>

መለስ ዜናዊ ከሞተ በኋላ ኢትዮጵያ የምትተዳደረው በስውር መንግስት ነው፤  (ካሳ አንበሳው)

መለስ ዜናዊ ከሞተ በኋላ ኢትዮጵያ የምትተዳደረው በስውር መንግስት ነው፤
ካሳ አንበሳው
*አብይ የቀውስ ጊዜ መሪ አይደለም፤ እርሱ “ቀኝህን ሲመታህ ግራህን ስጠው” የሚል ወንጌላዊ ነው
 
* አብይ በዚሁ ከቀጠለ የሚካኤል ጎርባቾቭን ስህተት በዚህ ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያ ይደግመዋል፤
ኤርሚያስ ለገሰ ሰለ ”ካሳንችሱ መንግስት” ነግሮናል፤ ከኤርሚያስ የተሰወሩ ሌሎች በርካታ መንግስቶች እንደሚኖሩ አይጠረጠርም፤ ኃይለማሪያ ደሳለኝ ዛጥ ብሎት “የግል እስር ቤት አለ” ብሎ ነበር፤ ይህንኑ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር በወጣ ማግስት አረጋግጦልናል፤ ጌታቸው አሰፋ ከመቀመጫው ተነሳ እንጂ ደህንነቱ አሁን እሱ ጋር ነው፤ ብታምንም ባታምንም ህወሓት ሀገሪቱን (በአንድ ጀንበር) ወደለየለርት ብጥብጥ የመክተት አቅም አለው፤
አብይ የቀውስ ጊዜ መሪ አይደለም፤ የቀውስ ጊዜ መሪ ቁርጠኛ መሆን አለበት፤ ቆምጨጭ ማለትን ይጠይቃል፤ እንደ ቆቅ ንቁ፤ እንደ ነብር ተወርዋሪ፣ እንደ አንበሳ አስፈሪ፤ እንደ እባብ ተናዳፊ መሆን ግድ ይላል፤ አብይ አህመድ ወንጌላዊ ነው፤ “ቀኝህን ሲመታህ ግራህን ስጠው” በሚል አስተምሮ ህወሓትን መግራት አትችልም፤ ወያኔን በጥፊ ካላጠናፈርከው በቀር “ይቅርታ እና መደመር” ብለህ ብትለፈልፍ አይገባውም፤ ገዱ አንዳርጋቸው እና ለማ መገርሳ ከአብይ የተሻለ የቀውስ ጊዜ መሪ ይወጣቸዋል ባይ ነኝ፤
ከአሁን በኋላ መወቀስ ያለበት የአብይ አህመድ መንግስት እንጂ ህወሓት አይደለም፤ ህወሓት በተፍጥሮው አሸባሪ ነው፤ መንግስት ዜጎቹን ከአሸባሪዎች መጠበቅ ካልቻለ ተጠያቂው መንግስት እንጂ አሸባሪው አይደለም፤
Filed in: Amharic