>
5:14 pm - Tuesday April 20, 6173

ዛሬ የተገደለው 100 ሚሊዮን ህዝብ ተስፋ ነው!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

ዛሬ የተገደለው 100 ሚሊዮን ህዝብ ተስፋ ነው!!!
ቬሮኒካ መላኩ
ዛሬ የተገደለው አንድ ስመኜው በቀለ አይደለም። ዛሬ የተገደለው 100 ሚሊዮን ህዝብ ተስፋ ነው። ዛሬ በአባይ ወንዛችን ላይ የተቃጣ ግዲያ ነው።
ሁልጊዜ በቀን ጅብ ማሳበብ አይሰራም ። ዶ/ር አቢይ አህመድ ይችን ታላቅ አገር ከነሙሉ ክብሯና ግዛቷ ለማስተዳደር ቃል ገብቶ ተረክቧል ። በዚህም መሰረት በአገሪቱ ለሚፈፀመው እያንዳንዷ ተግባር  በህግም በሞራልም ተጠያቂነት አለበት። ይሄ የስነ መንግስት ሀ ሁ ነው።
የዛሬውን የመስቀል አደባባይ ግዲያ ትተን  እንኳን አሁን በተጨባጭ ከቀን ጅብ የበለጠ አናርኪ እየፈጠረ ያለው ቄሮ የሚባለው ቡድን አይደለም ወይ ?
ባሌ ውስጥ 17 ሰዎች ከተቀበሩ ገና ሳምንት እንኳን አልሞላቸውም።
የኦሮሚያ ክልሉ የገጠር ዘርፍ አላፊ አዲሱ አረጋ  ቄሮ አገር እየበጠበጠ እንደሆነ ተናግሯል። ትናንት በኢሳት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሀረር ከተማ ህዝብ ቄሮ ወደ ሀረር ከተማ የሚያልፈውን ዋናውን የውሃ ጋን ቁልፍ በመረከቡ በውሃ ጥም እየተሰቃዩ እንደሆነ ዘግቧል። ሴቶች በቡድን እየተደፈሩ ነው። ባሌ ፣ ወለጋ ፣ሀረርጌ አሩሲ ህግ አለ ማለት አይቻልም። ህዝቡ በስጋት ነው የሚኖረው።  ቁልቢ የሚሄዱ ምእመናን እንኳን መንገድ በቄሮ ተዘግቶባቸው ከ3 ሰዎች በላይ ሞተዋል።
አገሪቱ በተለይ ኦሮሚያ ውስጥ አናርኪ እየተፈጠረ ነው። ኦነግና ቄሮ የሚባል የነጋበት የጅብ ስብስብ በጉያ አቅፎ ወያኔ ላይ እኝኝኝ ማለት አያስኬድም።
አሁንም አገር የሚኖረው ህግ ሲከበር ብቻ ነው። ቄሮ የሚባለውን ቡድን ወይ በመንግስት መዋቅር ውስጥ አስገቡትና እውቅና ስጡ አሊያም ደሞ ህግ አክብረው ወደ ቤታቸውና ስራቸው ይግቡ ። ካለበለዚያ ወደፊት የአገራችንና የህዝቡ እጣ ፋንታ ከአምናው የከፋ ይሆናል።
*****
አንድ አገሬን እወዳለሁ የሚል መሪ አገር በሀዘን አመድ ነስንሳ ማቅ ስትለብስ የአውሮፕላኑን አፍንጫ ወደ ኢትዮጵያ አዙሮ እየበረረ መምጣት አለበት ።
ጠ/ሚ አቢይ አህመድ  ለዚህ የኢትዮጵያ ሀዘን ቀን ያልደረሰ መቼ ሊደርስ ነው?።
በኢንጂነር ስመኘው  በቀለ ሞት ዙሪያ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል የሰጡት መግለጫ
 
Filed in: Amharic