ውብሸት ሙላት
ሰኔ 16 ቀን መስቀል ዐደባባይ የተፈጸመውን የሽብር ድርጊት የምርመራ ውጤቱን ወይም ያለበትን ደረጃ ሕዝቡ የማወቅ መብት ስላለው ይፋ ይደረግ።
ዛሬም እዚያው ቦታ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኝተልዋ። ከወር በፊት በእርስዎ ላይ ስለተቃጣው ጥቃት አቀናባሪዎች ማንነት ምንም ዓይነት መረጃ ለሕዝብ ሳይደረስ 1ወር ከ3 ቀናት ሆነ። በዚህ እለት ኢ/ር ስመኘውም ሞቶ ተገኘ።
የምርመራ ውጤቱ በየጊዜው ይፋ አለማድረግ ሕዝብን ከፍተኛ ስጋት፣ ጥርጣሬ ፣ አለመተማመን፣ ጣት መቀሳሰር ብሎም ግጭት ውስጥ ሊከት ይችላል።
የአንድ ግለሰብ ሞት ዓለምን ጦርነት ውስጥ ከቷል። አገራችንንም የእርስ በርስ እልቂት ውስጥ ላትገባ የምትችልበት ዋስትና የለም። የሚከፋው ደግሞ በመረጃ እጦት፣ ባሉባልታና በሀሜትም ጭምር አገር ስጋትና ግጭት ውስጥ ልትገባ የምትችልበት አጋጣሚም መኖሩ ነው።
የሰኔ 16ቱም የኢንጅነር ስመኘውም የምርመራ ውጤት በየጊዜው ይፋ ይደረግ። ሕዝብ በመላምት እየተደናገረ አላስፈላጊ ግጭትና ትርምስ ውስጥ እንዳይገባ ይታደጉት።
ኢንጂነር ስመኘው የተገደሉት መስቀል አደባባይ ሣይሆን በሌላ ስፍራ እንደሆነ እገምታለሁ። ምክንያቶቼ…
ኤርሚያስ ቶኩማ
* የህዳሴ ግድብ ስራ አስኪሃጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ በእለቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ቀጠሮ ነበራቸው
* አዲስ አበባ የተገኙት መስቀል አደባባይ መኪናው ውስጥ ተገድለው ተገኝተዋል
* የሕዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅና ኢንጂነር አስከሬን ለምርመራ ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል መላኩን የፖሊስ ታውቋል
1, መኪናው የቆመበት ስፍራ የመኪና መንገድ ላይ ሣይሆን ኳስ መጫወቻ ሜዳው ላይ ነው በምንም ምክንያት ኢንጂነር ስመኘው መኪናውን እዛ ቦታ ሊያቆመው አይችልም።
2, የኢንጂነር ስመኘው መኖሪያ ቤቱ የረር መብራት ሃይል አካባቢ ነው ደምበል አካባቢ ወደሚገኘው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለመሄድ ሊመርጠው የሚችለው መንገድ የቦሌን ወይም የኡራኤልን መንገድ ነው። መኪናውን እንደምናየው ግን ከሜክሲኮ ወይም አምባሳደር መንገድ መጥቶ ወደደምበል እንደሚሄድ ያሳያል።
….. ከእነዚህ ግምቶች በመነሳት ኢንጂነር ስመኘው ሌላ ቦታ ተገድሎ አብዮት አደባባይ እንደተጣለ መገመት አይከብድም። ለማንኛውም መርማሪ ቡድኑ ነፃ ሆኖ ይመረምራል ብዬ ባላስብም የሚሆነውን አብረን እንጠብቅ።
የኢ/ር ስመኘው ቢሮ በእሳት እንዳይቃጠል ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል!!
ስዩም ተሾመ
ባለፈው ሰሞን በህዳሴው ግድብ የሚገኙ ሰራተኞች ሁለት አይነት #payroll ለምን ታስፈርሙናላቸሁ” በማለታቸው የተወሰኑ ሰራተኞች #ጭለማ ቤት ታስረው የነበረ ሲሆን አሁንም ድረስ አልተፈቱም፡፡ ዛሬ ደግሞ የኢ/ር ስመኘውን ሞት ተከትሎ በህዳሴው ግድብ የአመፅና ተቃውሞ እንቅስቃሴ መጀመሩን በቦታው ከሚገኙ ሰዎች መረጃ ደርሶኛል፡፡ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በኢ/ር ስመኘው #ቢሮ ላይ #የእሳት_አደጋ በማድረስ መረጃዎችን የማጥፋት ሙከራ ሊደረግ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡ ስለዚህ እንዲህ ያለ እኩይ ተግባር እንዳይፈፀም የሚመለከታቸው አካላት ቅድመ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል፡፡