>

የዲሲ ፍጥጫ!!! (አርአያ ተስፋማርያም)

የዲሲ ፍጥጫ!!!
አርአያ ተስፋማርያም
ጠ/ሚ/ር አብይ ነገ ዲሲ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ስብሰባው ግን በሰላም የመጠናቀቁ ነገር አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። በተለይ ማን እንደወከላቸው የማያታወቁና “የሚዲያ አካል” ብለው ራሳቸውን የወከሉ ግለሰቦች ውጥረቱን እያከረሩት ይገኛሉ። በቀደም ጋዜጠኛ ያልሆኑ 50 ሰዎች ተመርጠዋል ተብሎ ጥቆማ ለማቅረብ ተሞክሯል። “አጣርተን መፍትሄ እንሰጣለን” ያሉትም አድፍጠው ዝም ብለዋል። ትላንት ደግሞ 1.500 ሰው እንዴትና በምን መስፈርት መረጣችሁ?..የምንፈልጋቸው ሰዎች እነደታማኝ በየነ ያሉ አክቲቪስቶች እንዳይገኙ አድርጋችኋል፣ ስለዚህም ስብሰባው ይሰተጓጎላል..የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል። አቤል የተባለው ተወካይ ሲመልስ “ብሄርና ዘር ለማመጣጠን ተሞክሮ ነው የመረጥነው። ከእያንዳንዱ ብሄርና ብሄረሰብ..” በሚል እጅግ የሚያሳፍር የደንቆሮ ምላሽ ሰጥቷል። አሜሪካ ሰው በሰውነቱ እንጂ..በቀለሙና በጎሳው፣ በብሄሩና በመጣበት አገር አይመዘንም! ይሄን አስቀያሚ ርካሽ የፖለቲካ ቁማር ድጋሚ አሜሪካ ላይ መስማት ያሳምማል! በዚህ አላበቃም…”ሌሎች ስብሰባዎች እናዘጋጃለን። ወደፊት ከጠ/ሚ/ሩ ጋር ተገናኝተን የምንወያይበት መድረክ ይዘጋጃል” ብሎ አረፈው። ይህ ሰው ገለልተኛ ነው እየተባለ እንዴት ስለወደፊቱ “እንሰበስባለን” ሊል ቻለ?..ደግሞስ ምን የሚሉት የሽወዳ ጨዋታ ነው?..ለማንኛውም እነዚህ ግለሰቦች በመጨረሻ ላይ ከውጭ ጉዳይ ዋና ቢሮ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ሳያውቁት አምልጧቸው ተናግረዋል። እዛ ላይ ነገሩ አበቃ! .
Filed in: Amharic