጉዳይ ኢህአዴግ አጣብቂኝ ውስጥ በነበረበት እና የአረብ ስፕሪንግ መቀስቀስ ስጋት በኢትዮጵያም ተመሳሳይ አብዮት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚለው ትንበያ ጭንቀት ውስጥ ከቶት ስለነበር ለግዜው የህዝቡን ልብ ለማማለል የተጠቀመበት የመውጫ አጀንዳው እንደነበር የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ከእቅዱ እስከ ፍፃሜው ይወሰዳል ተብሎ የተቀመጠው የግዜ ሰሌዳ አሰልቺና የተንዛዛ መሆን ታክሎበት በቅርቡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ስለ አባይ(ህዳሴ ግድብ በችኮላ የተቀይረ ስም መሆኑ ይሰመርበት) የሰጡት ጠቋሚ መረጃ በብዙዎች ዘንድ የመነጋገሪያ አጅንዳ ከመሆን ሳያበቃ የሕዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ዛሬ (ሐሙስ ሐምሌ 19 ቀን 2010 ዓ.ም.) ጠዋት አዲስ አበባ አብዮት አደባባይ በመኪናቸዉ ዉስጥ ሞተዉ ተገኙ የሚለው ዜና የበለጠ አስደንጋጭና ከኢንጂነሩ ሞት ጀርባ ምን አይነት ከህዝብ የተደበቀ አጀንዳ ሊኖር ይችላል የሚለው ጥያቄ በእያንዳንዱ ልቦና ውስጥ እንዲጫር በር ከፍቷል ፡፡

ትዝብት
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግድቡ ዙሪያ የሰጡትን ጠቋሚ መረጃ ተከትሎ በኢንጂነሩ ላይ ስድብና ዘለፋ ሲያፋፍሙ የነበሩ ዛሬ በህልፈቱ የቀን ጅቦች በሉት እያሉ አዛኝ መስለው ጣቶቻቸውን ወደሌላ ቀስረው ስመለከት ከማፈርም በላይ ወዴት እየሄድን ነው የሚለው ነገር ከትላንቱ በባሰ ሁኔታ ያሰጨንቀኝ ጀምሯል፡፡
የዚህ ሰው መጨረሻ ይሄ መሆኑ በጣም ያሳዝናል!!! ወያኔን ማገልገል መጨረሻው ይሄ ነው!!!
አምሳሉ ገ/ኪዳን
የዓባይ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ መስቀል አደባባይ ላይ መኪናው ውስጥ እንዳለ ሞቶ ተገኘ እየተባለ ነው።
ወያኔ/ኢሕአዴግ በዓረቦቹ ጫናና መደለያ የዓባይ ግድብ ግንባታን ከነአካቴው ሊያቆመው መስማማቱ እየተወራ ባለበት ሰዓት የዚህ ታታሪ ሰው መገደል በቀጥታ ከግድቡ ጋር በተገናኘ ምክንያት መሆኑ ምንም የሚያጠራጥር አይመስለኝም፡፡ ብዙ ሊያወጣው የሚችለው ምሥጢር መኖሩ ይታመን ነበረ፡፡
በእርግጠኝነት የሞቱን ምክንያት በግል ጉዳይ አንባጓሮ እንደሆነ ማውራታቸው አይቀርም፡፡
የዚህ ሰው መጨረሻ ይሄ መሆኑ በጣም ያሳዝናል!!! ወያኔን ማገልገል መጨረሻው ይሄ ነው!!! ምድረ ሰበድባዳ ጥቅመኛ ሁላ ለዚህ ምስኪንና ትጉ ሰው ያልተመለሰ አረመኔ አገዛዝ ለኔ ይመለሳል ብለሽ አስበሽ የምትልከሰከሽ ሁሉ ልብ ብትይ ይሻልሻል!!!
አመድ አፋሹ ወገናችን ነፍስህን ይማረው!!! ለመላ ቤተሰቡና ዘመድ አዝማዱ መጽናናትን እመኛለሁ!!!